Home News and Views ግልጽ ደብዳቤ ለመላ ኢትዮጵያ ሕዝብ በያላችሁበት ወሰኔ ይፍሩ

ግልጽ ደብዳቤ ለመላ ኢትዮጵያ ሕዝብ በያላችሁበት ወሰኔ ይፍሩ [ፕሮፌሰር]

ስለ ኢትዮጵያ ነፃ ምርጫ ለውይይት የቀረበ አጀንዳ

በቅድሚያ የከበረ ሰላምታዬን አቀርባለሁ።

ክፍል  አራት

ክፍል ሶስት ላይ እንደተጠቀሰው በቅደም ተከተል ይቀርባል እንደተባለው ስለ ነፃ ምርጫ ቦርድ፣ ስለ ብሔር ብሔረሰቦች፣ ስለ ጎሳ፣ ስለ የፖለቲካ ፓርቲ አመሰራረት፣ ስለ ነፃ ፍርድ ቤት በዚህ ክፍል ላይ በዝርዝር ይቀርባል። ሌላው እጅግ በጣም አስፈላጊ ነው የምንለው ነገር ቢኖር ምርጫው በምን አይነት “ሁኔታ” ይካሄዳል በሚለው ጉዳይ ላይ ነው።  ይህንን በተመለከተ በዚህ በመጨረሻው ውይይታችን ላይ በዝርዝር ይቀርባል፤ ይኸውም ዲያስፖራው ምን ሊረዳ እንደሚችል፤ የምርጫ ሳጥን [Eletronic Machine] ከተለያዩ አገሮች በእርዳታ የምናገኝበትን “ሁኔታ” ማመቻቸት፤ ሕዝብ የተስማማበት ከሶወስት ወይም ከአራት የማይበልጡ የፖለቲካ ፓርቲዎች በስምምነት የሚመሰረትበትን “ሁኔታ”፤ ለምሳሌ የገበሪዎች፤ የወጣቶች፤ የሴቶች፤ የሰራተኞች፤ ሕዝቡ በየቀበሌው፤ በየወረዳው፤ እንዴት ተደራጅቶ የምክር ቤቱን አባል እንዴት እንደሚመርጥ [A blue print and a road map for genuine democracy] እነዚህን ሁሉ ለማከናወን የሚወስደው ግዜ ተሰልቶ እንዲስተካከል ማሳሰብ፤ የምርጫው ቦርድ በምን አይነት “ሁኔታ” እንደሚመሰረት፤ ነፃ ፍርድ ቤት በሕገ መንግሥቱ ተደንግጎ ስራ ላይ እንዲውል ማድረግና ወንጀለኞች ወደ ፍርድ የሚቀርቡበት፣ የተዘረፉትና ወደ አንድ ክልል ቦታ ተወሰደው የተከማቹት የእንዱስትሪ ማምረቻዎች የሚመለሱበት “ሁኔታ” ማመቻቸት፤ በሕገ ወጥ መንገድ ተዘርፈው በውጭ አገር ባንኮች የተቀመጡ ገንዘብ በዓለም አቀፍ ፍርድ ቤት አማካይነት የሚመለሱበትን “ሁኔታ” መወያየት አስፈላጊ ነው። እነዚህ ሁሉ በቅጡ ተጠንቶ በዚህ ክፍል ላይ ይቀርባል። ግን እዚህ ላይ በጥንቃቄ ከግንዛቤ ውስጥ ማስገባት ያለብን የለውጡን ሂደት ለማሰናከል ወይም ደግሞ በመደመር መልክ እንደገና የለውጡ ደጋፊዎች ነን በማለት ወደስልጣን ለመመለስ የሚያደርጉትን ጥረት አጥብቀን መከላከል ይኖርብናል። የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ዲሞክራሲያዊ ግንባር (ኢሕደግ)ን ጠግነው ቢመለሱ የሚያመጣው የተለመድውን እልቂት እንጂ ለውጥን አይደለም። የ27 ዓመቱ አብዮትዌ ዲሞክራሲ፤ የብሒር ክልል መንግሥት፤ የብሒር ብሒረሰቦች እኩልነት ያመጣው አብዮታዌ ግርግርን ነው፤ የክልል ፌደራሊዝም ያመጣው ዘር ማጥፋትን፤ መፈናቀልንና ዝርፌያን ነው፤ ወያኔ አሁን የሚጮኸው በግርግር የሚሰርቀውንና የሚዘርፈውን ሃብት ስለቆመበት ነው። ሊያቀው የሚገባ ነገር ቢኖር ሁለተኛ የማሰር፤ የመግደል፤ ዘር የማጥፋት፤ በሕገ ወጥ መንገድ በቢሊዮን የሚቆጠር የአገር ሃብት ወደ ውጭ ማሸሽ ያለመቻሉን ነው፤ በዓለም አቀፍ ሕግ መሰረት ይጠየቃል፤ [Money Laundering, Illicit funds and Stolen Money , according to US Department of Justice and FBI is illegal; public corruption, no matter where it occurs, is a threat to a fair and competitive global economy. The FBI is committed to working with foreign and domestic partners to identify and return these stolen assets to their legitimate owners]. በቻይና፤ በሲንጋፎር፤ በመካከለኛው ምስራቅ፤ በካናዳ ባንኮች ውስጥ  የተቀመጡ ገንዘብና ንብረቶች የኢትዮጵያ ሕዝብ ስለሆነ በዓለም አቀፍ ሕግ መሰረት ማስመልሰ ግዲታ ስለሆነ አጥብቀን በስራ እንዲውል ማድረግ ነው። በተጨማሪ ወያኔ ለዉጡን ለማወናበድ ያልሆነ ታሪክ አለ እያለ የሚያወራዉን ፕሮፓጋንዳ ለሕዝብ ማሳወቅ ታሪካዌ ግዲታ ስለሆነ ጎሳ፤ ብሒር፤ የብሒር ብሒረሰብ እኩልነት፤ አብዮታዌ ዲምክራሲ፤ ዲሞክራሲ ምን ማለት እንደሆነና ታሪካዌ ሂደታቸውን እያመሳከርን እንወያያለን፤ ነገር ግን የምርጫውን ሂደትና ሕገ መንግሥቱን ሕዝብ በየቀበሊው ውይይት ተደርጎ  ስምምነት ላይ ሳይደርስ ወደ ምርጫ መሂድ ታጥቦ ጭቃ መሆኑን በቅድሚያ ማወቅ ይኖርብናል።  መልካም ንባብ።

