Home News and Views በዘሩ ምክንያት ጥቃት የደረሰበት ፓይለት ነጻነትን ፍለጋ በግብርና ሙያ ለመሰማራት ተገዷል። (ሊያዩት...

በዘሩ ምክንያት ጥቃት የደረሰበት ፓይለት ነጻነትን ፍለጋ በግብርና ሙያ ለመሰማራት ተገዷል። (ሊያዩት የሚገባ)

1 COMMENT

  1. የዚህን ወጣት አብራሪ ታርክ ስሰማ በጣም አዘንኩ።ተምሮ መና ይላሉ ሲተርቱ ተምሮ እውቀትና ስራ አግኝቶ ያለ እድሜው ሲሞት ።ይሄንን አይነት አሟሟት ደግሞ ምን ማለት እንደሚቻል አላውቅም ።ነገር ግን ምስጋና ይግባቸው ይሄንን ቀን ለማምጣት ተሰደው ታስረው ሞተው ታላቅ መስዋእትነት ከፍለው ለዚህ ጊዜ ላደረሱን ።በርግጥ አሁንም አልጋ በአልጋ ነው ማለት አይደለም ቢያንስ እንደዚህ ተደብቀው ያሉ ታሪኮች ተፈልፍለው እየወጡ ነው።የአንድ ብሄር የበላይነት ያመጣው ጣጣ። እኔ እርሱ ብቻ መስሎኝ ነበር አሁን ቀስ በቀስ በኢትዮጵያ አየር መንገድ ውስጥ በተለያየ ጊዜ ከስራ የተባረሩ ከሀገር የተሰደዱ ለእስራት እና ለሞት የተዳረጉ ጥቂት የማይባሉ ባለሞያዎች ቀስ በቀስ ታሪካቸውን እየነገሩን ነው።ላለፉት ሀያ ሰባት አመት በፖለቲካው ስልጣን በኢኮኖሚው በወታደሩ ክፍል በተለያዩ የመንግስት መስሪያ ቤቶች በአንድ ብሄር የበላይነት የተያዙ ቦታዎች በህዝባችን ላይ ተዘርዝሮ የማያልቅ ሰቆቃና ግፍ ፈጽመዋል።ጊዜና ትውልድ ይፍረደው ማለት ብቻ ነው።
    ይህንን ለማለት ያስቃጣኝ በመጠኑም ቢሆን በተለያዩ ጊዜ ከላይ በጠቀስኩዋቸው ቦታዎች ላይ የትግሬ የበላይነት እየቀነሰ የመጣ ነው ቢባልም ግን አሁንም በዚህ እና በስራ ጓዋደኞቹ ላይ ከፍተኛ ግፍ እና መከራን የፈጸሙት ግለሰቦች አሁንም በመንግስት ተገቢውን ክብር እና ስልጣን አግኝተው መቀመጣቸው ነው።ለእኔ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ትልቅ በር ነው።ከማናቸውም የሀገሪቱ የመግቢያ መንገዶች እውቀትን ስልጣኔን የተሸከሙ በርክታ ምሁራኖች መግቢያ መውጫ ቦታ ነው ።አየር መንገዳችንም በሀገራችን ካሉት የተለያዩ መስሪያ ቤቶች በአደረጃጀቱ በዘመናዊነቱን በተማሩ የሰው ሀይልንም ካቀፉ ዋነኛው ነው ።ስለሆነም አሰራሩንም ሆነ ሁሉ ነገሩን ዘመናዊ አድርጎ ለሀገራችን ታላቅ ስም እና ዝና ይዞ ያለ ስመጥር ድርጅት ነው።እንደምንሰማውም ትርፍ እንጂ ኪሳራ የሌለው ታላቅ የሀገራችን ሀብት ነው።በዚህም ድርጅት ውስጥ በትምህርትም በእድሜም ከሰራተኛውጋር ያለውን ችግር በመፍታት በኩል የሰራተኛውን መብት እና ጥቅማጥቅሞች በማስጠበቅ በኩልም በአለም አቀፍ ደረጃ ካያቸው ከሰማቸው ከተማራቸው በልምድም ከቀሰመው በመነሳት ተገቢ መፍትሄን በመስጠት የሰራተኛውን ህይወት በተረጋጋ እንዲቀጥል የስራ ዋስትናውም አስተማማኝ የሚያደርግ መሆን ነበረበት
