Home News and Views ሰራዊቱ ጥያቄ እና የም.ጠ.ሚ/ር ደመቀ ውሎ “ማን ይናገር የነበረ? ~ ማን...

ሰራዊቱ ጥያቄ እና የም.ጠ.ሚ/ር ደመቀ ውሎ “ማን ይናገር የነበረ? ~ ማን ያርዳ የቀበረ?”

 

ጠዋት 4:45
~~~~~~
ከወትሮው ባልተለመደ መልኩ የመከላከያ ሰራዊት የተውጣጡ ቀይ ቦኔት የለበሱ አባላት አራት ኪሎ በአራቱም አቅጣጫ ላይ መታየት ጀመሩ። በአጋጣሚ ወደ ገብርኤል የሚወስደው መንገድ በጠቅላይ ሚኒስቴር ፅ/ቤት ግንባታ ጋር በተያያዘ ለተሽከርካሪ ዝግ ተደርጎ ቆይቷል።

ቀትር 6:30
~~~~~~
በተለያየ አቅጣጫ ወደ ጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት የሚመጡት ልዩ ሃይሎች ቁጥራቸው እየበዛ መጣ።

ከቀኑ 7:30
~~~~~~
ለጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ ሊቀርቡ የሚገባቸው ጥያቄዎች እንዳላቸው ከሰራዊቱ የተውጣጡ አባላት ለፅ/ቤቱ አቅርበዋል።

ከቀኑ 7:45
~~~~~~
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን በሚሊኒየም አዳራሽ የኮንስትራክሽን ኤግዚቢሽን በይፋ ከፍተው ከቦሌ ወደ አራት ኪሎ ፅ/ቤታቸው አቀኑ።

ከቀኑ 7:55
~~~~~~
ከተለያየ አቅጣጫ ጥያቄያቸውን በሰላማዊ መንገድ ለማቅረብ የመጡ የሰራዊቱ አባላት ቁጥር መጨመሩን ተከትሎ፤ አራት ኪሎ አካፋይ መንገድ ላይ ወደ ቤተመንግስት የሚወስዱ መኪናዎች አቅጣጫ እየቀየሩ አከባቢው ተጨናንቆ ነበር።

ከቀኑ 8:00
~~~~~~
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀን የያዘው መኪና {ጥይት የማይበሳው} ወደ አራት ኪሎ አካፋይ መስቀለኛ መንገዱ ጋር ደረሰ። የአቶ ደመቀ ልዩ ጠባቂዎች በፍጥነት ከመኪናው ወርደው አጅበው ለማሳለፍ ሞከሩ።

ከቀኑ 8:05
~~~~~~
የምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ዋና ጠባቂ {Cheif Secirty} ወደ መኪና ተመልሶ ሰራዊቱ ጥያቄ ለዶ/ር ዓብይ ማቅረብ እንደፈለጉ ለአቶ ደመቀ ነገራቸው።

ከቀኑ 8:07
~~~~~~
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ የመኪናቸውን መስተዋት ዝቅ አድርገው ከተወከሉ የሃይል አመራሮች ጋር “ከናንተ በላይ ጥያቄው ሊደመጥ የሚገባ ማንም አይኖርም። ዶ/ር አብይ እስኪመጣ ከኔ ጋር መወያየት እንችላለን።” ብለው ካዘዙ በኋላ ሰራዊቱ በፍፁም ህዝባዊ ወገንተኝነት ስሜት ወደ ግቢ ተሰባስቦ ።

ከቀኑ 8:45
~~~~~~
የሃይል መሪዎቹም የሰራዊት አባላቱን ሰላማዊ ውይይት ለማድረግ የታጠቁትን መሳሪያ አስፈትተው፤ በሰለጠነ ወታደራዊ ዲሲፕሊን ውይይቱ ተጀመረ።

ከቀኑ 9:00
~~~~~~
በውይይቱ መነሻ ላይ የሰራዊቱ አባላት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ ያለማንገራገር ወደ ፅ/ቤት የመሄድ ሃሳባቸውን ሰርዘው ሰራዊቱን ለማነጋገር መወሰናቸው አድናቆታቸውን እና አክብሮታቸውን ገለፁ።

ከቀኑ 9:00 ~ 10:30
~~~~~~~~~~
ሰራዊቱ አባላት ከደሞዝ፥ ከኑሮ ውድነት፥ ከመልካም አስተዳደር፥ ከግዳጅ ተልዕኮ ጋር የተያያዙ የግብዓት ጥያቄዎችን ዲሞክራሲያዊ ባህል በሰፈነበት ድባብ አንስተዋል።

ከቀኑ 10:30 ~ 10:45
~~~~~~~~~~~~

~> ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ለሰራዊቱ አባላት ምላሽ መስጠት ጀመሩ።

~>መከላከያ ሃይላችን እንደዜጋ መደመጥ ይኖርበታል፤ በተግባርም ምላሽ ሊሰጠው ይገባል~ ብለዋል።

~>መንግስት እንደሃገር የጀመረው የሪፎርም ስራ በመከላከያ ዘርፉም በተመሳሳይ ተጠናክሮ ይቀጥላል ~ ብለዋል።

~>ተጨማሪ ውይይት በሚፈልጉ ጉዳዮች ዙሪያ መድረኮች እንደሚመቻች ~ ተናግረዋል።

ከቀኑ 10:45
~~~~~~
የም.ጠ.ሚ/ሩ ዋና ጠባቂ አስቸኳይ የስልክ ጥሪ እንደተደወለላቸው ለአቶ ደመቀ ቀረብ ብሎ ነገራቸው።

ከቀኑ 10:46
~~~~~~~~
አቶ ደመቀም የሰራዊት አባላቱን ይቅርታ ጠይቀው {የጀመሩበትን የንግግር ምት ሳይቀይሩ} . . . . ስልኩን ማናገር ጀመሩ።

ከቀኑ 10:47
~~~~~~~
አቶ ደመቀም ወደ ሰራዊት አባላቱ ድምፃቸውን ከፍ አድርገው . . . .

“የደወለው ሰው ዶ/ር ዓብይ ነው። ስብሰባ አጠናቋል አሁን ጉባኤ አዳራሽ ለማናገር እየጠበቃችሁ ነው። . . ” እንዳሉ ሰራዊት አባላቱ ንግግራቸውን በጭብጨባ አናጠቧቸው።”

ከቀኑ 10:50
~~~~~
በማጠናቀቂያው ሁለት አባለት ሰራዊቱን በመወከል በውይይቱ ለተነሱ የዘርፉ ችግሮች በሰከነ አግባብ እንደሚፈታ ያላቸውን ዕምነት በመግለፅ፤ እና የተጀመረው የለውጥ ጉዞ እንዳይደናቀፍ ታሪካዊ ሃላፊነታቸውን ለመወጣት ዝግጁነታቸውን አረጋግጠዋል።
~~~~~

ከቀኑ 10:55
~~~~~~

የሰራዊት አባላቱ ለምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ጠንካራ አመራር እና መልካም ሰብዕና ያላቸውን ፍቅር ለመግለፅ . . . የህብረት ፎቶ ለመነሳት መረባረብ ጀመሩ።

የቀረውን ከፎቶ ታሪኩ ዕውነቱን ይመልከቱ።

~~~~
“ማን ይናገር የነበረ? ~ ማን ያርዳ የቀበረ?”
30/01/11

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here