Home News and Views በአንድ በህግ የምትተዳደር ሀገር ዉስጥ ሁለት መንግስት አብሮ ሊኖር አይችልም:: (አቶ አዲሱ...

በአንድ በህግ የምትተዳደር ሀገር ዉስጥ ሁለት መንግስት አብሮ ሊኖር አይችልም:: (አቶ አዲሱ አረጋ ቂጤሳ-የኦሮሚያ ክልል የገጠር ፖለቲካ የኦዴፓ ዘርፍ አላፊ)

ክኦሮሞኛ የተተረጎመ
********
በአንድ በህግ የምትተዳደር ሀገር ዉስጥ ሁለት መንግስት አብሮ ሊኖር አይችልም::መንግስት እና ተፎካካሪ ፓርቲዎች በሰላም ተከባብረዉ ድርሻቸዉን አዉቀዉ በሰላም እና በህግ አግባብ ተፎካክረዉ አብሮ መኖር ያለነዉ ዘመናዊነትም ነዉ::የህግ የበላይነትን የማስከበር: የጦር መሳርያ መያዝ እና መምራት የመንግስት ሀላፊነት እና ድርሻ መሆኑን ሊሰመርበትና ሊታወቅ ይገባል::(Only as a monopoly as means of violence)የፖለታካ ድርጅቶች የመንግስት ስልጣን ለመያዝ በሰላማዊ መንገድ መታገል ትጥቃቸዉ ሀሳብ ነዉ ! ትጥቃቸዉ የፖለቲካ ፕሮግራማቸዉና ደጋፊዎቻቸዉ ናቸዉ::

ከዚህ ዉጪ በየትኛዉም ሀገር ዉስጥ አንድ የፖለቲካ ተፎካካሪ ፓርቲ በአንድ በኩል በሰላማዊ ትግል በሌላ ጎን ደግሞ መሳርያ ታጥቆ መንቀሳቀስ በጭራሽ የሚቻል አይደለም::በየትኛዉም ሀገር ሆኖም አያዉቅም::ኦሮሞ መሳርያ መታጠቅ ማለት እና የፖለቲካ ፓርቲዎች ከትጥቅ ትግል ወደ ሰላማዊ ትግል የተጋበዘ አካል ትጥቅ መፍታት የለበትም የሚል ጉዳይ የሚገናኝ አይደለም ::ስለሆነም ይህ ሁለት ጉዳይ አብሮ ማምታታት ተቀባይነት የለዉም ::

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here