    በዚህ ሀያሰባት አመት ያለመታደል ሆኖ ወያኔ በተከተለው የጎሳ ፖለቲካእንደዚህ አይነት ነገሮችን መስማት የተለመደ ሆኗል ይሄ አየር መንገድ ከላይ እስከታች በአንድ ብሄር የተሞላ ነው ተብሎ ውግዘት ብዙ ጊዜ ቀርቦበታል። በተለይ አሁን በስልጣን ላይ ያለው የአየር መንገዱ ስራ አስኪያጅ ነገሮች ፈር እየለቀቁ ስራዎች እየተበላሹ እንዲያውም የሀገሪቱ ዜጋ ተምሮ መቀጠር ሲገባው ለቻይናዎች የስራ እድል በመስጠት ኢትዮጵያውያኑን ሁለተኛ ዜጋ ያደረገ አመራር ነው።የዚህ የብልሹ አሰራር ቀንደኛ ተዋናይ ግን በነ ዶክተር አቢይ ለማ ቲም ምንም አይነት እርምጃ ሳይወሰድበት በስልጣን ወነበሩ ላይ ነው ያለው።ለመሆኑ እንደዚህ በአይን የሚታይ ግዙፍ ወንጀል የሰራን ግለሰብ መንግስት ለምን ከበደው።ስለዲሞክራሲ ስለፍትህ ስለመደመር ስለፍቅር እየተወራ እርሱን ተግባራዊ ለማድረግ እየጣርን ነው እየተባለ ከዘመኑ ከጊዜው አሁን ካለው አስተሳሰብ ጋር የማይሄዱ አመራሮችን አቅፎ መቀጠል ትርጉሙ አልገባን አለ።እየተዋሸን ነው መሰለኝ ።ለሀገሩ ሌት ተቀን ሲሰራ የነበርው ኢንጂነር ስመኘው ተገደለ ።መንግስት ራሱን አጠፋ አለን ።የነአቢይ ለማ ቲም በመደገፍ ታላቅ ሰላማዊ ሰል የወጣው የአዲስ አበባ ህዝብ ፍቅሩን አጋርነቱን በመግለጹ ማዘጋጃ ባለቤት አልባ እያለ እንደሚገላቸው ውሾች በከተማዋ ያሉ ወጣቶች በግፍ ታሰሩ ተገደሉ።ለመፍታትም ሆነ በሰኔ አስራስድስቱ ለተገደሉት አፍቃሪ አብይ እና ለማ ቡድን ማቾች መፍትሄ ጠፋ።ታዲያ ምኑ ነው ዲሞክራሲ እኮ ጉልበተኛው አቅም የሌለውን እንዳይውጠው በህዝብ ድምጽ አሸንፎ ስልጣን ሲይዝ የሁሉንም መብት በእኩለነት ለማስጠበቅ የሚያስችል የህዝብ አገዛዝ ስር አት ነው።ወደእዛ እየተንደረደርን ከሆነ ለዚህ ስርአት እንቅፋት የነበሩትን አሁንም የሆኑትን በማስወገድ ጥርጊያ መንገድ መክፈት ማለት ነው ይመስለኛል።በመሆኑም የዶክተር አቢይ መንግስት በነዚህ በተለይ በተወልደ ላይ ተገቢውን እርምጃ ወስዶ ግለሰቡ በህግ እንዲጠየቅ ማድረግ አለበት ።ያለአግባብ በእስር ቤት ውስጥ በእስር በመማቀቅ ላይ ያሉትን የአዲስ አበባ ወጣቶችን ፈትቶ ለዲሞክራሲያዊ ስርአት ተገዢነቱን ማሳየት አለበት ።