Home News and Views ምነው በዕንደመር ላይ ፀሐፊዮች በዙ! እኔም አለሁበት!

ምነው በዕንደመር ላይ ፀሐፊዮች በዙ! እኔም አለሁበት![ ታጠቅ መንጂ]

‘የዕንደመር’ ቃል፦ዘቤያዊ፣አርማዊ፣ ምልክታዊ፣ተምሳሌታዊ  ወዘተርፈ  ነው ። በእንግሊዝኛ <ሜታፎር ወይም ሜታፍሪካል> የሚል ትርጉም ያለው ይመስለኛል ።

የዕንደመር ቃል -ማኅበራዊ አብሮነት <ሶሻል ኢንክሉዥን> ከተሰኘ ከማኅበራዊ ሳይንስ  ጽንሰ-ሃሳብ የተወሰድ  ወይም ጋር የተዛመደ ሊሆን ይችላል ።

እንደ የቅድመ ኅድሳትና የዘመነ ኅድሳት ጥናት ሊሂቃን -በእነዚያ ዘመናት  የፖለቲከኞችን ንግግር፣የአደባባይ ስዎች ዲስኩር ፣የፀሃፊዮችን ጽሁፎች፣ የሳዓሊዮችን፣ የተዋኒያን (የኪነጥበብ)ሰዎችን  ወዘ…ሥራዎች በቅጡ ሳይተቹና ሳይፈተሹ በሕዝብ አእምሮ ይጸረጹ ነበር ፤ የሚተቹና አቃቂር የሚያወጡ ቢኖሩም በጣም ጥቂቶች ነበሩ ።

ጠ/ምኒስተር አብይ  ይህ አምስት ሆሄያት የያዘ ቃል በአደባባይ ንግግራቸው ጣልቃ አስገብተው ለኢትዮጵያ ሕዝብ ካስደመጡት በግምት ከአምስ እስከ ስድስት ወራት ይሆናል።ያንን ንግግር ካደረጉበት ሰዓት ጀምሮ የበርካታ የሃሳቡን ደጋፊና ተቃዋሚ ፀሃፊዮች ቀልብ ሳበ፤የመጻፊያ መድረክ ፈጠረ።           በኢንዱስትሪ፣በቴክኖሎጂ፣በኮምኒኬሽን፣ በኢኮኖሚ ወዘተርፈ እድገት ላቅ ባሉ አገሮች ሕዝቦች አሰያየም ፤አሁን ያለንበት ዘመን ድኅረ-ህድሳት (post modern) ይባላል።ለምን ድኅረ ህድሳት እንደተባለ የማያቁ ካሉ ወደፊት  ራሱን በቻለ ጽሁፍ እገልጸዋለሁ።

የድኅረ-ህድሳት ጥናት ሊሂቃን -የሉል/ግሎባል ማኅበረሰብ ንቃተ-ኅሊና ስላደገ  በዚኅ ዘመን በያንዳንዱ ፦በጥንድ፣ በቡድን እና በአደባባይ በሚነሱ (ነጥቦች ፣በሚወረወሩ ቃል/ቃላት፣በሚደረጉ ንግግሮች/ ዲስኩሮች ፣በሚጻፉ ጽሁፎች፣በሚሳሉ ሥዕሎች፣በሚተወኑ ትወናዎች፣በሚለበሱ ፋሽኖች)  ወዘተርፈ ላይ (የመተቸት ፣የመገምገም ፣የመሰንጠቅ ፣የመጠንጠን ፣የመቀጥቀጥ፣የመፈጥፈጥ) ወዘተርፈ ፈተናዎች አሉባቸው ይላሉ ። ለምን ?ስለምን?በምን ምክንያት?እንዴት ? መቼ? ከየት? ወዘተርፈ ብሎ የሚጠይቅ ማኅበረሰብ ተፈጥሮዋል ይላሉ ።

ስለሆነም ነው ‘በዕንደመር’ ላይ የዕንደመርን ቃል ካዋቀሩት ሆሄያት የበዙ ሰንጥቅጥቅ ታይታዎችን የተፈጠሩት ። ጠ/ሚኒስተር  አብይ ‘ዕንደመርን’ የወረወሩት  ይህንን ሳይረዱ ይሆን?

