Home News and Views ኦነግ ወደ ሀገር የገባው ትጥቅ ፈትቶ ነው፣ የቀረውን ትጥቅ መፍታት አለበት፤ ካልሆነ...

ኦነግ ወደ ሀገር የገባው ትጥቅ ፈትቶ ነው፣ የቀረውን ትጥቅ መፍታት አለበት፤ ካልሆነ መንግስት ትጥቅ የማስፈታቱን ስራ ይሰራል:- የመንግስት ኮ/ጉ/ጽ/ቤት

ኦነግ ወደ ሀገር የገባው ትጥቅ ፈትቶ መሆኑንና አሁንም ቢሆን የቀረውን ትጥቅ መፍታት እንዳለበት፣ ካልሆነ ግን መንግስት የዜጎችን ደህንነት #ለማስጠበቅና ህገመንግስታዊ ስርዓቱን ለማስጠበቅ ሲል ትጥቅ #የማስፈታቱን ስራ እንደሚሰራ የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ካሳሁን ጎፌ ገልጸዋል፡፡

ከሰሞኑ የኦነግ አመራር አቶ ዳውድ ኢብሴ ከዋልታ ቴሌቪዥን ጋር በነበራቸው ቆይታ ከመንግስት ጋር ትጥቅ ለመፍታት አልተደራደርንም፤ ትጥቅ የሚፈታም የሚያስፈታም የለም ማለታቸውን ተከትሎ ዛሬ የኢፌዲሪ መ/ኮ/ጉ/ፅ/ቤት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ካሳሁን ጎፌ በጉዳዩ ላይ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

መንግስት የፖለቲካ ምህዳሩን ለማስፋት ባደረገው የሰላም ጥሪ መሰረት በርካታ የፖለቲካ ድርጅቶችና የትጥቅ ትግል ሲያደርጉ የነበሩ ሀይሎች ወደ ሀገር መግባታቸውን ያስታወሱት አቶ ካሳሁን ኦነግም ወደ ሀገር ሲገባ 1300 ያህል ጦሩን ትጥቅ አስፈትቶ መግባቱንና ጦሩም በአሁኑ ሰአት በጦላይ ማሰልጠኛ ስልጠና እየተከታተለ ነው ብለዋል፡፡

ኦነግ በአስመራ በተደረጉ ሶስት ድርድሮች በሰላማዊ መንገድ ወደ ሀገር ገብቶ ለመፎካከር መስማማቱ የሚታወቅ ነው፤ ለዚህም ወደ ሀገር ሲገባ ደማቅ አቀባበል ተደርጎለታል ያሉት አቶ ካሳሁን በድርድሩ ወቅት ትጥቅ የመፍታት ጉዳይ ያልተነሳው የመደራደሪያ ጉዳይ ስላልሆነ ነው ብለዋል፡፡

ሰላማዊ ትግል የሚደረገው በሀሳብ እንጅ በአፈሙዝ ስላልሆነ ትጥቅ የመፍታትን ጉዳይ ለድርድር የማናቀርበውና ቀይ መስመር ነው ሲሉ አቶ ካሳሁን በመግለቻቸው ተናግረዋል፡፡

ስለሆነም ኦነግ አቋሙን እንደገና በመፈተሽ ትጥቁን እንዲፈታ መንግስት ጥሪውና ያስተላልፋል ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው ካልሆነ ግን የዜጎችን ደህንነት ለማስጠበቅና ህገመንግስታዊ ስርዐቱን ለማስጠበቅ ሲል መንግስት ትጥቅ የማስፈታቱን ስራ ይሰራል ብለዋል፡፡

መንግስት ህግን የማስከበር ስራውን በቆራጥነት ስለሚሰራ መላው ህዝብ የደህንነት ችግር ይገጥመኛል በማለት ስጋት ላይ እንዳይወድቅና እንዳይደናገር አቶ ካሳሁን መልእክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

ምንጭ:- የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት

 

2 COMMENTS

 1. የኦነግ ጥያቄ የኦሮሞ ህዝብ በኢትዮጵያ ፖለቲካ የሚገባውን ሚና መጫወት አለበት ነው። ይህም ትክክል ነው። መደነቅ ያለበትን እናድንቅ።ኦነግን ማመስገን ዘረኛ-ነት ከሆነ ኦነግን መተቸት ቅዱስነት ሊሆን ነው? የራሴን ለራሴ ያለ ስህተት ከሆነ የራሴም ለራሴ የናንተም ለኔ የሚልስ ምን ሊባል ነው? ኦነግ ራስ በራስ የመተዳደር (Self Determination and Self Rule) ጥያቄ እንጂ የመገንጠል (Secessionist) ዓላማ አለው ብዬ አላምንም። የመገንጠል ዓላማ እንኳ ቢኖረው ለመገንጠል የፈለገበትን ምክንያት ጠይቆ መፍትሔ መፈለግ እንጂ ማጥላላት ምናመጣው!? እገነጠላለሁ ከሚል በላይ ተገንጣይን የሚያጥላላ ወገን የባሰ ገንጣይ የለም።