ውይይታችን በመረጃ እየተደገፈ እንዲዳብር በማለት ታሪካዌ ሂደቶችን እየጠቀስን በተረጋጋ መንፈስ ሆነን መወያየት አስፈላጊ ነው። ኢትዮጵያ ጥንታዌት አገር ነች ስንል ታሪክን ምስክርነት ይዘን ነው። በአንጻሩ ደግሞ ኢትዮጵያ የተፈጥረችው በምኒልክ ዘመን የዛሬ መቶ ዓመት ነው፤ ከዚያ በፊት “የበርካታ ብሒረ ሰቦች በነፃነት በብሒር ተደራጅተው” የሚኖርበት አካባቢ ነው [አገር እንዳይባል ኢትዮጵያ የሚባል የለም ተብላል] ሲባል አይን ያወጣ የባንዳዎች ፕሮፓጋንዳ ነው። ይህንን በተመለከተ በተረጋጋ መንፈስ ሆነን አጠር ያለ ውይይት እናድርግ።

ጎሳ ማለት ምን ማለት ነው? ስቲቭን ኦፕንሃመር [Stephen Oppenheimer, 2004] የሚባል የኦክስፎርድ ዩነቭርስቲ [Professor of Anthropology at Oxford University] የስነ ፍጥረት መምሕር ስለ ሰው ልጅ “ታሪካዌ” ሂደት ሲጽፍ እንዲህ ይላል፤

የሰው ልጅ አመጣጡና እድገቱ አስገራሚ ነው። ከሁሉ በላይ እጅግ በጣም ያስገረመኝ ነገር ቢኖር የሰው ልጅ ከአንድ አፍሪቃዌ እናትና አባት መምጣቱን ያለማወቁን ነው፤ በአንድ ወቅት አውሮፕላን ጣቢያ ላይ ሆኜ የተገነዘብኩት ነገር ነው። ቺጋጎ አውሮፕላን ጣቢያ ትኪት ማስቆረጫ ላይ የተሰለፉትን ሰዎች ስመለከት አንዱ ከካሪያባን፤ አንዱ ደግሞ ከአውሮፓ፤ ሊላው ደግሞ ከአውስታራሊያ፤ ከኒው ግኔ፤ ከደቡብ አሚሪካ፤ ከሕንድ፤ ከቻይና ለስብሰባ ለመሂደት ትኬታቸውን ለማስቆረጥ በተሰለፉበት ወቅት አይን ለአይን አይተያዩም ነበር። ይህም የሆነበት ምክንያት ከተለያየ ዘር ነን ብለው ስለሚያምኑ መተያየቱን አስፈላጊ ሆኖ ስላ አላገኙት ነው። ነገር ግን እነዚህ ሰባት ሰዎች ከአንድ እናትና አባት የተወለዱ አፍሪቃውያን ናቸው [ Stephen Oppenheimer 2004].

ይህ ማለት  እነዚህ ከተለያየ አገር የመጡ ሰዎች ጎሳችው ቢጠና ከአፍሪቃዋ እናትና ከአፍሪቃው አባት ነው። የሰው ልጅ ዘር አንድ ነው፤ እንደ እህል ዘር የተለያየ አይደለም፤ ጢፍንና ማሽላን ቀላቅለህ ብትዘራው የምታገኝው ሰብል “ማሽላና ጢፍን ነው፤ ማሽላው ጢፉን መስሎ አይበቅልም፤ ጢፉም ማሽላን መስሎ አይበቅልም። እንግዲህ “ጎሳ” በታሪክ ውስጥ እጅግ ጎልቶ የሚታየው በአስራ ሁለቱ ነገደ እስራኢላውያን ነው። ይህንን እንመልከት።