ዕንደመር፦

 1. ከመሰረታዊ የሂሳብ ሚናው ወጣ ብሎ የኢትዮጵያውያን የሰላምታ መግበያ ቋንቋ ይሆናል
 2. የኢትዮጵያውያን ፖለቲካዊ ፦ ቧልት፣ምፀት፣ቀልድ፣ትወና <political satire> ይሆናል/ይፈጥራል                             3.(ግራ፣ቀኝ ፣ማሃል ግራ፣ማሃል ቀኝ) ዘመም ፀሃፊዮች-ያከራክራል ፣  ያፋትጋል፣ ያፋጫል፣ የሃሳብ፣የብዕርና የወረቀት አቧራ ያስነሳል…

4.ኢትዮጵያውያን የዕንደመርን ፦ባህላዊ፣ ታርካዊ ፣ቋንቋዊ ፣ብሄረሰባዊ …ፋይዳ ምንድነው? በማለት በየ-የኢትዮጵያ ኤምባሲዮች ተሰባስብው የሚያከራር አጀንዳ ወዘተርፈ ይሆናል ብሎ በማሰብና በማስላት ይሆን ‘ዕንደመርን’ የወረወሩት? ወይስ በግብታዊነት?

የማሃል ግራዎችና የማሃል ቀኝ ዘመሞችን የክርክር ቅኝት ለግዜው ትቼ  የግራና የቀኝ ዘመም አስተሳሰብ ካላቸው ተክራካሪዮች የሚሉትን ከሁለቱም አንዳንድ ለናሙና እነሆ፤

ሀ) የቀኝ ዘመሞች ክርክር ፦ ዕንደመር ፍቅር ነው ፣ዕንደመር ብዚህ ነው፣ ዕንደመር አብሮነት ነው፣ ዕንደመር የተፈጥሮ ህግ ነው <መዋለድ> ነው ፣ ስለሆነም ያለገደብ ያለአጥር ፣ያለጥያቄ ፣ያለቅድመ ሁኔታ መደመር ያስፈልጋል ይላሉ

ለ) የግራ ዘመሞች ክርክር (ሃቅ ፈላጊዮች)፦ለመደመር ቅድመ-ሁኔታዎች መኖር አልባቸው  ፣ መደመር በገደብ ፣ እንዴት ቂጥኝ ፣ኤድስ፣ የሳምባ ፣የአባለዘር ወዘተርፈ በሽተኞች ታክመው ሳይፈወሱ  ከሰፊው ሕዝብ ጋር ይቀላቀላሉ ይላሉ ። በሌላ አነጋገር ወንጀለኞች፣ ፀረ-ሕዝቦች፣ፀረ-አገረኞች ግፈኞች፣ ዘራፊዮች ወዘተርፈ  ለፈፀሙት ጥፋት ተጠያቂ መሆን አለባቸው! ለሕግ ይቅረቡ!  ፍትህ ይሰጥ!  ፍትህ አልባ ይቅርታ ቀልድ ነው! ስለሆነም ዕንደመር በገድብ መሆን አለበት ይላሉ ።

 የዕንደመር፣ተደመሩ ትርጉም በእኔ ታይታ

የዕንደመር ፣ተደመሩ መልዕክት ኢትዮጵያውያን የተሳሳተ ትርጉም ሰጥተው ሲጠቀሙበት እሰማለሁ ።ጥሪው ለኢትዮጵያ አውደ ሕብና ከአውደ ሕዝባቸው ጎን ተሰልፈው -ለታገሉትና መሰዋዕትነት ለከፈሉት አይደለም ።እውነተኛ ጥሩው እንደሚከተለው ነው።

[1]

