Home News and Views ጅቡቲ ያሉ ስደተኛ ኢትዮጵያውያን እንግልት እየደረሰብን ነው አሉ

ጅቡቲ ያሉ ስደተኛ ኢትዮጵያውያን እንግልት እየደረሰብን ነው አሉ

BBC በጅቡቲ የሚኖሩ ስደተኛ ኢትዮጵያኖች እንግልትና በደል እየተፈፀመብን ነው ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል። በጂቡቲ ነዋሪነቱን ያደረገው አቶ ሐምዛ ቶላና በርካታ ኢትዮጵያውያዊያን ድብደባ እንደተፈፀመባቸው ለቢቢሲ ገልጿል።

የአምስት ልጆች እናት የሆኑት ወይዘሮ ፋጤ ሁሴን በበኩላቸው “ወደ ኢትዮጵያ የሚወስደው መንገድ ዝግ ነው ህፃናት ይዘን መጥተን የምንገባበትና የምንወጣበት ጠፍቶናል” ብለዋል።

ጉዳት ደረሰባቸው ኢትዮጵያውያኑ ስደተኞች የህክምና አገልግሎት እያገኙ እንዳልሆነና በጅቡቲ የሚገኘው ኢምባሲ ምንም አይነት ድጋፍ እያደረገላቸው እንዳልሆነ ገልፀዋል።

አቶ ሐምዛ እንደሚናገሩት “ነጋዴ ነበርኩ የንግድ ስራዬን ትቼ ሸሽቼ ነው ያለሁት ወደ ቤቴ መመለስ እፈራለሁ” ብለዋል።

እንዲህ አይነት ችግር እሁድ እለት መከሰቱን ሰኞ ጠዋትም ቀጠሎ እንደነበር ስደተኞቹ ለቢቢሲ ተናግረዋል።

ቢቢሲ ያናገራቸው ስደተኞች በርካታ ሰዎች ስለመጎዳታቸው ገልፀው የሞተ ሰው ስለመኖሩ ባያውቁም ከመካከላቸው አንዱ ግን ስለሞቱ ሰዎች መረጃ እንዳለው ተናግሯል።

በጅቡቲ የኢትዮጵያ አምባሳደር የሆኑት ሻሜቦ ፊታሞ በስደተኞችና በነዋሪው መካከል በተፈጠረ ግጭት ቀላል ጉዳት መድረሱን አረጋግጠዋል።

ግጭቱ በምን እንደተነሳና ምን ያህሉ ጉዳት እንደደረሰባቸው እንደማያውቁም አስረድተዋል።

አምባሳደሩ እንዲህ አይነት ግጭት ከ15 ቀን በፊት እንደጀመረና በትናንትናው እለት ወደ 7 ሰዎችን ቀላል ጉዳት አጋጥሟቸው ሆስፒታል መላካቸውንም ለቢቢሲ ገልፀዋል።

 

ኢምባሲው በፌስ ቡክ በሚለቀቁ “ሀሰተኛ ወሬዎች” ምክንያት እንደሚቸገር ተናግረው የኢትዮጵያውያንን ደህንነት ለመጠበቅ ከጅቡቲ መንግስት ጋር አብረው እየሰሩ መሆኑን ተናግረዋል።

” ከፖሊስ ኮሚሽነር፣ ከሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር፣ ከውጭ ጉዳይና ከጠቅላይ ሚኒስትር ጋር ኢትዮጵያውያዊያን ጥቃት ሳይደርስባቸው ፖሊስ ደህንነታቸውን እንዴት እንደሚጠብቃቸው ተነጋግረናል። በትናንትናውም ላይ የጁቡቲ መንግስት መግለጫ እንዲያወጣ አድርገናል” ብለዋል።

አክለውም ጥቃቱን ያደረሱ አካላትም በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ተናግረዋል።

በጅቡቲ በስፋት ስለተገደሉ ኢትዮጵያውያን መረጃዎች እየወጡ መሆናቸውንና ቢቢሲም ያነጋገራቸው አካላት ይህንን እንዳረጋገጡ በተጠየቁበት ወቅት”ተገደለ ብለው ሪፖርት ያደርጋሉ በስፍራው ስንሄድ ምንም ነገር የለም” በማለት የወሬውን ሀሰተኝነት ተናግረዋል።

በተጨማሪም በጅቡቲ 1500 ሕገወጥ ስደተኞች በቁጥጥር ስር ውለው በተለያዩ እስርቤቶች እንደሚገኙ ገልፀዋል።

አይ ኦ ኤም በጅቡቲ መጠለያ ስለሌለው ኢምባሲው ከጠባብ እስር ቤቶች ወደ ግቢ ወዳላቸው ሰፋፊ እስር ቤቶች እንዲዛወሩ እየሰራ ነው ብለዋል።

“በስፍራው ጥቃት እንዳይደርስባቸው አድርገናል” ብለዋል።

በጅቡቲ የሚገኙ ስደተኞች ወደ ሀገር ቤት የመመለስ ፍላጎት አላቸው ሲሉም ተናግረዋል።

የጅቡቲ ፖሊስ አዛዥ የሆኑት አብደላ አብዲ በትንትናው ዕለት ኢትዮጵያውያን ላይ ጥቃት የፈፀሙ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ለቢቢሲ አረጋግጠዋል።

2 COMMENTS

 1. To all please pick a less addicted place to go in exile to. Narcotic khat dominates Djibouti life.Most part of the whole world is in a crisis because of drugs narcotics.Exile is not a solution especially if you are headed to addicted people’s destination.I live as a refugee in one of the most the richest cities in the world but I donot feel it since drug addiction is everywhere.The situation here is not much different than Djibouti. Addcition to drugs is rampant here too.Foreigners from Middle East and Africa are suffering.Even people born and raised in the city are suffering.There is not enough home,medical services , social services and so on .People used to live in camp like make shift tents but the city took our tents away with all our belongings.