ብሔር ምን ማለት ነው? ከላይ ስለጎሳ የተሰጠዉን “ታሪካዌ” ሂደት በትኩረት ብንመለከት “የብሔርን” አመጣጥ ይነግረናል። ሕንድ፤ ቻይና፤ ኒው ግኒ፤ አውስታራሌያ ብሒር ናቸው፤ ማለትም አገር ወይም መንግሥት ማለት ነው። አስራ ሁለቱ የእስራኢል ጎሳዎች ደግሞ አንድ ነገድ ወይም ብሒር ናቸው እንጂ በሔሮች አይደሉም፤ “ብሔር” አይበዛም አንድ ነው። ደግሞ “ብሔረ ሰቦች” ሲባሉ የሚያመለክተው የተለያዩ አገሮችን እንጂ አንድ አገርን አይደለም፤ ለምሳሌ አሜሪካ የተለያዩ “ብሔረ ሰቦች” ያሉበት አገር ስለ ሆነች ሊለያይ የማይችል አንድ “ብሔር” ተብሎ ነው የሚጠራው። ጥንታዌት ኢትዮጵያ ከሰማንያ የሚበልጡ “ጎሳ” ያለባት አንድ “ብሔር” ነች። በረጅም ግዜ ታሪካዋ የተለያዩ “ብሔረ ሰቦች “ ሆና አታውቅም፤ ማለትም ከሕንድ፤ ከቻይና፤ ወይም ራሱን ችሎ እንደ አገር ሆኖ የተደራጀ “ብሔረ ሰቦች” አልነበረችም። ዘመነ መሳፍንት “የብሔረ ብሔረሰቦች” አገዛዝ ሳይሆን “የጎሳ” ክፍፍል ነው። ምኒልክ “ጎጃምን” “ወሎን” “በጌምድርን”፤ “ኦሮሞን” “ደቡቡን” ቀጥ ቅጦ ነው አንድ ያደረገው ፤ በተለይም የኦሮሞን ሴት ጡት ቆርጣል የተባለው የባንዳ ልጆች ፕሮፓጋንዳ ነው፤ ሚኒልክ ጠብቶ ያሳደገውን ጡት አልቆረጠም፤ የምኒልክ እናት ወይዘሮ እጅጋየሁ የጫጫው ባላባት የአቦ“ዋቆዮ” የልጅ ልጅ ናቸው፤ የተቆረጠውንም ጡት የሚያሳየው ሐውልት ሕዝብን እርስ በርሱ ለማፋጀት የተደረገ ጥረት መሆኑን የኢትዮጵያ ሕዝብ ማወቅና ይህንን የጥላቻ መታሰብያ ማፈርስ “ታሪካዌ” ግዴታ ነው። ከዚህ በተጨማሪ በኢትዮጵያ ታሪክ ንጉሠ ነገሥቱ ከአንድ የተለየ ብሒር ሆኖ አያውቅም፤ ቀዳማዌ ኃይለ ሥላሴ ከግማሽ በላይ ኦሮሞ ናቸው፤ ልጅ ኢያሱ የራስ አሊ [ንጉሥ ሚካኢል] የወሎ ኦሮሞ ባላባት ልጅ ናቸው፤ በንጉሠ ነገሥቱ ዘመን የገዥው ክፍል ከሁሉም ጎሳ የተሰባሰበ ነው፤ መንግሥቱ ሃይለማርያም ኦሮሞ ነኝ ይላል፤ እንዲት ሆኖ ነው የአማራ ጎሳ ለነበረው “ሁኒታ” ሁሉ ተጠያቂ ሊሆን የሚችለው? በኢትዮጵያ ታሪክ “የጎሳ” የበላይነት የተጀመረው በወያኔ ዘመነ መንግሥት ነው፤ የሂትለርን ትግል [ My Kempf or My Struggle] አንብቦ በስራ እንዲውል ያደረገው መለስ ዜናዌ ነው፤ የኤርያን ወይም የኖርዲክ ዘር [ Aryan or Nordic race] የሚለዉን የሂትለርን የጀርመን በላይነት ሃሳብ ተክትሎ ነው “እንደ ወርቅ ከጠራው ከትግሬ ሕዝብ መወለዴ ያኮራኛል” ያለው። ግብዝነቱ እንጂ የትግሬ ሕዝብ “ወርቅም” “ብርም” “መዳምም” አይደለም፤ እንደ ሊላው ወንድሞቹና እህቶቹ ሰው ነው፤ የትግሬ ክብርና ሞገሱ ጥንታዌት ኢትዮጵያ ነች፤ ከዚህ ውጭ የትግራይ ብሔር መንግሥት በታሪክ ኖሮም አያቅም፤ ይህንን የትግራይ ምሁራን ለትግራይ ሕዝብ ማሳወቅ ታሪካዌ ግዲታቸው ነው።  ጎሳን በተመለከተ አጠር ያለ ውይይት ያስፈልጋል። በተለይ በአማራና በኦሮሞ መካከል ያለው ግንኙነት ልዩ ነው፤ እንደነዚህ ሁለት ጎሳዎች የተደባለቀ የለም፤ በተለይ የሸዋው አማራና ኦሮም ሙሉ በሙሉ መለየት በማይቻልበት “ሁኔታ” ላይ ነው ያለው፤ ሸዋ ውስጥ ያለ ኦሮሞኛ ተናጋሪ አማራ ነው፤ ይህም በግራኝ መሐመድ ወረራ ግዜ የተካሂደ ታሪክ ነው።  የአዲስ አበባ ሕዝብ ግማሹ አማርኛ ተናጋሪ ኦሮሞ ነው። ይህ በታሪክ ተደግፎ መጻፍ ይኖርብታል። ያለማወቅ ደፋር ያደርጋል እንደተባለው የወያኒ ካድሪዎች “አማራና ኦሮም እሳትና ጭድ ናቸው” እያሉ የሚያሶሩት ከፋፍሎ ለመግዛት ነው።

አብዮታዌ ዲሞክራሲ ማለት በክፍል ሶወስት ላይ በአጭሩ እንደተጠቀሰውና ሜጀር ጄነራል ባጫ ደበሌ እንዳሉት “የማፍያ ግርግርና የአሸባሪዎች” መዝረፊያ ዘዴ ነው። የአብዮታዌ ዲሞክራሲ ጽንሰ ሃሳብ ተቆንጽሎ ይተወሰደው ከማርክሲዚምና ከሊንንዝም ርዕይተ ዓለም ነው [Marxsim/Leninsm]። የዚህን ጽንሰ ሃሳብ ጥራዝ ነጥቀው “በራሳቻው አመለካከት “ጎሳውን ብሒር” ነው፤ “ብሒሩን ክልል”  ነው፤ “ክልሉን መንግሥት”  ነው በማለት በዓለም ታሪክ ውስጥ ታይቶ የማይታወቅ ዝርፊያና ገደብ የሊሽ ሌብነት የተካሂደበት፤ በዓለም ውስጥ ታይቶ የማይታወቅ የሰብአዌ መብት ጥሰት የተካሂደበት “ሁኔታ” ነው። ዝርፊያውና ሌቢነቱ ገደብ የሊሽ ነው። ኢትዮጵያን እርቃነ ስጋዋን አስቀርተው ምንም ነገር የለንም በማለት የካዱበት “ሁኔታ” ነው አሁን ያለው። ይህም ማለት “ያዘው” “ልቀቀው” የሚል “ሁኔታ” ሊፈጥር ይችላል የሚል ስጋት አለ፤ አንድ የሕግ ባለሙያ በአደረጉት ጥናት ላይ እንደዘገቡት ያለፉት ሶወስት መንግሥታት ከውጭ ያገኙት እርዳታ የዝርፊያውን ልክ በሚገባ ያሳያል። በንጉሠ ነገሥቱ ዘመን  በአርባ ዓመታት ውስጥ ከውጭ የተገኝው እርዳታ $ 4.5 ቢሊዮን ዶላር፤ የደርግ መንግሥት በአስራ ሰባት ዓመታት ግዜ ውስጥ ያገኝው $ 5.0 ቢሊዮን ዶላር ሲሆን የወያኔ መንግሥት በ27 ዓመታት  ግዜ ውስጥ ከውጭ በእርዳታ  $50 ቢሊዮን መሆኑን አሳውቀዋል። ከዚህ ሊላ በኢትዮጵያ ሕዝብ ስም $20 ቢሊዮን ከውጭ ተበድረዋል፤ በድምሩ $70 ቢሊዮን ዶላር የት እንዳለ ሊታወቅ አልቻለም ብለዋል።  ለዚህ ሁሉ ተጠያቂው መለስ ዜናዌ ያወቀረው “የማፊያው አሸባሪ” መንግሥት ነው።