ከወያኔ/ህወሃት ጋር ተሰልፈን፦አገር ያስገነጠልን፣የባህር በርዎች ያስወሰድን፣በጎሳ ቋንቋ ሕዝብ ያካለልን/ያጠርን፣አንድ ጎሳ በሌላ ጎሳ ላይ ያዘመትን፣ የኢትዮጵያ ታርክ የመቶ ዓመት ታርክ ነው ብለን ያስተማርን ፣የገረፍን/ያስገርፍን፣የጠቆምን/ያስጠቆምን፣የገደልን/ያስገደልን፣የዘረፍን/ያዘረፍን፦                                                                                 በባዕዳን አገራት ቤተክርስቲያናት፣መስጊዶች ፣ምዕምናን፣ ኮምኒቲዮች ፣የስፖርት ተቋማት ወዘተርፈ በመከፋፈል የወያኔ ተልዕኮ ያስፈጸምን  በሰፊዩ  የኢትዮጵያ ሕዝብ ተሸንፈናልና ኑ ወደ አወደ ሕዝቡ ዕንደመር ማለታቸው ነው ፤ማለት  ጠ/ምኒስተር አቢንም ጨምሮ ።

[2]

ተደመሩ፦ ከደርግ ጋር ተሰልፋችሁ -የአንድ ሕዝብ ወጣት ትውልድ  የመተራችሁ፣አገር ምሁር አልባ ያደረጋችሁ፣ወላጅ ልጅ አልባ ያደረጋችሁ፣ገድላችሁ እሬሳ የሽጣችሁ ፣በብዙ ሺዎች ላይ ሰቆቃ የፈፀማችሁ፣ ብዙ ሺዎች ዘር አልባ ያደረጋችሁ፣የብዙ ሺዎች አካለ ያጎደላችሁ፣ ብዙ ሺዎች በረንዳ አዳሪ ያደረጋችሁ፣ ብሁ ሺዎች የአእምሮ በሽተኛ ያደረጋችሁ፤

ሸማግሌዎች ፣አሮጊቶች፣አዛውንቶችና አረጋውያን ያሰቃያችሁ ፣የገረፋችሁ ፣ያዋረዳችሁ፣ የገደላችሁ፣ የማኅበረሰቡን ሕይወት ያመሰቃቀላችሁ ፣የማኅበረሰቡን ቅስምና ስነ-ልቦና ያዘቀጣችሁ፣ያኮታኮችሁ ፤

ምርጥ ወታደራዊ መኮንኖችን በመመንጠርና  በመጨፍጨፍ ኢትዮጵያ ኤርትራን ፣አሰብና ምጽዋን እንድታጣ አስተዋጾ ያደረጋችሁ ወዘተርፈ  ፀር-ሕዝብና ፀረ-አገር ደርጎችና የደርግ ካድሬዎች ኑ ወደ ሰፊው ሕዝብ ተደመሩ። ሕዝብ ሃያልና አሸናፊ ስለሆነ ተሸንፈናል ስለሆነም ለሰፊው ለኢትዮጵያ ሕዝብ እንበርከክ ፤ተምበርከኩ ማለታቸው  ነው ።

