Home News and Views ግልጽ ደብዳቤ ለመላ የኢትዮጵያ ሕዝብ በያላችሁበት -ክፍል ሁለት

ግልጽ ደብዳቤ ለመላ የኢትዮጵያ ሕዝብ በያላችሁበት -ክፍል ሁለት [ፕሮፌሰር ወሰኔ ይፍሩ ]

የተከበራችሁ ወገኖቼ ሆይ በቅድሚያ የከበረ ሰላምታዬን አቀርባለሁ።

በክፍል አንድ ላይ እንደተጠቀሰው፣ በክፍል ሁለት ላይ የሚቀርበው በተከታታይ ያለፉት ሶስት ትውልደ ዘመናት ያደረጉትን ታሪካዊ ፖለቲካ ለውጥ ነው። ይህም በጊዜ ብዛት 90 ዓመታት የፖለቲካ ሂደት ይሆናል። ሂደቱም ሙሉ በሙሉ ስለተጠናቀቀ እንደ ታሪክ መወሰድ ይቻላል። ጊዜውም እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር ከ1930 እስከ 2020 ያለው የፖሊቲካ ሂደት ይሆናል። እንግዲህ ውድ ወገኖቼ ይህንን የፖለቲካ ሂደት በምን አይነት “ሁኔታ” ላይ ሆነን ነው መወያየት የምንችለው? ለውይይቱስ ምን አይነት ቅድመ “ሁኔታ” ያስፈልጋል? በማለት ነው። በአጭሩ የሚያስፈልገው ቅድመ “ሁኔታ” የመናገር፣ የመጻፍ፣ በአጠቃላይ ፍጹም ነፃ የሆነ የብዙሐን መገናኛ፣ ከምንም ነገር ገለልተኛ የሆኑ ጋዜጠኞች ተደራጅተው [institutionalized] ሲገኙ ነው። ጋዜጠኞች ከፖለቲካ፣ ከጎሳ፣ ከሃይማኖትና ከግል ጥቅም ጋር የተያያዘ ነገር ሁሉ ፍጹም ነፃ መሆን ግዴታቸው ነው። የጋዜጠኛ ዋናው ተግባሩ የአገርን ጉዳይ በተመለከት ሁለ ገብ በሆነ መንገድ ተመልክቶ ለሕዝብ ማሳወቅና ጥቅሙንና ጉዳቱን ለይቶ ማመልከት ነው። ከሁሉ በላይ የሕገ መንግሥቱን መከበር፣ የሕግ በላይነትን አስፈላጊነት፣ የግለ ሰቡን ሰብአዊ መብት መከበሩን፣ የፍትሕ ሥርዓት መጠበቁንና መንግሥት በሕዝብ ስም የሚሰራውን በጥብቅ እየተከታተለ ማሳውቅ ነው።