እንግዲህ በዋነኛነት የሚቀርበው ጥያቄ ከላይ የተጠቀሰዉን የሕዝብ ገንዘብ እንዲት ማስመለስ ይቻላላል?  ወንጀሎኞች በምን አይነት ፡ሁኔታ” ፍርድ ሊቀርቡ ይችላል? ነው። ከዚህ በተጨማሬ አሽዋ ስካር ነው ተብሎ፤ የአገር መሬት በጅምላ ተሸጦ፤ የግል አየር መንገድ በግለሰብ ተደራጅቶ፤ የኢትዮጵያ መርክብ ኃይል በግለ ሰብ ተገዝቶ፤ አትራፊ የተባሉትን የመንግሥት ድርጅቶችን እንደ አየር መንገድ፤ መብራት ኃይል፤ ቴሊኮሙኒኬሽን ወደ ግል ንብረት እንዲዛወሩ ተመቻችቶ፤ የትግራይ ሕዝብ መረዳጃ፤ የሜቴክ ድርጅት፤ በአጠቃላይ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚክስ አውታር በወያኔ ስር አድርጎ፤ በአገሩ ውስጥ አሉ የተባሉትን እንዱስትሪዎች በአጠቃላይ ወደ ትግራይ ክልል ተካቶ፤ በዓለም ላይ ታይቶና ተሰርቶ የሚያውቅ ስብአዌ መብት ተጥሶ፤ የሰውን ልጅ እራቁቱን ከአሪዌት ጋር እጫካ ውስጥ እንዲያድር ተደርጎ፤ የሰው ልጅ ከነነፍሱ መቃብር እንዲገባ ሆኖ፤ የአካሉ ቆዳ እንዲበጣጠስ ፤ የወንዱ ልጅ ብልት ተኮላሽቶ፤ ሴታን መካን አድርጎ፤ በቂም በቀል ዘር ጠፍቶ በአለበት “ሁኔታ” ለውጥን ማምጣት ያለበት ሕዝብ እንጂ እነዚህን ሁሉ አሰቃቂ ወንጀል የሰራ ኢሕደግ አይደለም። ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ለኢትዮጵያ ሕዝብ የገቡት ቃል “በሁለት ዓመት ውስጥ በምርጫ ማስረከብ ነው እንጂ ኢሕደግን መልሶ ስልጣን ለማውጣት አይደለም።  አሁን ያለው የለውጥ ሂደት የተገኝው በሕዝብ ታላቅ መስዋዕትነት ነው፤   ስለዚህ የኢትዮጵያ ሕዝብ ሳይቻኮል በተረጋጋ መንፈስ ሆኖ ከጠቅላይ ሚንስትሩ ጋር በተዋዋለው መሰረት “መንግሥት በሕዝብ ለሕዝብ” ብሎ በዲሞክራሲ ተወያይቶ አዲሲታን ኢትዮጵያን ይመሰርታል። ስለዚህ ከዚህ የሚከተሉትን መርሃ ግብር በቅደም ተከትል በስራ ላይ ማዋል ታሪካዊ ግዲታ ነው።

 

 1.  ሕገ መንግሥትና ዲሞክራሲ ማለት ምን ማለት ነው? እንዲትስ በስራ ላይ ሊውል ቻለ? በዚህ መርሃ ግብር ላይ በየቀቢለው ሰፋ ያለ ውይይት ያስፈልጋል። ለውይይቱ እንዲረዳ በማለት የአሚሪካንን ሕገ መንግሥትና ዲሞክርሲ አመጣጥ በአጭሩ ይቀርባል [በሶወስትኛው ክፍል ተጠቅሳል]።

የአሚሪካ ሕገ መንግሥትና ዲሞክራሲ ምንጭ

የአሚሪካ ሕገ መንግሥት “አባቶች” እየተባሉ የሚታወቁት ሕግ አርቃቂዎች ሕገ መንግሥታቸዉን ያረቀቁት ከተለያዩ አገሮች በተሰባሰቡ ስነ ፍጥረትን በአትኩረት ከሚያጠኑ የፍልስፍና ተመራማሪዎች ነው። የሰኒጋሊስ ስነ ፍጥረትና ታሪክ ምሁር ሼክ አንታ ዲዮፕ በጥናት እንደደረሰበት ፍልስፍናን ፍልስፋና የሚያደርጉት ሁለት ባሕርይ ሴኖሩት ነው ይላል። አንደኛው  ተፈላሳፊው “እሱ ራሱን መሆኑን ሲያቅ “ ሁለተኛው ደግሞ ተፈላሳፊው “እውነት የሆነውንና እውነት ያልሆነውን ለይቶ ሲያቅ” ነው ይላል። እንስሳትና ሰው የሚለዩት በዚህ መስፈርት ነው። እንስሳት ራሳቸውን ያውቃሉ ግን “እውነትንና እውነት ያልሆነዉን” ነገር ያውቃሉ ማለት ያስቸግራል፤ “እውነትንና እውነት ያልሆነዉን” ለይቶ ማወቅ ትኩረትን ይጠይቃል፤ ስለዚህ ሰው ስለሆነ ብቻ ትኩረት ይኖረዋል ማለት አይቻልም። ትከረት ከሊለ “እውነትንና እውነት ያልሆነዉን ነገር ማወቅ ያስቸግራል። ስለ ፍልስፍና ጥራት ሁለት “ሐተታዎችን” የጻፈ የምዕራብ አፍሪቃው አሞ የሚባል ፈላስፋ ደግሞ [Amo, West African Philosopher 1703/1759]  “ፍልስፍና ጥራት ሊኖረው የሚችለው ተፈላሳፊው ቅን በሆነ ልቦና እና ትክክል የሆነ የስነ ፍጥረትን መመርመሪያ ሲከተል ነው” ይላል። እንግዲህ እዚህ ላይ በአትኩረት መመልከት ያለብን የአሚሪካ ሕገ መንግሥትና ዲሞክራሲ በምን አይነት “ሁኒታ” እንደተፈጠረ ነው፤ የሕገ መንግሥታቸዉን መግቢያ እንመልከት።

Preamble

We the People of the United States, in Order to form a more perfect Union, establish Justice, insure domestic Tranquility, provide for the common defense, promote the general Welfare, and secure the Blessings of Liberty to ourselves and our Posterity, do ordain and establish this Constitution for the United States of America.