ያለገደብ ይደመሩ ወይስ በገደብ ? ጥያቄ ላይ የእኔ አቋም

 • በየትኛውም አገር በአእምሮ ጤና የታወኩ የማኅበረሰቡ አባላት-በዜጎች ላይ አድጋ እንዳያደርሱ ከሰፊው ሕዝብ ተነጥሎና እርቀው እንዲቀመጡ  ይደረጋል  ወይም በቤተሰብ ቁጥጥር ሥር ይውላሉ
 • በኢኮኖሚና በሁለ-ገብ ዘመናዊ ሥልጣኔ አደጉ የምንላቸው እንደ አሜሪካና እንግሊዝ የመሳሰሉ አገራት ወይም መንግሥታት ለውጌያ  ወደ ቬትናም፣ ካምቦዲያ፣ ላዎስ፣ ኢራቅ፣ አፍጋኒስታን ወዘተርፈ የላክዋቸው ወታደሮቻቸው ወደ አገራቸው ሲመለሱ በቀጥታ ከአውደ ሲቪሉ ሕዝብ ጋር አይቀላቀሉም ።ምክንያቱም  የጦርነቱ ቴያትር ቁጡ፣ጠበኛ፣ብስጩ፣ አመጸኛ ወዘተርፈ ስለሚያደርጋቸው  በሕዝብ ላይ አደጋ ያደርሳሉ ተብሎ ስለሚታመንና ሃኪማዊ ጭብጥነትም ስላለው። ስለሆነም ከሰፈው ሕዝብ አርቀው ያስቀምጥዋቸውና የአእምሮ ህክምናና ዋግምት/ትራፒ ከሰጥዋቸው በኋላ ከሕዝብ ጋር ተቀላቅለው መኖር ይጀምራሉ።
 • በኢኮኖሚና በሁለ-ገብ ዘመናዊ ሥልጣኔ በተጎናጸፉ ምዕራባዊያን ሃገራት እንዲታደኑ በህግ ከተደነገጉ- የቤት የዱርና የሜዳ እንስሳት ውጭ ህግ ጥሶ/ተላልፎ እንስሳ/ት የገደለም ሆነ ያቆሰለ በእስር ወይም በገንዘብ ይቀጣል ። ከመብዛታቸው የተነሳ በአካባቢ የተፈጥሮ ሃብት ላይ ጥፋት ያስከትላሉ ተብለው የተፈረጁትን እንስሳት ለስፖርት ኤላማ መለማመጃና ለመዘናኛ የሚታደኑ ተብለው ይፈረጃሉ (animals can be hunted for sport and recreation)
 • የዲሞክራሲ እምብርት እንደሆነ በሚነገረለት አሜሪካ አንድ ሰው – ሰው መግደሉን በማስረጃ ከተድርሰበት ፤ሟቹና ገዳዩ እንደሚኖሩበት ክ/ሃ ወይም  እስቴት በሞት ወይም በዕድሜ ይፍታህ እሥር ይቀጣል
 • የአሜሪካ መንግሥት አንድ ሰው ወይም ቡድን በኅብረ-አሜሪካም ሆን በአንዱ የአሚሪካ ግዛት ላይ ክህደት የፈፀመ/ምች መሆኑን/መሆ ኗን በማስረጃ ከተረጋገጠባቸው በግዲያ ይቀጣሉ ።የሚከተለውን የእንግሊዝኛ ትርጉም ተመልከቱ

·          Treason laws in the United States

In the United States, there are both federal and state laws prohibiting treason.[1] It was defined in Article III, Section 3 of the United States Constitution. Most state constitutions include similar definitions of treason, specifically limited to levying war against the state, “adhering to the enemies” of the state, or aiding the enemies of the state, and requiring two witnesses or a confession in open court.[2] However, fewer than thirty people have ever been charged with treason under these laws.[3]

Constitutionally, citizens of the United States owe allegiance to at least two sovereigns. One is the United States, and the other is their state. They can therefore potentially commit treason against either, or against both.[4] At least fourteen people have been charged with treason against various states; at least six were convicted, five of whom were executed.However, no person has ever been executed for treason against the federal government [www.wikipedia,free encyclopedia]

ዝምብልችሁ ተደመሩ ፤እንደመር ማለት፦

 • አገር ማስገንጠል ፣የብሄራዊ ባህር በር ማስነጠቅ ፣ብሄራዊ አንድነት ማናጋት ፣ሕዝባዊ አንድነት መሸርሸር፣ማፈናቀል፣የእርስ በርስ ግጭት መቀስቀስ ፣ በአጠቃላይ በዜጎችና በአገር ሉዓላዊነት ላይ ከፍተኛ ደባና ክህደት መፈጸም ወዘተ..ምንም ዓይነት ዋጋ ላያስክፍል ነውን?
 • .ዊኒ ማንዴላ ለአፓርታይድ ፖሊሶች ሚስጥር ያቀብላል በማለት አንድ ልጅ በማስገደሏ የገጠማትን ማኅበራዊ ተጽኖና ውግዘት ሰምተናል። 300,000 በሚደርሱ የቅይ ሽብር ተጠቂ ቤተሰቦች ፦ሃዘን ፣ ቁስል ፣ህመም ፣ኅዋስ ፣አጥንት፣ ነፍስ/ሶል ፣ሥነ-ልቦና ወዘተ..ላይ ቤንዚን አርከፍክፎ ማጋየት አይሆንምን?
 • በዜጎች ላይ ሰቆቃ መፈጸም ፣ ማስቃየት፣ዘርልባ ማድረግ፣ አካለ ስንኩል ማድረግ፣  መግደል ፣ አስክሬን መሸጥ ወዘተርፈ እንደ መዝናኛ እስፖርት መቁጠር አይሆንምን?