በተጨማሪ ጋዜጠኛ የውጭ አገርን ግንኙነት በዓለም አቀፍ ደረጃ ያለዉን የፖለቲካ ሂደትንና “ሁኔታ” እየተነተነ ለሕዝብ ማሳወቅ ዋነኛ ከሚባሉት ተግባራት አንዱ ነው። እንግዲህ እዚህ ላይ የሚደረገው ጥረት ከዚህ በላይ የተዘረዘሩት የመልካም አስተዳደር “ቅድመ ሁኔታ” እንዴት መፈጠር እንዲሚችሉ መላ ለመምታት ነው። ምክንያቱም ይህ “ሁኔታ” ካልተፈጠረ መልካም አስተዳደር በራሱ ወይም በተአምር ሊፈጠር የሚችል ርዕተ ዓለም አይደለም። ዶክተር አቢይ የኢሀደግን አሽባሪነትና የሰራቸውን ወንጀል ለኢትዮጵያ ሕዝብ አሳውቀው ይቅርታ ጠይቀው በሁለት ዓመት ጊዜ ውስጥ ሕዝብ ለሚመርጠው መንግሥትን እናስረክባለን ብለው ቃል ሲገቡ የነፃነት “ሁኔታ” ተፈጠረ ብለን ነበር። እዚህ ላይ በጥንቃቄ ማስተዋል ያለብን ጠቅላይ ሚንስትሩ ያሉበትን “ሁኔታ” ነው። ለለውጥ ተዘጋጁ ብሎ መልዕክቱን ከማድረስ በላይ ሌላ ስልጣን የላቸውም። ይህም ለጠቅላይ ሚኒስትሩ በጻፍኩት ደብዳቤ ላይ በግልጽ ተቀምጧል፤ ሕዝብ በትግል ያመጣዉን ለውጥ አንድ ሰው ሊቀለብሰው አይችልም። የጠቅላይ ሚኒስትሩም ስራ ከዚህ ሊያልፍ አይችልም። ሆኖም አሸጋግራለህ ባሉት መሰረት የአገሩን ሰላምና የሕዝቡን ደህንነት ማስጠበቅ ግዴታ ነው። ወገኖቼ እዚህ ላይ በቅጡ ማስተዋል ያለብን ተፈጠረ የተባለው “ሁኔታ” በአንድ ሰው ችሮታ የተሰጠ አይደለም፤ ብዙ ሰው በአደረገው ከፍተኛ መስዋዕትነት ነው። እኛ ግን ልክ እንዳለፈው ትውልድ ሳንጠቀምበት ከእጃችን ሊያመለጠን ነው። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለውጥ ሊያመጡልን ነው ብሎ መጠበቅ ቀበሮዋን መሆን ነው፤ ቀበሮዋ በሬ ስታይ ብልቱ ዱብ ብሎ የምትበላው እየመሰላት ትከተላላች ይባላል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ የኢሃደግ ጠቅላይ ሚንስትር ናቸው። ተጠሪነታቸውም ለድርጅቱ እንጂ ለኢትዮጵያ ሕዝብ አይደለም። እኛም በሕዝብ ደም የተገኝዉን “ሁኔታ” ካልተጠቀምንበት ጠቅላይ ሚንስትሩ በደስታ ኢሃደግን በድል አድራጊነት መልሶ ስልጣን እንዲወጣ ለማድረግ መሆኑን ማወቅ ይገባናል። ይህም ሊሆን የሚችለው ከአለፈው ጥፋት ስላልተማርን ነው። ስለዚህ ምናልባት ትምህርት እንዲሆን በማለት ያለፈውን ትውልድ የፖለቲካ ሂደት አጠር ባለ መልኩ ይቀርባል። መልካም ንባብ።

ያለፈው ትውልድ ያደረጋቸው የፖለቲካ ለውጥና ታሪካዊ ሂደት የሚጀምረው በንግርት መልክ ተጽፎ እንደ ምሳሌ ሆኖ ለአንደኛ ደረጃ ተማሪዎች ግብረገብ እንዲማሩበት በግዕዝ ብራና ላይ የተጻፈ ጽሑፍ ነው። ይህ ጸሐፊ ደብረ ሲና በሚገኝው አብዮ ትምህርት ቤት በሚባለው አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በነበረበት ጊዜ በግብረገብ ክፍል በቂስ ታደሰ እየተተረጎመ የተማረው ትምህርት ነው። አስተማሪያችን እንደነገሩን ከሆነ ደራሲው መሪጌታ አጥናፍ ሰገድ ዋቄ ይባላሉ። እሳቸውም የዶባው ባላባት የአቦ ዋቄ ልጅ እንደሆኑና አሉ ከሚባሉት የዋዜማ ሊቃውንት አንዱ እንደነበሩ ይነገርላችዋል። በተጨማሪ መሪጌታ አጥናፍ ሰገድ ዋቄ ተጉለት በሚገኝው አጃና ሚካኤል በሚባለው ደብር የዋዜማ መምሕር እንደነበሩ አስተማሪያችን ይነግሩን ነበር። ተጉለትም በዋዜማ ታዋቂ እንደሆነ ይታወቃል። የሳቸዉንም ጽሁፍ በምንማረበት ጊዜ እሳቸዉን በሃላፊ ጊዜያት ስለሚጠራቸው በዚያን ጊዜ በሕይወት እንደሌሉ ያስታውቃል። የግብረ ገብ መምሕራችን ድምጻዊ ስለነበሩ ግዕዙን ወደ አማርኛ እየተረጎሙ ጣዕም በሚሰጥ ዋዜማ ሲያነቡልን ተመስጠን ነበር የምናዳምጥው። ምንም እንኳ ከ60 ዓመት በፊት ቢሆነውም የመሪጌታውን ትንቢት በሚገባ ላስታውሰው እችል ይሆናል ብዬ እገምታለሁ። ምናልባት ቋንቋው እንደሊቃኑ ላይሆን ይችላል። ታላቁ ሊቅ አፈወርቅ ገብረ ኢየሱስ እንዳለው የአማርኛ ቃንቋ እጅግ የላቀ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቋንቋ ስለሆነ ታላቅ ሊቅ ሲጽፈው ጣዕሙ የተለየ ይሆናል፤ ለማንበብም ሆነ ለመስማት የሚያስቸግር በከፍተኛ ደረጃ የዳበረ ቋንቋ ነው ይላል። ስለዚህ እዚህ በትውስታ የሚቀርበው ቋንቋ እንደ ዋዜማው መምህር ሊሆን አይችልም። ሆኖም በተቻለ መጠን የመመህሩን አጻጻፍ ችሎታ ለማንጸባረቅ እምክራለሁ። ጽሑፉ በነጠላ ዓረፍተ ነገር፣ በመስተዋድድ፣ በአንቀፅና በንዑስ አንቀጽ ታጅቦ ተጽፏል፤ የመሪጌታው ትንቢት እንዲህ ይላል፤

