Home News and Views ጠቅላይ አቃቤ ህግ በፀረ-ሽብር ህጉ ክፍተቶች ዙሪያ ሲያካሄድ የነበረውን የጥናት ውጤት ይፋ...

ጠቅላይ አቃቤ ህግ በፀረ-ሽብር ህጉ ክፍተቶች ዙሪያ ሲያካሄድ የነበረውን የጥናት ውጤት ይፋ አደረገ

የህግና ፍትህ ጉዳዮች አማካሪ ጉባዔ የፀረ-ሽብር ህግ እና የሲቢክ ማህበራት ህግ ላይ ባሉ ክፍተቶች ዙርያ ባለፉት ሶስት ወራት ጥናት ሲያካሂድ እንደነበረ የጠቅላይ አቃቤ ህግ የህዝብ ግንኙነትና ኮሚኑኬሽን ዳይሬክተር አቶ ተስፋዬ ደንደአ ለኢቲቪ ገልፀዋል፡፡

እነዚህ ሁለቱ ህግጋት ላይ ህብረተሰቡም ሆነ የተፎካካሪ ፖለቲካ ፓርቲዎች የሚያነሱትን ጥያቄ ከግምት በማስገባት መንግስት የፖለቲካ ምህዳሩን ለማስፋት ካለው ቁርጠኝነትም ጋር ተያይዞ ህግጋቱን ሲመረምር እንደነበረም ነው የገለፁት፡፡

በዚህ መሰረት ጉባዔ በፀረ-ሽብር ህጉ ከለያቸው ክፍተቶች አንዱ የአዋጁ ይዘትና አተረጓጎም ነው፡፡

በመረጃ አሰባሰብ ረገድም ክፍተት እንዳለበት ተመልክቷል፡፡

በሽብር ወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር የሚውሉ ሰዎች የዋስትና መብት አለማግኘታቸውና የፍርድቤትን ስልጣን መገደብም ህጎቹ ላይ የሚታዩ ክፍተቶች በሚል በጉባኤው ታይተዋል፡፡

የህጉ አተገባበርም የጐላ ክፍተት ያለበት መሆኑን ነው የተገለፀው፡፡

በዚህም መሰረት ጉባዔዉ ሶስት አማራጮችን አቅርቧል፡፡

ህጉ ያስፈልጋል አያስፈልግም የሚለው ከነዚህ ውስጥ ዋነኛው ነው፡፡

በዚህ ጉዳይ ላይም በመጪው ዕሮቡ የተመዘገቡም ሆነ ያልተመዘገቡ የተፎካካሪ የፖለቲካ ፐርቲዎችና ሌሎች አካላት በሚገኙበት የጥናቱ ውጤት ላይ ግብዓት የሚሰበሰብ ይሆናል ፡፡

የህግና ፍትህ ጉዳዮች አማካሪ ጉባዔ በሌሎች ህጐች ላይም የማሻሻያ ጥናቶች እያደረገ ነው፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here