እንግዲህ ይህንን የሕግ መግቢያ ስንመለከተው የሚያሳየው የሕዝቡን አንድነት ነው። “እኛ በአሚሪካ ውስጥ የምንኖር ሕዝብ ሕብረታችን ከምንግዚም በፊት እንዲዳብር፤ ፍትህና ሰላም እንዲኖረን፤ ዳር ድንበራችን እንዲጠበቅ፤ ለሁላችንም መልካም አስተዳደር እንዲኖረን፤ ተባርኮ የተሰጠነን ነፃነት ለእኛና ለመጭው ትውልድ እንዲተላለፍ በማሰብ ይህንን ሕገ መንግሥት ለተባበረችው አሚሪካ የመተዳደሪያ ደንብ እንዲሆን አጽድቀናል።” ይህ ከተባለ በኃላ ለአገራቸውና መለያ ለሆነው ባንዲራቸው ያላችውን ክብርና እምነት ለመጠብቅ ቃል ኪዳን ይገባሉ:: “I pledge allegiance to the Flag of the United States of America and to the Republic for which it stands, one nation, indivisible, with liberty and justice for all.”

እዚህ በአትኩረት የምንመረምረው በመግቢያው ላይ  የተጻፈብትን ቃላት ነው፤ “የአገር ሰላም” “የአገር መከላኪያ ጦር” “የአገር መልካም አስተዳደር” “ከትውልድ ትውልድ የሚተላለፈው ነፃነት” ሲሆን “ጎሳ” “ብሔር” “የብሔር ቢሔር እኩልነት” “አብዮታዌ ዲሞክራሲ” የሚል ነገር የልበትም ። ቃል ኪዳናቸውም ለባንዲራቸው፤ ለማይከፋፈለው  ሕዝብ፤ ለነፃነታቸውና በፍትሕ ለተመሰረተችው ለተባበረችው አሚሪካ መቆመቻዉን ያስታውቃሉ።

የአሚሪካ ሕዝብ ከመላ ዓለም የተሰባሰበ ነው፤ የሊለ አይነት ጎሳ የለም፤ ምንአልባትም ከማንም አገር የበለጠ የጎሳ አይነት ያለበት አገር ነው ማለት ይቻላል፤ ግን ልዕላዊነትን መርጦ አንድ ሕዝብ በመሆን የማይከፋፈል  አገር በሕገ መንግሥቱና  በዲሞክራሲ የሚመራ ስርዓት መስርተዋል። ሕጉም የተረቀቀው ከተለያዩ ፈላስፋዎች በተወሰደ ጽንሰ ሃሳብ ነው። ለምሳሌ የአንድ አገርን መንግሥት አስተዳደር ለሶወስት ከፍሎ የጻፈውን የፖለቲካ ስርዓት ተመራማሪዉን ፍልስፍና የወሰዱት ሞንቴስኪው [Montesquieu 1689/1755] ከሚባለው የፈረንሳይ ፈላስፋ ላይ ነው። በሶወስት የተከፈሉት  የአስተዳደር ስልጣን ክፍሎች ሚዛናዊ ስለሆኑ በእኩልነት የአገሩን ዲሞክራሲ ይጠብቃሉ፤ የሕዝብ ምክር ቢት ሕጉን ያወጣል፤ ፍርድ ቢቱ ሕጉን ይተረጉማል፤ የአገሩ መሪ ሕጉን ያስከብራል፤ አንዱ ከአንዱ አይበልጥም፤ ሶወስቱም መንግሥት በእኩልነት እየተጠባበቁ ሕዝቡን በዲሞክራሲ እንዲተዳደር በአንድነት  ሆነው ይመራሉ። ያለመግባባት ሲፈጠር በዲሞክራሲ ይፈታል፤ የአገሩ መሪ ሕግን ሲተላለፍ ፍርድ ቢቱ ያግተዋል፤ የሕግ በላይንትን አልቀበልም  ሲል ደግሞ የሕዝብ ምክር ቢቱ  ከጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ጋር በመተባበር ከአመራር ስራው ላይ ያነሰዋል።

የአሚሪካንን ሕገ መንግሥት ታሪካዌ ከአደርጋቸው አንዱ የሰብአዌ መብት ነው [The Bill of Rights]። ይህም ጽንሰ ሃሳብ የመጣው ከእንግሊዛዌ ፈላስፋ ጆን ስተዋርት ሚል [John Stuart Mill 1806/73] ነው። የግለ ሰብ መብት ሊታገት የሚችለው የሕብረተሰቡን መብት ሲነካ ብቻ ነው፤ ይህ እስከ አልሆነ ድረስ የግለሰቡ መበት መነካት የለበትም፤ ብዙኃኑ የአናሳዉን መብት እንደራሱ አድርጎ መጠብቅ አለበት ይላል፤ የአሚሪካ ሕገ መንግሥት አጥብቆ የግለሰቡን መብት ከሁሉ አብልጦ ያስከብራል። ቮልተየር [Voltaire 1694/1778] የሚባለው የፈረንሳይ ፈላስፋ ሃይማኖትና መንግሥት መለያየት አለባቸው ይላል፤ መንግሥት ሃይምኖት ስራ ውስጥ፤ ሃይማኖት መንግሥት ስራ ውስጥ መግባት የለበትም፤ ግለሰብም የፈለገዉን ሃይማኖት መከተል መብቱ ነው፤ መንግሥትም እግለሰቡ ሃይማኖት ውስጥ መግባት የለብትም፤ የመናገር፤ የማመልክ፤ የመነገድ መብት መነካት የለበትም ይላል፤ የአሚሪካ ሕገ መንግሥት እነዚህን መብቶች በጥንቃቄ ይጠብቃል፤ በተጨማሪ ሕግ አርቃቂዎቹ የበርካታ ፈላስፋዎችን ጽንሰ ሃሳብ በመውሰድ የተጻፈ ሰነድ ነው፤ እንደ አስፈላጊነቱ ሕገ መንግሥቱ ይሻሻላል፤ በ 225 ዘመን ውስጥ ለ27 ጌዜ ተሻሽላል።