የደጉ እምዮ ምኒልክና የደጓ ንግሥት ዘውዲቱ ዘመን ሲያበቃ ኢትዮጵያ ለሶስት ትውልድ በመከራና በስቃይ ውስጥ ታልፋለች፤ ከቀዳማዊ ምኒልክ እስክ ዳግማዊ ምኒልክ ሲወርድ ሲዋረድ የመጣው የነገሥታት ዘመን እዚህ ላይ ያበቃል። በመጨረሻው ዙፋን ላይ የሚቀመጠውም ንጉሥ ራሱን ወዳድ አገሩን አሳልፎ ለባዕድ የሚስጥ፤ ሃብትና ንብረት በቃኝ የማይል ንፉግ፤ ስለስሙ ታላቅነት ተቀን ሳይታክት የሚሰራ በግለሰባዊነት መንፈስ የተሞላ ሰው ይሆናል። ሰውነቱንም እንደሰው ሳይሆን እንደ ጣኦት እንዲመለክ አድርጎ ለግዛት ዘመኑ ዘለዓ እንዲሆን የሚመኝ ጣኦት አምላኪ ይሆናል። በግዛት ዘመኑም ረሃብ፤ ድርቀት፤ ፍ፤ ማዕበል፤ ሰብሉን ጠራርጎ የሚበላ አንበጣ ይመጣበታል፤ በውጭ ጦርም ተሽነፎ ይሰደዳል። እንደገናም ተመልሶ አገሩን ይገዛል፤ የግዛት ዘመኑም 44 ዓመት ይሆናል፤ በዘመኑም አገሪቷ የምትታወቀው በረሃብና በችግር ይሆናል። ከሱ በኋላ የዘውድ አገዛዝ ዓት በጉግ ማንጉግ ዓት ይተካል፤ የጉግ ማንጉግ ትውልድ ሁሉን አውቃለህ የሚል ይሆናል፤ ሁሉም አዋቂ፤ ሁሉም መሪ ሆኖ እኔ በልጥ እኔ በልጥ በማለት ይገዳደላል፤ እሱ ያለው ከአልሆነ አባቱን፤ እናቱን፤ ወንድሙን፤ እህቱን የሚገድል ትውልድ ነውና፤ መግደልም ግንነት ስለሚመስለው ይመጻደቃል፤ መጎደኛም ስለሆነ ግብረ ገብነት የለውም፤ ከጥፋቱም መማር አይፈልግም፤ ስህተትን ስለማያቅ ምንጊዜም ቢሆን የሚሳሳት አይመስለውም፤ ፍጹም አዋቂ ነኝ ብሎ ያምናል፤ አዋቂነቱንም በግድ እንዲታወቅለት ያደርጋል፤ ራሱን ማወደስ ትልቀኛው ተግባሩ ይሆናል። ግን በራሱ ይል እንደ ንፋስ ብን ብሎ ይጠፋል። ከሱም ቀጥሎ የወንበዴ መንግሥት ይመጣል። ውንብድናውም በአገሩ ታሪክ ታይቶም ተሰምቶም የማይታወቅ ይሆናል፤ ሴትን ልጅ እባልዋ ፊት ይደፍራል፤ ልጅም እናዳፈራ መካን ያደርጋል። የሰውን ንብረት ያለምንም ሃፍረት ይቀማል፤ ይሉኝታ የሚል ቃል ቋንቋው ውስጥ ያለ አይመስልም፤ አገሩን ለውጭ ሃብታሞች ይሽጣል፤ የአገሩን ሃብት ወደ ውጭ አገር ያሸሻል፤ የኢትዮጵያን የተለያዩ ጎሳዎች ለያይቶና በድንበር ከልሎ ነፃ ረሰቦች ናችሁ በማለት ራሱን የብ ሔረሰቦች የበላይ ጠባቂ በማድረግ በሚቃወሙት ላይ የዘር ማጥፋት ያካሂዳል። የብ ረሰቦች ጽንፈኞችን አሰልጥኖ እሳትና መርዝ አጉርሶ እርስ በእርሳቸው እንዲፋጁ ያደርጋል።  ኢትዮጵያ የምትባል አገር አልነበረችም እያለ ሕዝቡን እንዳይግባቡ ያደርጋል። ይህም ፍጅትና መከራ የበዛበት ሕዝብ ሙሉ በሙሉ ይነሳበታል፤ አናሳም ስለሆነ መግቢያ ቀዳዳ ያጣል፤ ያም መከራና ፍጅት የበዛበት መልካሙን ትውልድ ይወልዳል፤ መልካሙ ትውልድ መላ ኢትዮጵያን ይሞላታል፤ ሆኖም ወንበ ተኩላ ሆኖ የበግ ለምድ ለብሶ መልካሙን ትውልድ ሊበላ ይመጣል፤ ግን በመከራ የተፈተነው መልካሙ ትውልድ እራሱን አሳልፎ ለተኩላዎቹ አልሰጥም በማለት በአሽናፊነት አገሩን ኢትዮጵያን ያድናል:: በመጨረሻም መልካሙ ትውልድ ጥንታዊት የሆነዉን የኢትዮጵያን ክብርና ግርማ ሞገስ ይመልሳል፤ የጎሳ እኩልነት፤ ያልቅ ጋ፤ ማርና ወተት እንደ ውሀ የሚፈስበት አገር ትሆናለች፤ እንደገና ኢትዮጵያ በነፃነ ለዘለዓለም ተክብራ ትኖራለች።