4) የኢትዮጵያ ህዝብ ሥርዓትና ሕግአልባ እንዲሆን ፤ ያራዊት ሥርዓት እንዲከተል አይጋብዝምን?

5) ማኅበረሰባችን ኢ-ግብረገባዊ ፣ኢ-ኅሊናዊ ፣ኢሰባዊ ወዘተ..ባህል እንድያዳብር አይጋብዝምን?                                                                                            በአጭሩ፦  በአገራዊና በሕዝባዊ ሉዓላዊነት ላይ ክኅደት የፈፀሙ፣አንድ ትውልድ የመተሩ፣ ነቃተ-ሊናው ከፍ ያለው ቢያንስ  የሁለት ተውልድ ማኅበረሰብ አባላት እንድ አረም የመነጠሩ፣ሬሳ የሸጡ፣ የአገር ሃብት የዘረፉ ውዘተርፈ የጥፋት ሃይሎች ያለ አንዳች ቅጣት             (retribution) ከሰፊው ሕዝብ ጋር ተደባልቃችሁ ኑሩ ማለት፤ለነገው ትውልድ የሚሰጠው ትምህርት ምንድነው ? ?

በእኔ እይታ መሆን ያለበት ወይም መፍትሄ

1.አንድ ሰው በሃሜት ወይም በጥርጣሪ ወንጀለኛ ስለማይባል፤ተጠርጣሪዮቹ የብሄራዊ እርቅ ኮሚሽን አምኖ በመረጣቸው በወንጀል መርማሪ ሞያተኛ ቡድን   ማስመርመርና ማጣራት

2.ወንጀሉን የተፈጸመው አእምሮ በመታወክ ወይም በሥልጣን መከታ መሆኑንን ማጣራት

3.በሥልጣን መከታ የተፈጸሙትን ወንጀሎች በ [1ኛ፣2ኛ፣3ኛ …]በሚል በደረጃ ማስቀመጥ

4.የሰዎቹ ስም ፈጸሙት ከተባሉት ወንጀል ዝርዝር ጋር ለብሄራዊ እርቅ ኮሚሽን ማቅረብ

5.የብሄራዊ ዕርቅ ኮሚሽን -ወንጀል የፈጸምነው በአእምሮ በሽታ ምክንያት ነው የሚሉትን ወደ እውቅ  የአእምሮ ህመም ሊሂቃን መምራትና የእነሱ የሚሰጡትን የምርመራ ውጤት ተመርኩዞ ለውሳኔ መድረስ