እንግዲህ የአሚሪካ ሕገ መንግሥት የተወለደው በርከት ከአሉ ስነ ፍጥረትን ከሚመራመሩ ፈላስፋዎች በተወሰደ ጽንሰ ሃሳብ ነው። ሰነዱ የሰዉን ልጅ ባሕርይ በሚገባ ሊቆጣጠር የሚችል መስፈረት ነው። ይህም ሆኖ የሕገ መንግሥቱ ታሪካዌ ሂደት ብዙ ውጣ ውረድ ነበረበት፤ ሕገ መንግሥቱ በፈጠረው “ዲሞክራሲ” የተባበረችው አሚሪካ “አንድ ሕዝብ”፤ “አንድ የማይከፋፈል አገር” “የገለሰብ መብት የሚጠበቅበት ሕብረተሰብ” “በአንድ ባንዲራ” ስር ሆኖ በስምምነት ለመኖር ቃል ገብቶ አገሩን የመሰረተበት “ሁኔታ” ነው። ግን በአጭር ግዜ ውስጥ ያንን ቃል ኪዳን የሚያፈርስ ኃይል ተነስቶ ነበር፤ እንግዲህ ትኩረታችንን ከፍ አድረገን ማየት ያለብን እንደገና “ራሴ ላስ” ላይ የተጻፈዉን [ሶወስተኛውን ክፍል ያንብቡ] ፍጡራዌ የሆነዉን ታሪካዊ ሂደት ነው። ይኸውም በእንስሳና በሰው ልጅ ያለውን ፉጡራዌ የሆነዉን ገደብና ገደብ የሌሽን እርካታ ነው። የሕግ በላይነትን አንቀበልም ብለው ገደብ የሌሽን ፍላጎታቸዉን ለማርካት የፈለጉ ግለሰቦች ችግር በመፍጠር አዲስ የተፈጠረውን ዲሞክራሲ ሊያፈርሱ በተለያዩ ግዜ ሞክረው ነበር። ነገር ግን የሕግ በላይነትን ተቀብለው አገራቸዉን በዲሞክራሲ እንድትመራ የፈለጉ ዜጋዎች ታላቅ ተጋድሎ በማድረግ የአሚሪካንን ዲሞክራሲና የግለስቡን “ሰብአዌ መብት” አሰከብረዋል፤ በተለይ የጥቅርን ሕዝብ በታችነትና የተለየ “ጎሳን” በላይነት “ሁኔታ” ለመፍጠር በተደረገ ሙከራ የአሚሪካ ሕዝብ በታላቅ ጀግንነት አንድነትንና እኩልነትን በዲሞክራሲ መስርታል:: የአሚርካንን ዲሞክራሲ በስራ ላይ ለማዋል በዙ አገሮች ሞከረው ነበር፤ ላቲን አሚሪካኖች የአሚርካንን ሕገ መንግሥት ለመከተል ሙከራ አድረገዋል ግን በስራ ላይ ሊውል አልቻለም፤ አውሮፓውያንም በተለያየ ግዜ ሙከራ አድርገዋል፤ የፊሊፕን መንግሥት ቃል በቃል ሕገ መንግሥቱን ወስዶ ነበር፤ ነገር ግን ዲሞክራሲ በስራ ላይ እንዲውል ከተፈለገ ሕብረተሰቡ እንደ አይኑ ቢሌን መጠበቅ አለበት፤ ይህ ከአልሆነ አምባ ገነን ተነስቶ ገደብ የሊሽ የሆነዉን ፍላጎቱን ሕዝብ ላይ ስለሚጭን “ዲሞክራሲን” በታላቅ ጥንቃቄ መጠበቅ የዜጋዎች ሃላፊነት ነው። አምባ ገነን አጥብቆ መዋጋት ለሰው ልጅ ነፃነቱና ክብሩ ነውና [ከሶወስተኛው ክፍል የተወሰደ]።

ይህ ከላይ የተጠቀሰው በሶወስተኛው ክፍል ቀርባል፤ ስለዚህ የተማላውን ጽሑፍ ለውይይት ለማቅረብ ከተፈለገ በሚያስፈልግበት ጊዚ ሊላክ ይቻላል።

ለተከብሩ ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር አቢይ አህመድ በተላከው ግልጽ ደብዳቢ ላይ እንደተጠቀሰው [የተላከዉን ደብዳቢ ይመልከቱ] ለለውጡ በመጀመሪያ ደረጃ አስፈላጊ ናቸው ከተባሉት ውስጥ ሕገ መንግሥትና የሕግ በላይነት ነው። ይህንን በተመለከተ የሕግ አርቃቂ ኮሚሽነር በአስቸካይ እንዲሰየም ነበር። እስከአሁን ድረስ የተወሰደ እርምጃ የለም፤ ስለዚህ አስችካይ እርምጃ መወሰድ አስፈላጊ ነው። የሕግ ባለማዮዎች ሕገ መንግሥቱን ከአረቀቁ  በሕዝብ ይጸድቃል። ይህ እንዳለ ሆኖ የኢትዮጵያ ሕዝብ ከምርጫ ቦርድ መምሪያ እስኪመጣ ድረስ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መውያየቱ ጠቃሚ ነው።