የመሪጌታው ንግርት አፈ ታሪክ ነው ተብሎ መወሰድ አይኖርበትም፤ ንግርት የሌለው ሕብረተሰብ የለም፤ በሁሉም ባሕል አለ። ንግርቱም እንደ ትንቢት ተወስዶ ከሃይማኖት ጋር ከተያያዘ የሕብረተስብ ችግር ሊፈታ አይችልም፤ በአገራችን በየጊዜው ባሕታውያን እንደዚህም የሌላ ሃይማኖት ተከታዮች “ሁኔታን” አይተው የሚያስከትለውን በማስታዋል ይናገራሉ። መሪጌታው የሁለቱን ነገሥታት “ሁኔታ” በአንክሮ ተመልክተው በቀጣዩ ሶስት ትውልድ የሚመጣውን መከራ በትክክል ሊያውቁ ችለዋል፤ የመጥፎ “ሁኔታ” ውጤት ጥሩ ሊሆን አይችልም፤ ሌላ ጥሩ “ሁኔታ” ካልተፈጠረ ታሪካዊ ሂደቱ በተከታታይ መጥፎ ስለሚሆን፤ ስለዚህ የትንቢት ጉዳይ ሳይሆን “ሁኔታ” እየተከሰት የሚያመጣው መከራ ነው። እንግዲህ እዚህ ላይ የሚደረገው ጥረት የመሪጌታውን ንግርት መተንተን ይሆናል።