  አሁንም ኦነግ የመገንጠል ዓላማ አለው ብዬ አላምንም። ቢኖረውም ለኦነግ ያለኝ ክብር አይቀንሰውም። ኦነግ ባሁኑ ሰዓት ጠንካራ ድርጅታዊ መዋቅር ላይኖረው ይችላል። ኦነጋዊ አስተሳሰብ ግን በኦሮሞ ህዝብ ልብ ውስጥ አለ።

  ኦነግ የስልጣን ጥማቱ ለማርካት ሲል ከህወሓት ኢህአዴግ ጋር አልተሞዳመደም። ብአዴንና ኦህዴድ ለስልጣን ሲሉ የህዝባቸውን ጥቅም አሳልፈው በመስጠት የህወሓት ቅጥረኛ አሻንጉሊቶች ሆነው ከህዝብ ይልቅ ግዝያዊ ስልጣን መርጠው ጌቶቻቸውን ለማገልገል ህዝባቸውን ሲበድሉ ነበር።

  ኦነግ ግን ህዝቡን መርጦ ከህወሓት ጋር ተጣልቶ ጫካ ገባ፤ ለህዝብ ቆመ እንጂ ለስልጣን አልተሸጠም። ክብር ይገባዋል። ከስልጣን በላይ ህዝብን የሚያስቀድም ድርጅት ያልተመሰገነ ማን ሊመሰገን!? አሻንጉሊት? አሻንጉሊት ክብር የለውም! ልብ በሉ የኦነግ አባላት ለ27 ዓመት ያህል በህወሓት ኢህአዴግ ሲሰቃዩ የኦህዴድ ባለስልጣናት የጨቋኑ ስርዓት ቁልፍ መሳርያ ነበሩ።

  የኦነግ ጥያቄ የኦሮሞ ህዝብ በኢትዮጵያ ፖለቲካ የሚገባውን ሚና መጫወት አለበት ነው። ይህም ትክክል ነው። መደነቅ ያለበትን እናድንቅ።

 2. ፋሺሽት-ወያኔ ሕውሃትን ራቁቱን ማስቀረቱ በቀላሉ ሊገባን የማይችል ነው።
  XXXXXXXXXXXXXXXX
  አጭበርባሪው የገዳይ ኩባንያው ፋሺሽት-ወያኔ ሕውሃት ትጥቁን በአስቸኳይ ካልፈታ፤ኦነግ ትክክለኛ እርምጃ ነው የወሰደው፤ሕውሃት ትጥቁን በአስቸኳይ በራሱም ሆነ በአባላቱ ይሁን በካድሬዎች እጅ ላይ ያለውን መሣሪያ ወይም ትጥቅ በአስቸኳይ መፍታት እለበት።ያለበለዚያ ኦነግን ብቻ ትጥቅ ፍታ ማለት ትርጉሙ ሌላ ነው፤ለምን ጉጅሌ ትጥቁን አይፈታም????????????????????????????????????????ማነው ምክንያቱን የሚያውቅ እና የሚያስረዳኝ??????????????????????????????????????????????ዋናው ዕብድ ጉጅሌ ተደብቆ፤ለምንድነው ኦነግ ላይ ሰዎች የሚረባረቡት ????????????????????????????????????????አጋንንቱ የገዳይ ኩባንያው ፋሺሽት-ወያኔ ታጥቆ ለምንድነው ለሰላም ወደ አገር ቤት የገባውን ኦነግ ለይተው የሚረባረቡበት????????????????????????????????
  አጭበርባሪው ይውጣ።

  ኣሁንም በኦነግ ስም ፋኅሺሽቷ ወያኔ፤
  ያልተነቃ መስሏት ጀመረች እእንደያኔ።
  ግንሳ ያላወቀችው አንዴ አምኖ የተካደ፤
  ጅል ሆኖ አይደግምም አውቆ ካላበደ።
  እናም ጉጅሌ አብዷል ሰዎች ተጠበቁ፤
  እጁ የጨበጠውን አይቀርም ማነቁ።
  እንደው ለጫወታ የኦነግን ላንሳ፤
  ጉጅሌ እየጮኸች ፣ነገር ልታስረሳ፤
  ሲመሽ አይዞህ ብላው፤
  ቀን ቀን ስትጠላው።
  ማታ እንደልማዷ፤
  ቀን ቀን ከነኣመዷ።
  ራሷን ስትቀይር በእሽትነቷ፤
  ከኣጋንንት ታድራለች እንዲቀር መሞቷ።
  አትመኑኝ እዪዋት ትንፈራገጣለች፤
  እንዳበደ ውሻ ሁሉን ትነክሳለች።
  እናም በኦነግ ሥም ተንኮል ሥትሰራ፤
  ወገኔ አትቀበል መርምረህ አጣራ።

  የአማርኛ ቋንቋችን በምርምር የተቀመመ እንደሆነ ለሚያውቁት በሙሉ ማስረዳት አይጠበቅብኝም፤ይበልጥ ተቀምሞ ኢትዮጵያዊነቱ በዓለም እንዳይነገር የሚፈልጉት የጣሊያን ምርኮኞች ፋሺሽት-ወያኔዎች ግን ሌት ተቀን