 1. ነጻ የሆነ የምርጫ ቦርድ፤ ጠቅላይ ሚንስትሩ ወይዘሮ ብርቱካን መደቅሳን ለምርጫ ቦርድ በሊቀ መንበርነት መምረጣቸው ትልቅ እርምጃ ነው። ሆኖም ነጻ ፍርድ ቢት ሳይኖር የሕግ በላይነት ሳይከበር ወይዘሮ ብርቱካን በተአምር የሚሰሩት ነገር አይኖርም፤ እዚህ ላይ መጠቀስ ያለበትና ለውጥን ማየት ያለብን ከአስተሳሰባችንና ከባሕላችን ጋር ነው፤ ለውጥ በግለሰብ በጎ ፈቃድ የሚስጥና የሚመጣ ነገር አይደለም። የወይዘሮ ብርቱካን መደቅሳና የዶር አቢይ አህመድ በጎ አስተሳሰብ ቀና ነው፤ ግን እላይ እንደተጠቀሰው በዓለም ታሪክ ሕገ መንግሥትና ዲሞክራሲ በግለሰብ ስጦታ አልመጣም፤ ሊመጣም አይችልም፤ ዲሞክራሲ የሚዋቀረው በስምምነት ነው። ለውጥ የየግለሰቡን አስተሳሰብና የፍላጎቱን ገደብ ሕግን ተቀብሎ መገደብ ይኖርበታል፤ የሕግ በላይነት ለምርጫ “ቅድመ ሁኒታ” ነው። ይህ ከአልሆነ ውጢቱ ያው የምናውቀው ነው፤ቢደመረም ቢቀነስም የሚያመጣው ለውጥ የለም።
 2. የፖለቲካ ፓርቲዎች ቢበዛ ከሶወስት መብለጥ የለበትም፤ በአሁኑ ግዚ የኢትዮጵያን ሕዝብ ሊያካቱቱ የሚችል የሴቶችድርጅቶች ነው፤ አንደኛ በድርጅት ደረጃ የኢትዮጵያ ሴቶች፤ የተከበሩ ወይዘሪት ብርቱካን መደቅሳ እናድሉት፤ “የነፃነት ሀውልት ነች” ስለዚህ የኢትዮጵያን ልዑላዌነትና ሰላም የማስጠበቅ የተለየ ችሎታ ስለአላቸው በማሕበር  ተደራጅተው የኢትዮጵያን የፖለቲካ ፓርቲዎች መምሪያ እየሰጡ ተመራጮችን ከሕዝብ ጋር ያዋያያሉ፤ “የኢትዮጵያ ሴቶች መልካም አስተዳደር፤ ሰብአዌ መብት፤ አንድነትና ሰላም ድርጅት” [Ethiopian League of Women for Democracy,  Huaman Rights, Peace and Unity] ተብሎ ቢሰየም የኢትዮጵያን ፖለቲካ ፓርቲዎች ሊያስተባብሩና በአገር ውስጥ ሰላም ሊያመጡ ይችላሉ፤ እንደ ኢትዮጵያ እናቶች በኢሕደግ መንግሥት ያለቀስና የተሰቃየ የለም፤ ልጆቻቸው በጅምላ ተገድለዋል፤  ልጃ ሬሳ ላይ እንድትቀመጥ ተገዳለች፤ መካን እንዲሆኑ ተገድዋል፤ አባቶቻቸው፤ ባሎቻቸው ታስረዋል፤ ተገድለዋል፤ ከሴቶች ሊላ የኢትዮጵያን ሰላምና የሰውን ልጅ ሰብአዌ መብት የሚያስጠብቅ ሊላ ሰው አይኖርም፤ የኢትዮጵያን አንድነትና ነፃነት ያስክብራሉ፤ ለፖለቲካ ፓርቲዎች ተምስሊት ይሆናሉ።
 3.  በፖለቲካ ፓርቲ ደረጃ አንደኛ፡  የወጣቱ ትውልድ [በመከራ ተፈትኖ የተወለደው መልካሙ ትውልድ] “የኢትዮጵያ ወጣቶች ዲሞክራስዊ ፓርቲ” [Ethiopian Youth Democratic Party] ተብሎ ሊጠራ ይችላል፤ አዲሱ ትውልድ ያሳለፈው መከራና ስቃይ ከፍተኛ ስለሆነ የአንድነትንና የሰላም አስፈላጊነት ጠንቅቆ ያውቃል፤ ሰብአዌ መብትንም ያከብራል፤ እሱ እንደተዋረደው ማንም እንዲዋረድ አይፈልግም። በዚህ የፖለቲካ ፓርቲ ውስጥ የወጣቱን የኢኮኖሚና ማሕብረሰባዊ ፍላጎት እንዲማላ እሰራለሁ የሚል ሁሉ አባል ሆኖ ለምርጫ መቅረብ ይሽላል።
 4. ሁለተኛ “የኢትዮጵያ ገበሪዎች አንድነት ፓርቲ” [Ethiopian Union Farmers Party] የገበሪውን ጥቅምና መበት አስከብራለሁ የሚል ገበሪዉን ወክሎ መመረጥ ይችላል።
 5.  ሶወስተኛ “የኢትዮጵያ የተባበሩት ሰራተኞች ፖለቲካ ፓርቲ” [ Ethiopian United Labor Party] የሰራተኛዉን መብትና ጥቅሙን አስጠብቃለሁ የሚል አባል በመሆን መመረጥ ይችላል። የእነዚህ ሶወስት የፖለቲካ ድርጅቶች [ፓርቲዎች] ፍላጎት በሚገባ ተተንትኖ መጻፍ ይኖርበታል [party platform]፤ አሁን የፖለቲካ ፓርቲዎች ነን የሚሉ ሁሉ በእነዚህ ክፍል ተካተው በአገር ደረጃ መንቀሳቀስ ይችላሉ፤ ከሶወስት አንዱን መርጠው ፕሮግራማቸዉን አስተካክለው የአገሩን የመኖሪያ ሕግ ተቀብለው መመረጥም መምረጥም የሚችሉበትን መንገድ ሊያስተከክሉ ይገባችዋል። ይህንን በተመለከተ የምርጫ ቦርድ ሰፋ ያለ መግለጫ ማዘጋጀት አለበት፤ ተወዳዳሪዎች ለሶወስቱም የመንግሥት ክፍል ሊወዳደሩ ይችላሉ፤ ይኸውም “የሕዝብ መምሪያ ምክር ቢት”“የሕዝብ መወሰኛ ምክር ቢት” እና  “የአገሩን መሪ” [ፕሪዚዳንት] ይሆናል። ለፕሪዚዳንነት ሁለት ከፍተኛ ድምጽ ያመጡ ተወዳዳሪዎች በአገር አቀፍ ደረጃ ለምርጫ ይቀርባሉ። ለዚህ ሁሉ የምርጫው ቦርድ በዝርዝር መምሪያ ማዘጋጀት ይኖርበታል። በሕገ መንግሥቱ በዝርዝር ስለተመራጮና ስራና የስራ ግዲታ ይደነገጋል።