የመጀመሪያው “ሁኔታ” የተፈጠረው በኢጣልያን ፋሺስት ጦርነት ምክንያት ንጉሡ ወደ እንግሊዝ አገር ተሰደው ለአምስት ዓመት ኖረዋል፤ በዚህ አጋጣሚ የእንግሊዘን አገር የአስተዳደር ስርዓትና የንጉሠ ነገሥቱን በአጠቃላይ በአገር ውስጥ ያለውን ተግባር ሳይመለከቱ ከግንዛቤ ያስገቡት የንጉሠ ነገሥቱን ኑሮውንና ክብሩን ብቻ ነበር። የእንግሊዝ ንጉሥ በማግና ካርታ [Magana Carta-Liberation] 1215 የነፃነት ሰነድ ላይ በተፈረመው ውል መሰረት ንጉሡ እንደማንኛውም ሰው የሕግ በላይነትን ተቀብሎ በአገሩ ሕገ መንግሥት ደንብ ለመተዳደር የተስማማመብት ነው። በሕዝብ ምክር ቤትና በጠቅላይ ሚንስተር የሚመራ መንግሥት መመስረቱንና ንጉሠ ነገሥቱ ምንም ዓይነት ስልጣን እንደሌለው አስተውለው ወደ አገራቸው ሲመለሱ ተመሳሳይ “ሁኔታን” ፈጥረው ሕዝባቸዉን ነፃ ሊያወጡ ሲችሉ ስለአልተጠቀሙበት ሕያዉነት የሚያስገኝላቸውን እድል አልፈው ለጥፋት ተዳርገዋል። ታሪካዊ “ሁኔታን” ያለመገንዘብ የሚያስከትለው ጥፋት ከባድ ነው። ንጉሡ ከስልጣን ሲወርዱ ከፍተኛ የጦር መኮንኖች የተከሰትዉን “ሁኔታ” ተመልክተው አገሩን መሪጌታው እንዳሉት ከጉግ ማንጉግ ስር እንዳትወድቅ ማዳን ሲችሉ በቸልተኛነት አገሩን ጥፋት ላይ እንድትወቅ አድርገዋል። ጉግ ማንጉግ በኖ ሲጠፋ የተፈጠረው “ሁኔታ” አገርን መከፋፈልና እንዳልነበረ ማድረግ ስለነበር ለወንበዴዎቹ ጥሩ “ሁኔታ” ስለሆነ ዛሬ አገራችንና ሕዝቡን በክልል የተከለለ የ80 ብሔረሰቦች አገር ሆኖ አክራሪ ጽንፈኞች እያሽበሩ በስርዓት አልባነት የምትገኝ አገር ሆናለች።

