Home News and Views በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ካማሽ ዞን ላይ የተፈጠረዉን ግጭት የሚያጣራ ገለልተኛ ቡድን ተቋቋመ

በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ካማሽ ዞን ላይ የተፈጠረዉን ግጭት የሚያጣራ ገለልተኛ ቡድን ተቋቋመ

የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል በካማሽ ዞን ላይ የተፈጠረዉን ግጭት የሚያጣራ ገለልተኛ ቡድን ተቋቋመ፡፡

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ካማሽ ዞን 4 አመራሮች ላይ የተፈፀመዉን ግድያ ተከትሎ በተፈጠረዉ ግጭት የዜጎች ህይወት እና ንብረት መጥፋቱንና በርካቶች ከቀያቸዉ መፈናቀላቸዉ ይታወሳል፡፡

በፌደራል የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ሃላፊ ኮሚሽነር ዶ/ር አታክልቲ ገብረኪዳን ለኢቢሲ እንደተናገሩት የግጭቱን መንስዔና አባባሽ ሁኔታዎችን ጨምሮ የደረሰዉን ጉዳት የሚያጣራ ከሁሉም ክልሎች የተዉጣጣ ገለልተኛ ቡድን በጥቅምት ወር ስራ እንደሚጀምር ገልፀዋል፡፡

አልመሀልና ዳለቲ በተባሉ አካባቢዎች ላይ ቡድኑ ከካማሹ ጋር አብሮ የማጣራት ስራ እንደሚካሄድባቸውም ኮሚሽነሩ አስታውቀዋል፡፡

በአሶሳ ጉምባ በዳንጉር፣በሽርቆሌ፣በማኦና ኮሞ ልዩ ወረዳዎች ላይ ተፈጥሮ በነበረዉ ግጭትና የዜጎች መፈናቀል አጣሪ ቡድን የምርመራ ስራዉን አጠናቆ ለሰብዓዊ መብት ኮሚሽን መስሪያ ቤት ማቅረቡን ዶ/ር አታክልቲ ገልፀዋል፡፡

በክልሉ የተከሰተዉን የሰብዓዊ መብት ጥሰት ጨምሮ በአገሪቱ ተፈጥሮ የነበረዉን ግጭት የተመለከተ የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ሪፖርት በቅርቡ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ይፋ እንደሚደረግ ተናግረዋል፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here