ያለበለበዚያ የተንኮል ፖለቲካ ወይም የሸፍጥ ፖለቲካ የትም አያደርስም ለጊዜው እንደ ወያኔ ባለስልጣስናት በሀብትም በስልጣንም ተጠቃሚ ሊያደርግ ይችላል። በተመሳሳይ የሀገራችንን ህዝብ ታላቅ መስዋእትነት እንደ አለፉት ሀያሰባት አመት ያስከፍለዋል ግን ህዝብ ያሸንፋል ።ህዝባችን የአንድነትን አብሮ የመኖርን ጥቅም የፖለቲከኞቻችን ሴራ እና ተንኮልን በሚገባ ተርድቶአል።ስለዚህ ከመሸነፍ ይልቅ የሚከፈለውን መስዋእትነት ከፍሎ ሀገሩን አንድነቱን ሰላሙን ያስጠብቃል ።ለዚህም ምስክሩ በዚህ ዘመን ላይ ያለው ወጣት ትውልድ ሊፈጥረው የነበረው ተንኮል ሊያጠጣው የነበረ መርዝ ከሽፎአል ።ዶክተር ከነእርሱ ወጥታችሁ የተናገራችሁት በከፊል ያደረጋችሁት ተግባር የሚያስመሰግን ቢሆንም ግን አንዳንዴ የመለስን አይነት የሴራ ፖለቲካ ህዝብን እያለሳለሳችሁ ለመቀጠል የምታስቡም ትመስላላችሁ ግን ህዝብ ያሸንፋል።ይሄን ያልኩብት ምክንያት በአንዳንድ ቦታዎች የሚሰጠው ሹመት ልክ እንደስድሳስድስቱ ፖለቲካ ጉልቻ ቢቀያየር ውጥ አያጣፍጥም የሚያስብሉ ተመሳሳይ አንድን ብሄር በሁሉ ቦታ የመሾም እና የማስቀመጥ በተለይ በአዲስ አበባ ደግሞ ላይ ችግር ጎላ ብሎ እየታየ በመምጣቱ ለዚህ ተገቢ ማብራሪያም ሆነ መፍትሄ ለመስጠት ያለመፈለግ ዝንባሌ እየታይ እና ነዋሪውን ድህንነት ለማስጠበቅ ዳተኝነት በማሳየት የተወሰኑ ብሄሮችን በማጥቃት ዘግናኝ ወንጀል ሲፈጸም ፈጥኖ ባለመድረስ የታየ እውነት አለ።
    በመጨረሻ ግን ስለኢትዮጵያ አየር መንገድ እና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ላይ ችግር አለ።ሁን ጊዜው የሚፈታበት ወቅት ነው።በርግጥ ቤተክርስቲያንዋ የእምነት ተቋም ናት ።በሷውስጥ ለመኖር መንፈሳዊ እውቀት እና ጸጋ ወሳኝ ናቸው።ነገር ግን አየር መንገድ መስፈርት ሊሆን የሚችለው መሆንም ያለበት ሞያዊ ብቃት እና ለስራው ያለው እውቀት ነው ።እንጂ የቁንጅና ውድድር አይደለም።አየር መንገዱ የኢትዮጵያን ስም እስከያዘ ሁሉንም የሀገሪቱ ህዝቦችን መወከል አለበት።የአንድ ብሄር ብቻ መሆን የለበትም በጋራ ለሀገር እስከወደቅን ድረስ ምቾት ባላቸው የመንግስት ስራ እና ሀላፊነት ቦታዎች ተወዳድሮ ቦታውን መያዝ ወይም መቀጠር ለሁሉም እኩል መብት መሆን አለበት።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here