በእርግጥ አንድ ሰው “ሁኔታን” ፈጥሮ አምባገነንነትን ሊያመጣ ይችላል። ምክንያቱም የአምባገነንት ባለቤት ምንም ጊዜ ቢሆን አንድ ሰው ነው። የእንግሊዙ ንጉሠ ነገሥት በማግና ካርታ ላይ የሕዝቡን ነፃነት የተቀበለው ተገዶ ነው፤ በኢትዮጵያ ያ “ሁኔታ” ስላልነበረ ነገሠ ነገሥቱ በፈቃደኝነት ለሕዝብ ስልጣንን መሰጠት ፈቃደኛ አልነበሩም። አሁንም ቢሆን ለሕዝብ አምባገነኖች ስልጣንን አይሰጡም። ዲሞክራሲን የሚያመጣ ሕዝብ እንጂ ጠቅላይ ሚንስትሩ አይደለም፤  ዲሞክራሲ በአንድ ሰው ፈቃድ የሚከሰት አይደለም፤ ይህንንም በክፍል ሶስት በዝርዝር ይጻፋል፤ ከዚህ ሌላ ውድ ወገኖቼ በጥንቃቄ መመልከት ያለብን እውጭ አገር ያለን ኢትዮጵያውያን በእነዚህ የለውጦች ዘመናት ምን አይነት ሚና እንደተጫውትን ነው። የምንፈልገዉን ዲሞክራሲ ማምጣት የምንችለው አንድ ሆነን በውውይት ነው፤ የሃሳብም ልዩነት ቢኖር የሚፈታው ዲሞክራሳዌ በሆነ ውይይት ነው። የንጉሠ ነገሥት አገዛዝ አበቃ ሲባል ተሰባስበን ወደ አገር የገባነው ለመወያየትና አገራችንን በዲሞክራሲ እንድትመራ ለማድረግ ሳይሆን እያንዳዳችን ስልጣን ለማግኝት ስለሆነ “ቀይ ሽብር፣ ነጭ ሽብር” ብለን ተላለቅን፤ ይህ መሪጌታ እንዳሉት “የጉግ ማንጉግ ዘመን ሆነ።” በወንበዴዎቹ ዘመን ደግሞ ተሰባስበው የገቡት  “ካሪ ሜትር ቦታ ተመርተው” ኢትዮጵያን ሊከፋፍል ለመጣ ጠላት ሃይል ድጋፍ በመስጠት የጥፋቱ ተካፍይ ሆነዋል። ይህ መጻፍ አለበት፤ ስለዚህ  ይህ ጸሐፊ የዚያ “አጥፍቶ ለጠፋው ትውልድ” ወገን ስለሆነ ያደረግነውን ስህተት ለመጭው ትውልድ መጠቆም አስፈላጊ መስሎ ስለታየው ነው። እንግዲህ “እኔን ያየህ ተቀጣ” ብሎ የሚቀጥለው ትውልድ የቀድሞው ትውልድ የሰራዉን ጥፋት አርሞ ደሙንና አጥንቱን ከስክሶ ለመጣው “መልካም ትውልድ” ማስረከብ ታሪካዊ ግዴታ ነው።

ክፍል ሁለትን ለማጠቃለል ያህል አሁን የተፈጠርውን “ሁኔታ” በአጭሩ መግልጽ አፈላጊ ነው። ኢሃደግ በጠቅላይ ሚንስትሩ አማካይነት በሁለት ዓመት ውስጥ ሕዝብ ለመረጠው መንግሥት ሥልጣን አስረክባለሁ ያለው ተገዶ ነው። ሕዝብ ከእንግዲህ ወዲህ በክልል ለከፋፈለን፣ ለአሰረን፣ ለገደለን፣ ከመኖሪያችን ለአፈናቀለን፣ ዘርን ላጠፋ፣ አገርን ሽንሽኖ ለውጭ ሃይል ለሽጠ መንግሥት ሁለተኛ አንገዛም ብሎ ነው። ይህንን ለውጥ እዉን ለማደረግ የኢትዮጵያ ሕዝብ መነጋገር ያለበት በለውጡ ሂደት መሆን አለበት እንጂ ጠቅላይ ሚንስትሩ ስለሚሾመውና ስለሚሽረው፤ ኢሃደግ ለ27 ዓመታት አደርኩት ብሎ ስለሚሰራው ድራማ፤ ቤተመንግሥት ዉስጥ ወታደሮች ስለአደረጉት ጨዋታ አይደለም። የኢሃደግ ጉዳይ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ጉዳዩ መሆን የለበትም። ነፃ የሆኑና ገለልተኛ የሆኑ ጋዜጠኞች ካሉ ውይይታቸው ስለሚጻፈው ሕገ መንግሥት፤ ስለ ነፃ ምርጫ ቦርድ፤ ስለ ነፃ ፍርድ ቤት፤ ለኢትዮጵያ ምን አይነት ሕገ መንግሥት ያስፈልግታል፤ ሕዝብ በሕዝብ ለሕዝብ ተብሎ ለሚመሰርተው መንግሥት የሚያስፈልገው አመራር ምን አይነት ቢሆን ጥሩ ነው? በፕሬዝዳንትና በጠቅላይ ሚንስትር ያለዉን ልዩነት፤ የፖለቲካ ፓርቲ በምን አይነት መደራጀት እንዳለበት? በጎሳና በብሔር ያለዉን ልዩነት? ታሪካዌ አመጣጡንና ሂደቱን፤ በሕገ መንግሥቱ እንዴት መካተት እንደሚችል? እነዚህ ሁሉ በአዋቂዎች አስተባባሪነት ከሕዝቡ ጋር መወያየት አስፈላጊ ነው።