  San Francisco struggles with growing homelessness problem
  Jul. 25, 2018 – 2:18 – The City by the Bay spends hundreds of millions of dollars each year trying to help an estimated 7,500 homeless people; critics say what’s needed isn’t more money, but a bold new approach.The number of tents on San Francisco streets has been cut by more than half in the past two years, but despite the shrinking numbers, the street behavior by the homeless, the mentally ill and the drug-addled continues to be a challenge — with no quick solution in sight………………

  https://www.sfchronicle.com/bayarea/matier-ross/article/Fewer-tents-on-SF-streets-but-drugs-feces-13139181.php

  https://www.reuters.com/article/us-djibouti-drugs/narcotic-khat-dominates-djibouti-life-idUSL2717658520070827

  http://video.foxnews.com/v/5813836795001/?#sp=show-clips

  • ከጅቡቲ ከ30 ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያን ተፈናቀሉ
   (ኢሳት ዲሲ–ነሐሴ 7/2010) ከጅቡቲ ከ30 ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያን ተፈናቅለው ወደ ኢትዮጵያ መግባታቸው ተገለጸ።

   በአብዛኛው የኦሮሞ ተወላጅ የሆኑት ኢትዮጵያውያን ጥቃትን ሸሽተው የተሰደዱ መሆናቸው ታውቋል።

   በምዕራብ ሀረርጌ አሰቦት በትምህርት ቤቶች ተጠልለው የሚገኙት የጅቡቲ ተፈናቃዮች ምግብና ውሃ አጥተው በመሰቃየት ላይ መሆናቸውን የደረሰን መረጃ ያመለክታል።

   በሌላ በኩል በምስራቅ ሀረርጌ ትላንት በተፈጸመ ጥቃት ከ30 በላይ ሰዎች መገደላቸው ታውቋል።

   ጥቃቱን የሶማሌ ክልል ልዩ ሃይል መፈጸሙን መረጃው አመልክቷል።

   ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው የፖለቲካ ውጥረት ድንበር ተሻግሮ አሉታዊ ተጽዕኖ እየፈጠረ ነው።

   በምስራቁ የኢትዮጵያ ክፍል የተነሳው ግጭት ጅቡቲ በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ላይ አደጋ ማምጣቱን ነው ለኢሳት የደረሰው መረጃ የሚያመለክተው ።

   በሰሞኑ ግጭት በቀል እየተፈጸመብን ነው ባሉ የአንድ ብሄር አባላት ጥቃት እንደደረሰባቸው የገለጹ ኢትዮጵያውያን የኦሮሞ ተወላጆች ከሚኖሩበት ጅቡቲ ሸሽተው ወደ ሀገር ቤት በመሰደድ ላይ መሆናቸው ታውቋል።

   ባለፉት አምስት ቀናት ከ30ሺህ በላይ የሚሆኑ ዜጎች ከጅቡቲ መሸሻቸውንና በአሰቦት አከባቢ ተጠልለው እንደሚገኙ ኢሳት ያነጋገራቸው አንድ ነዋሪ ገልጸዋል።

   እነዚህን ዜጎች በአሰቦት ከተማና በዙሪያዋ ባሉ ትምህርትቤቶች ውስጥ በማስጠለል ጊዜያዊ ድጋፍ እየተደረገላቸው መሆኑንም ለማወቅ ተችሏል።

   በአሰቦት ከተማ የውሃ አቅርቦት ከተቋረጠ ከ15 ቀናት በላይ በመሆኑ ከጅቡቲ ተፈናቅለው ለመጡት ዜጎች የሚጠጣ ውሃ ለማግኘት እንዳልተቻለ ጉዳዩን የሚከታተሉት የአሰቦት ከተማ ነዋሪ ለኢሳት ገልጸዋል።

   የምግብና የውሃ ችግር ተፈናቃዩቹን አደጋ ላይ በመጣሉ መንግስት አፋጣኝ ምላሽ እንዲሰጥ ጥሪ ቀርቧል።

   ከጅቡቲ ሸሽተው ኢትዮጵያ የገቡት ዜጎች እንደሚሉት በተፈጸመው ጥቃት በርካታ ሰዎች ተገድለው መንገድ ላይ ቀርተዋል።

   አሁንም ጥቃቱ ባለመቆሙ ዜጎች ከፍተኛ አደጋ ውስጥ ናቸው ሲሉ ስጋታቸውን ገልጸዋል።

   በሚቀጥሉት ቀናት ከጅቡቲ ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡ ዜጎች ቁጥር የሚጨምር በመሆኑ የሰብዓዊ ቀውስ ሳይከሰት መንግስት መፍትሄ እንዲሰጥ ተጠይቋል።

   በሌላ በኩል በምስራቅ ሀረርጌ ዞን መዩ ሙለቂ ወረዳ በተፈጸመ ጥቃት በርካታ ሰዎች መገደላቸውን ለማወቅ ተችሏል።

   ቢቢሲ ኦሮምኛ እንደዘገበው በታጠቁ ሃይሎች በተፈጸመው ጥቃት ህጻናትና አዛውንቶችን ጨምሮ ከ30 በላይ ሰዎች ተገድለዋል።

   በመቶዎች የሚቆጠሩ ቆስለዋል። ጥቃቱን የሶማሌ ክልል ልዩ ሃይል ፈጽሞታል የሚል መረጃ እንዳለም ተጠቅሷል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here