Home News and Views ፕ/ር አለማየሁ ገ/ማ፣ታማኝ በየነና ኦባንግ ሜቶ የተካተቱበት የዳያስፖራ ትረስት ፈንድ አማካሪ ምክር...

ፕ/ር አለማየሁ ገ/ማ፣ታማኝ በየነና ኦባንግ ሜቶ የተካተቱበት የዳያስፖራ ትረስት ፈንድ አማካሪ ምክር ቤት አቋቋመ

ጠ/ሚኒስትር አብይ አህመድ በተለያዩ ሀገራት የሚገኙ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን የተሻለች ኢትዮጵያን ለመገንባት በሚደረገው ጥረት የበኩላቸው እንዲወጡ ጥሪ ማቅረባቸውን ተከትሎ አስተባባሪ ኮሚቴ መቋቋሙን የጠላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ፍፁም አረጋ ገልጸዋል።

የዳያስፖራ ትረስት ፈንድ  አማካሪ ኮሚቴ  15 አባላት ያሉት ሲሆን በተለያየ ሙያ የተሰማሩ ታዋቂ ኢትዮጵያዊያን ናቸው።የኮሚቴው አባላት ስም ዝርዝርም፦

 1. ፕሮፌሰር አለምአየሁ ገብረማርያም – የምክር ቤቱ ሊቀመንበር
 2. ዶክተር ብስራት አክሊሉ
 3. አቶ ገብርኤል ንጋቱ
 4. አቶ ካሳሁን ከበደ
 5. ዶክተር ለማ ሰንበት
 6. ወይዘሮ ሉሊት እጅጉ
 7. ዶክተር መና ደምሴ
 8. ወይዘሮ ሚሚ አለማየሁ
 9. አቶ ሚኒልክ አለሙ
 10. አቶ ኦባንግ ሜቶ
 11. አቶ ሮብሰን ኢታና
 12. አቶ ታማኝ በየነ
 13. አቶ ተሽታ ቱፋ
 14. አቶ ይሄነው ዋለልኝ እና
 15. አቶ ኤሊያስ ወንድሙ የምክር ቤቱ አባላት ሆነው መመረጣቸውን አቶ ፍፁም አረጋ በትዊተር ገፃቸው ዛሬ አስታውቀዋል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here