ከሁሉ በላይ ለውጡን ምክንያት በማድረግ የገቡት ኢትዮጵያን ከአለፈው ትውልድ ምን መማር እንዳለባቸው ከግንዛቤ አስገብቶ ምን አይነት ሚና እንደሚጫወቱ በዝርዝር መታወቅ ይኖርበታል። ይህ ካልሆነ ከአለፈው ጥፋት መማር ስለማይቻል አስፈላጊውን ጥንቃቄ ማድረግ ይገባቸዋል። እስከ አሁን ድረስ ለለውጡ ሂደት የፖለቲካ ፕሮግራም አዘጋጅተው ለሕዝቡ ያቀረቡት ነገር የለም፤ ጥቂት አክራሪ የጎሳ ጽንፈኞች በቁርስና በምሳ ተገዝተው በሕዝቡ ላይ ሽብር እየፈጠሩ ነው። አንዳዶቹም ድርጎ እየተቀበሉ በምርጫ ጊዜ ሽብር ለመፍጠር መዘጋጀታቸው የአደባባይ ሚስጥር ነው። አንድ መቶ የፖለቲካ ድርጅቶች፤ የተለያዩ የጎስ ድርጅቶች የየራሳቻውን ፕሮግራም በማውጣት ተደራጅተዋል። በጎሳ ተደራጅተው የሕዝቡን ደህንነት መጠበቅ ተገቤ ነው። ግን በሃይማኖትና በዘር የፖለቲካ ፓርቲ መመስረት የሚያመጣው የኢሃደግን ክልል መንግሥት ስለሆነ ይህንን ከግንዛቤ አስገብተው ከሕዝባቸው ጋር ተነጋግረው የሕዝብ መንግሥት የሚመሰርበትን “ሁኔታ” መፍጠር ታሪካዊ ግዴታቸው ነው። መልካሙ ትውልድ ደሙን አፍሶና አጥንቱን ከስክሶ ያመጣዉን ነፃነት ማደናቀፍ መሆኑን ተረድተው ያለዉን ልዩነት በውይይትና በዲሞክራሲ አጥብቦ የሕዝብ መንግሥት የሚመጣብትን “ሁኔታ” መፍጠር ታሪካዌ ግዴታ ነው። ይህ ካልሆነ ተመልሶ ያለፈው ትውልድ ያጠፋዉን መድገም ይሆናል።

በክፍል ሶስት ላይ “ዲሞክራሲ እንዴት እንደተመሰረተ ከዓለም አቀፍ ታሪካዊ ሂደት ጋር እያመሳከርን እንማማራለን። አገራችን ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ተከብራ ትኑር።