  ኢትዮጵያን ሊያጠፏት ከሮማውያን(ጣሊያን)በተቀበሉት መሃላ ልጆቿን የሥጋ ትል ሆነው በልተውባታልና እንደ እኔ ዓይነቱ ኢትዮጵያን የሚል ሁሉ ሊያስከብራት ይገባል።ለዚህም ነው በፋሺሽት ውድቀት ማግሥት የተፈጠረችውን ፋሺሽት-ወያኔን የሥጋ ትል መሆኗን አበክረን የምንገልፀው።የዚህም አገላለፄ መነሻ የሚሆነኝ የቃላት አጠቃቀሜ ነው፤ዛሬ በመሳሌ የማቀርበው፤”አቀፈ እና አዘለ ሁለቱም ተሸከመ ነው”እንደሚሉት በቀልድ የማልፈው አይደለም፣በመሠረቱ ሁለቱም ይለያያሉ፤ውጤታቸው አንድ ቢሆንም።አሁን የምገልፃፍቸው ቃላት በሕልውናችን ላይ የተመሰረቱ በመሆናቸው ነው፤ይኸውም እኛን ሊያጠፋ ዘመናት ያስቆጠረ የኢትዮጵያ ሕዝቦች ጠላት ደዌ ሆኖ ከውስጣችን ስለወጣ አፍርጠን፣አምግለንና አድምተን እንድናወጣው ነው።
  የፋሺሽት-ወያኔ ባሕርይ እንደ እሥስት ሲቀያየር ምን ዓይነት ስያሜ ልንሰጠው ይገባናል?በዚያም ስያሜ ማንነቱን በትክክል እናረጋግጣለን።
  አጭበርባሪ፣ሸንጋይ፣አቄለ፣ቀጣፊ፣(ሮሜ ም፩ ቁ ፴፣፴፩)አታላይ የሚለው ይቆይና፣መሰሪ፣ተንኮለኛ፣እባብ፣እያልን ምርጫዎችን በድርጊት ውስጥ በማብዛት ልንፈልግ እንችላለን፤”መሠሪ” ግን በእኔ አመለካከት ተስማሚው ነው እላለሁ።የሚሄድበት መንገድ የማይታወቅ የሚመስለው፤ዳሩ ግን እግዚአብሔር በአንድም ሆነ በሌላ መንገድ እየተናገረ ኢትዮጵያን እንደሚጠብቅ እያወቀ “በሠይጣን ስላመነ”ያላወቀ ከሃዲ የሆነ ምስለ-ደብተራ እባብ ነው።
  በትንሹ በምሳሌ ላስደግፈው ሰኔ ፲፮ ፈንጂ ብቻ አይደለም አመፅ አደራጅቶ አዲስ አበባን በደም አበላ ሊያረክሳት ዶለተልን፤ቅድስት ማርያም በዕለተ-ቀኗ አወጣችን፤መቁሰል ያለ ነው፣ትንሽ የማይባሉ ሰዎች ተሰዉ፣የመጣውን ግን አላየነውም፤እርሱ አያሳየን።አብዲ ኢሌ የሚባል የሰይጣን እስረኛ ላከብን በምስራቅ ካህናትን ጨምሮ ሰዎች አሳረደብን፣በመድሃኒዓለም ብርታት ተጋልጦ

  ይኼው በድብቅ የተገደሉት ሬሳዎች እየተሰበሰቡ ነው።
  ኦነግ ለሰላም ብሎ ወደ አዲስ አበባ ሲገባ በወጣት ልጆቹ “ቄሮ”ሥም የተባረሩ ኦሂዲድን በማሰማራት ብዙ ሰዎችን ገድለው አሳረዱብን።
  አሁን ደግሞ ሕውሃት ራሱ መሳሪያ ሳይፈታ ፈትቶ ወደሕብረተሰቡ የተቀላቀለውን ኦነግን ለመኮነን ለማስጠላት በመሯሯጥ ላይ ነው፤የኦነግ አባባል “እኔ አመራሬን ይዤ ወደከተማ የገባሁት ሁሉንም ነገር በሠላም ለመጨረስ ስለሆነ ከኢትዮጵያ ሰራዊት ውስጥ ያሉት የሕውሃት ታጣቂዎች በሙሉ መውጣት አለባቸው ነው።ይህንን መሰሪ የሆነ ሃቅ የምናውቀው በጣም ጥቂት ሰዎች ነን።አሁን ግን ኦነግ ካለፉት ስህተቶቹ ተምሮ ለሠላም ውይይቱ መምጣቱና ጉጅሌን ራቁቱን ማስቀረቱ በቀላሉ ሊገባን የማይችል ነው።በዚያም አለ በዚህ ኦቦ ዳዊት ኢብሳ፤ፋሺሽት-ወያኔን አሳዩት አበሳ፤የገባችሁ ቀጥብላችሁ አምርሩ፤መታገሉን ጀምሩ።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here