Home News and Views ለአዴፓ ማእከላዊ ኮሚቴ አባላት

ለአዴፓ ማእከላዊ ኮሚቴ አባላት [ቬሮኒካ መላኩ]

እንደምን ሰንብታችኋል ?
.
የዲያሌክቲክ ህግ እንደሚለን ከሆነ ‹‹መሪዎች አሻፈረኝ ሲሉ ህዝቦች ልክ ያገቧቸዋል›› ይላል፤፤ ዛሬ እንኳን ብቅ ያልኩት እንደ አንድ የድርጅታችሁ ደጋፊ በአንድ ጉዳይ ላይ ለመጻፍ ፈልጌ ነዉ ፤፤የአማራ ህዝብ አብሪ ከኮብ ፖለቲከኛ የሆነዉንና በማእከላዊ ኮሚቴ ምርጫ አንደኛ በመሆን ያጠናቀቀዉን ዶ/ር አምባቸዉን ብአዴን የሚመጥነዉን ከፍተኛ ቦታ እንድሰጠዉ ለማሳሰብ ነዉ፤፤ እንደምታዉቁት በአማራ ህዝብ ዘንድ እኛ የአማራ ልጆች ከእናንተ ከባለስላጣናቱ የበለጠ ተሰሚነት አለን ፤፤ ከላይ እስከታችም ከህዝቡ ጋር እንገናኛለን፤፤ ለእናንተ ለመሪ ፓርቲያችን አዴፓም ምክረ ሀሳብ እናቀርባለን፤፤ ምክረ ሀሳባችንን በቅንነት ወስዳችሁ ከሰማችሁ ድጋፋችን ይቀጥላል የማትቀበሉም ከሆነ ወላድ በድባብ ትሂድና የአማራ ህዝብ አሁን ከአዴፓ ሌላ አብን የሚባል አማራጭ ፓርቲ ብፌዉ ላይ ስለቀረበለት ‹‹መሪዎች አሻፈረኝ ሲሉ ህዝቦች ልክ ያገቧቸዋል›› በተባለዉ የድያሌክቲክስ ህግ መሰረት ልክ ትገባላችሁ ማለት ነዉ፤፤
..
አሁን የአለንበት የክልላችንም ሆነ የአገራችን ሁኔታ እንደምትረዱት ጊዜዉ እጅግ አስቸጋሪና የአማራ ህዝብ ስትራቴጅክ አመራር የሚፈልግበት ወቅት ስለሆነ እንደ ዶ/ር አምባቸዉን የመሳሰሉ አመራሮች የአማራ ህዝብ እጅግ ያስፈልጉታል፤፤

በመሰረቱ አብዛኞቹ ግለሰቦች በፓርቲ የፖለቲካ ህይወታቸው የመታለል እጣ ይገጥማቸዋል፡፡ በትልቅነታቸውና ሆይ ሆይ በሚባሉበት ሰዓት፣ ከቶም መውደቅ የሚል ነገር እንዳለ ትዝ አይላቸውም! በታሪክ የነበሩ መሪዎች፣ የፖለቲካ ኃላፊዎች፣ ታላላቅ ሰዎች እንዴት ወደቁ? የእኔስ አካሄድ ምን ይመስላል? አለማለት፤ ቢያንስ የዋህነት ነው! ከታሪክ አለመማር ነገን ለመገመት አለመቻል ነው፡፡ ነገን አለመገመት የራስን ፍፃሜ አለማጤን ነው፡፡ ስለሆነም የድንገቴ አወዳደቅ አይቀሬ ይሆናል፡፡
..
አሁንም የማሳስባችሁ በደጉ ሰዓት ያላቆያችኋቸዉ ደጋፊዎች ፣ በክፉው ሰዓት አይኖሩምና፤ የማታ ማታ አጋዥ ደጋፊ ማግኘት አዳጋች ይሆናል፡፡ ብዙዎች የሚወድቁት ህዝብ የደገፈን ሲመስለን ጥንቃቄ ስለማናደርግና የእኔው ነው ብለን ስለምንኮፈስ ነው! ሲመሽብን ግን በምን ያህል ፍጥነት ህዝብ እንደሚተፋን፣ በምን ያህል ፍጥነትስ ገፍትሮ እንደሚጥለን ሳንገነዘብ ከአደባባይ ሸንጎ እንወገዳለን። ይህ አጠቃላይ እዉነታ እንዳይደርስባችሁ እኛ የአማራ ህዝብ የምንላችሁን ትሰሙን ዘንድ አሳስባለሁ ፤፤

1 COMMENT

  1. ይህን ስል ግን የትምክህት በማያውቀን ህዝብ መሪ ፓርቲያችን አይናቅ ነው ።አብን ህጋዊ party ነው ።ለጭቁኑ አማራ መቆምም ትክክል ነው ።However it is not yet met my political consciousness level. I dont think it transcend ethinic bab eclipses. ቢሆንም በራፌ ክፍት ነው, የአማራ ፓርቲ ይሁን መብታችን ነው ነገር ግን ለአዳማ አማራ ብቻ ቁሞ የናዝሬት ጉራጌን የማያይ? አብን “የአማራ ፓርቲ ለመላው የኢትይጵያ ህዝብ ነፃነት! ” የሚል motto political metaphysics አድርጎ እስከሚመሰርት ADP አለን ።ዶ/ር አንባቸው እንደኔ ብቸኛው የአብይ ምትክ ነው ።ምክትል እንዲሆን እንታገል, በዛቻ ግን አይሁን ።አብይ የ Machiavelli ን lion ለሚያምነው Utopian መደመር convection ሲል አባሮታልና በህይወት ተወራርዶ ጉዞ ከፍቶ ኢትዮጵያ ሊያደርገው ይችላል -አንባቸውን deputy አድርጎ ማስጠጋቱ ወሳኝ የለውጡ መቀጠል ቀብድ ነው ።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here