ክፍል ሶስት ይቀጥላል።

2 COMMENTS

  1. የ ፕ ሮ ፈ ሶ ር ወ ስ ኔ ይ ፍ ሩ ግ ል ፅ ደ ብዳቤ በ ሚ ል ር አስ የ ተ ፃ ፈ ው ን በ ሚ ገ ባ በ ፅ ሞ ና አና በ ጥ ን ቃ ቄ አ ን ብ ቤ ዋ ለ ሁ ::በ አውነ ቱ ያ ለ ፉ ት ን የ 27 አ መ ታ ት የ ጭ ቆ ና የ ግ ፍ የ ሲ ኦል የ አልቂ ት ዘ መ ና ት አ ን ድ ም ሳ ይ ቀ ር በ ዝ ር ዝ ር ተ ፅ ፈ ዋ ል :: ይ ህ በ ክ ፍ ል አ ን ድ ሲ ሆ ን በ ክ ፍ ል ሁ ለ ት ደ ግ ም ለ አ ዲ ሱ ት ው ል ድ ና ለ መ ጪ ው ት ው ል ድ የ ሚ ጠ ቅ ም ከ ፍ ያ ለ ታ ሪ ከ ያ ዘ ለ ቀ ድ ም ሲ ል በ ን ግ ር ት መ ል ከ ስ ለ ባ ለ ታ ሪ ኩአ አ ገ ራ ች ን አትዮ ጵ ያ የ ተንነረ ና
    በ መ ፈ ፀ ም ና ለ ወ ደ ፈ ት ም የ ሚ ፈ ፀ ው ን አ ስ ተ ን ከ ሮ የ ተ ፃ ፈ ስ ለሆ ነ በ ሁ ሉ ም ያ ገ ር ል ጆ ች መ ነ በብ ይ ገ ባ ዋ ል አ ያ ል ኩ ፀ ሀ ፈ ው ከ ፍ ል ሶ ስ ት ይ ቀ ጥ ላ ል ስ ላ ሉ ይ ህ በ መ ፅ ሀ ፍ መ ል ክ ቢ ቀ ር ብ ይ ሻ ላ ል አ ያ ል ኩ ፅ ሁ ፌን በ ዚ ሁ አ ደ መ ድ ማ ለ ሁ ::: ለ አ ስ ተ ዋ ፅ ኦ በ ጀ ጉ አ መ ስ ግ ነ ዎ ታ ለ ሁ ::

  2. በ ድ ጋ ሜ የ ፕ ሮ ፌ ሶ ር ወ ስ ኔ ይ ፍ ሩ ን ግ ልፅ ደ ብ ዳ ቤ ክ ፍ ል ሶ ት ን ና አ ራ ት ን አ ን ብ ቤ ዋ ለ ሁ ቀደ ም ሲ ል አ ን ብ ቤ አ ስ ተ ያ ዬ ቴ ን ና አ ድ ና ቆ ቴ ን መ ግ ለ ፄ ይ ታ ወ ቃ ል ከ ዛ ም አ ል ፎ ከ ደ ብ ዳ ቤ ነ ት ወ ደ መ ፅ ሀ ፍ ቢ ቀ የር ይ ሻ ላ ል ብ ዬ አ ስ ተ ያ የ ት ስ ጥች ነ በ ር በ ዚ ሁ አ ስ ትያ የ ት ፅ ሀ ፊ ው በ መ ስ ማ ማ ት በ ጥ ራዝ መልከ ሁሉንም ከ ክ ፍ ል አ ንድ አስከ አ ራ ት ያ ለ ው ን አ ቅ ር በ ው ታ ል ና ወ ገ ኖ ቼ ኢት ዮጵ ያ ው ያ ን ሁሉ በ ተ ቻ ለ መ ጠ ን አ ን ባ ች ሁ ለ ሌ ው ወ ገ ን አ ን ድ ታ ስ ተ ላ ል ፉ ከ ል ብ አ ማ ፀ ና ለ ሁ ም ክ ን ያ ቱ ም አ ኝ ህ ሀ ገ ር ወ ዳ ድ ም ሁ ር የ ፃ ፉ ት ት ል ቅ አ ው ነ ታ ና አ ሉ ታ አ ለ ው ና ስ ለዚህ ሁ ሉ ም አ ን ደ ሚ ያ ነ በው አ ና አ ን ደ ሚ ደ ስ ት መ ቶ በ መ ቶ ተ ስ ፋ አ ለ ኝ ::ለ ተ ስ ጠ ኝ አ ድ ል አ መ ስ ግ ና ለ ሁ ይ ህ ም አ ስ ተ ያ የቴ ፖስት አ ን ደ ሚ ሆ ን ል ኝ
    በ ሙ ል ተ ስ ፋ በ መ ተ ማ መ ን ነ ው በ ዚ ህ አ ጋ ጣ ሚ ቁአ ጠ ሮ ን በጅጉ ላ መ ስ ግ ን አ ወ ዳ ለ ሁ ያ ለ ፈ ው ን አ ስ ተ ያ የ ቴ ን ፖስት ስ ላ ረ ገ ል ኝ :::
    ከ ሰላም ታ ጋር ::

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here