6.የብሄራዊ ዕርቅ ኮሚሽን ከመካከለኛ እስክ ትላልቅ ወንጀል/ሎች የፈጸሙትን ወደ  ፍትህ/ዳኝነት አካል  መምራት/መላክ

7.ትናንሽ ወንጀል የፈጸሙትን ለሕዝብ ተገልጾ ፤ ለብሄራዊ ዕርቅና ስላም ሲባል ከሕዝብ ጋር እየተመካከረ ምህረት ማድረግ

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

1 COMMENT

 1. ——-የመደመር ዜና።የደም-ዋጋ ዜና!!!…….
  ምንድነው ሺህ ማውራት???
  ጉጅሌን መዳራት።
  እናምጣ በዝና፤የመቅደምን ዜና!!!
  ስንጠቃ አቆዩና፤ቃል ግቡልንና።
  አምጡልን በዝና፤
  የመደመር ዜና!!!
  እባካችሁ ወገኔ ዛሬም አትሞኙ፤
  ቅድሚያ ያቺን ቅማል ትኋኗን አግኙ።
  ቅማል እንኳን ባቅሟ፤
  አሳብጧት ደሟ፤
  ጥርሷን ከተከለች፤
  ጥብጣብ ታስፈታለች።
  ሺህ ቦታ መቶ ጥግ በየጉራንጉሩ፤
  ማከክ መሞዠቁ አካል መቆፈሩ፤
  ለሰይጣን ደንግጦ ሬሳ መቁጠሩ፤
  መፍትሔ ባይሆንም እንደው ለጅምሩ፤
  ገዳይ እንዳይቀድመን:-ከልብ ግን አምርሩ።
  ለሕዝብ በመቆማችሁ ባንዳ የጠላችሁ፤
  የኢትዮጵያ ሕላዌ ያንገበገባችሁ።
  ለአገር የምትጓጉ፤
  ትርጁማን ፈልጉ!!!
  ተብሎ የሰለቸ ነገር አትደጋግሙ ፤
  ሕዝቡ ሁሉን ያውቃል ይናገራል ባፅሙ ።
  ይልቅ ለነፃነት እንዲቆም በዝና፤
  ዛሬውን አምጡለት የመቅደምን ዜና።
  ለፍትህ ለፍፉ፤
  ለነፃነት ፃፉ።
  ያሻችሁን በሉ፤
  በሙያችሁ ሁሉ።
  ሁሉም ሆኖ ግና፤
  ቃል ግቡልንና።
  አምጡልን በዝና፤
  የደም-ዋጋ ዜና!!!…….
  ለጥቅም የማሉ፤
  ጋዜጠኞች አሉ።
  ሕዝብን ነገ ብለው፤
  ዛሬ በመንግሥት ጉያ አሉ ተጥልለው።
  ሕዝብን የሚወጉ፤
  ከሕዝብ እንደመሸጉ፤
  ሕዝቡ ቢያቅም ግና፤
  አቅሙን ሰርቀዋልና፤
  አምጡልን በዝና፤
  የመደመር ዜና።የደም-ዋጋ ዜና!!!
  “ተሰለፉ“ “ወጡ““ረበሹ“ “አበጡ ።“
  “አመፁ“ “አደፈጡ““አድማ ተቀመጡ ።”
  ማለቱ አብቅቶ ፤ለፍትሕ መያዙን፤
  ጉጅሌ እጁን ሰጥቶ ወደሞት መጋዙን።
  ከያለበት ሁሉም እየተለቀመ፤
  ለሕዝቡ ይነገረው ከተከረቸመ።
  ካናት መጀመሩን ፤አምጡልን በዝና፤
  ባንዳው መታሰሩን የደም-ዋጋ ዜና!!!
  ምንድነው ሺህ ማውራት ፤ሕዝቡን አነቃቁት ፤
  በብዕር መዳራት በጦማር ጠቅጥቁት።
  ስንቱ ጀግና እያለ ፤ከትግል የወጣ:-
  እንደምን ይውላል አትክልት እያጠጣ።
  ስንት ሙያ እያለው እንዴት በቁም ይሙት?
  ሕዝቡ ከጎኑ ነው ድሉንም አሰሙት።
  ሁሉም ተራው እስኪደርስ:-ማመንዠጉ ጥሞት ፤
  በሰላም ሥም አይድን ፤ውስጥ-ውስጡን ከመሞት።
  እናም ቃል ግቡልን ባናት ዝመቱና፤
  በልሳን በብዕር ሕዝቡን ኮትኩቱና፤
  አምጡልን በዝና:-
  የመቅደሙን ዜና!!!……..
  በሠላም ይሻላል ብለን ስንታገል፤
  ሕዝቡን በታጠቁት አየነው ሲገደል።
  እስኪ ለነጋችን ዛሬን እንኳን ንቁ:-
  ከእባብ እንቁላል የዕርግብ አትጠብቁ።
  በጥራት ፃፉና
  መረጃ አጣፉና።
  አትጠራጠሩ እንደ እነዚህ ያሉ:-
  የጉጅሌን ፍትፍት በደም ይበላሉ።
  ፖለቲካ አይወዱም ሕዝቡን አያስቡም:-
  ገበያና ሽያጭ አውርተው አይጠግቡም።
  እንደጣሊያን ቅዠት ማውራት ነው ግንባታ:-
  “ዶሮን ሲያታልሏት…” እንዳሞኟት ማታ።
  እስኪ አናቱን በሉት ሙያውን አትፍሩት:-
  በልሣን አሰሙን በብዕር ውገሩት።
  እናም ሳይመሽ ቀኑ ሳንደነባበር:-
  እንደ’ነ “አዲስ ነገር” ።
  ደምረነ በሉት ሂዱ ተደመሩ፤
  “በአጦለሌ…”ግና ብዙ ነው ችግሩ።
  መፃፍ አቆዩናቃል ግቡልንና።
  እናምጣ በዝና
  የመደመር ዜና!!!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here