 6. በሕገ መንግሥቱ በጎሳና በሃይማኖት መደራጀት ክልክል መሆን ይኖርበታል።
 7. አሁን ያለው የክልል መንግሥት እንዲት እንደሚካለል ሕዝብ ተውያዮቶ መወሰን ይኖርበታል፤ በጎሳና በሃይማኖት የኢትዮጵያ መሪት እንዳይካለል በሕዝብ ውይይት ተወስኖ በሕገ መንግሥቱ የክልል መንግሥት ክልክል መሆን አለበት።
 8. የኢትዮጵያ ሕዝብ የአሚሪካንን ሕገ መንግሥትና ዲሞክራሲ በትኩረት ተመልክቶ በስራ ላይ የሚውልበትን ዘዲ መመካከር አስፈላጊ ነው፤ ከእንግሊዝ የተወሰደው የጠቅላይ ሚኒስትር አመራር ለኢትዮጵያ አይሰራም፤ በሕዝብ የሚመመረጥ የሕዝብ ምክር ቢት፤ የፍርድ ቢት፤ በፕሪዝዳንት የሚመራ አመራር ለኢትዮጵያ መልካም አስተዳደር ሊያመጣ ይችላል። ይህንን በተመለከት ሰፋ ያለ ውይይት ያስፈልጋል።
 9. ለተመራጮች የግዚ ገደብ ማድረግ፤ ግዲታቸውንና ኃላፊነታቸውን በሕገ መንግሥቱ ማካተት ያስፈልጋል።
 10.  በሶወስት ክፍል የተጠቀሱትን የፖለቲካ ፓርቲዎች ለአካባቢው ሕዝብ አቅርቦ ማስተዋወቅና መወያየት፤ ሕዝብ ጥቅሚንና እነኒትን ያስክብራል የሚልዉን ድርጅት እንዲመርጥ መብቱን ማሳወቅ፤ ይህንን ድርጅት ወክለው ለመመረጥ የሚያስችላቸዉን ሕግ ማውጣት፤ በሚመረጡበት አካባቢ የንዋሪነት ዘመን መተመን። የእድሚና የስነ ምግባር መስፈረት በግልጽ ማስቀመጥ።
 11. የቀብሊያቸውን አስመራጭ ኮሚቲ ደንብና ስርዓት በግልጽ ማሳወቅ።
 12. የውጭና የአካባቢውን የምርጫ ታዛቢዎች ደንብና ስርዓት በግልጽ ማሳወቅ።
 13. በሕገ መንግሥቱ መሰረት የምርጫውን ቀን፤ ግዚና ስዓት በግልጽ ለሕዝብ ማሳወቅ።
 14. የምርጫ ምዝገባዉን ቀን፤ግዚና ስዓት በግልጽ ማሳወቅ።
 15. ምርጫ በሚካሂድበት ግዚ መራጮች ተረጋግተው እንዲመርጡና ምንም አይነት ችግር እንዳይፈጠር አስፈላጊውን እርምጃ መውሰድ።
 16. በምርጫ ቀን ተመራጮች ምረጡኝ የሚል ምንም አይነት መልክት በየትኛውም ቦታ ማደረግ እንደማይችሉ ሕጉንና ስርዓቱን ለሁሉም ወገን ማሳወቅ።
 17. የቀበሊው አስመራጭ ኮሚቲ ሕዝቡን በነፃ ሆኖ የመምረጥ መብቱን ማስተማር።
 18. በሕገ መንግሥቱ መሰረት ምርጫው እንደተከናወነ ለበላይ አካል ለሆነው ለብሒራዊ ምርጫ ቦርድ ማሳወቅ።
 19. ምርጫው ከመደረጉ በፊት ብዙ “ቅድመ ሁኒታዎች” ያስፈሉጉታል፤ ነፃ የምርጫ ቦርድ፤ ነፃ ፍርድ ቢት፤ በኢትዮጵያ ሕዝብ የጸደቀ ሕገ መንግሥት፤ እነዚህን “ሁኒታዎች” ለመፈጠር ብዙ ግዚ ይጠይቃል፤ በተባለው ሁለት ዓመት ውስጥ ሊከናወን ስለማይችል ኢሕደግ በሰጠው ሁለት ዓመት ላይ 3 ዓመት ጨምሮ “ቅድመ ሁኒታዎችን” ማስቀመጥ አስፈላጊ ነው። ሕዝብ ይህንን ጉዳይ ከምርጫ ቦርድ ጋር ተነጋግሮ ግዚውን ማረዘሙ ግዲታ ነው።
 20. እነዚህ ከዚህ በላይ የተዘረዘሩት ከብሒራዊ ምርጫ ቦርድ ከሚመጣው መምርያ በተጨማሪ እንዲረዳ ተብሎ ነው።  የአስተዳደር ክፍሉ ከማዕከላዊ መንግሥት የተለየ ቀብሊዉን የሚያስተዳድርበት ሕግ መኖር አለበት፤ ለምሳሊ የቀበሊው ናሪ ለምክር ቢት አባልነት መወዳደር ቢፈልግ የቀበሊዉን ሕግ ማማላት ይኖርበታል፤ በስነ ምግባር ብቁነት፤ ቢያንስ ሰባት ዓመት[?] በቀበሊው የኖረ ሲሆን ሊላ የሰብአዊ መብቱ የማይጣስና በማዕከላዊ መንግሥት የተጠበቀ ይሆናል።

ይህ ከዚህ በላይ የተጠቀሱትን መርሐ ግብር የኢትዮጵያ ሕዝብ በየአውራጃው፤ በየወረዳው፤ በየምስሊነው፤ በየቀቢለው መወያየት ያስፈልጋል፤ ይህንን ውይይት ለማካሂድ ሕዝቡ የማንንም ፈቃድ አያስፈልገውም፤ መግሥትን በሕዝብ ለሕዝብ የሚመሰርተው ሕዝብ ነው፤ የአገሩን ሕግ የሚደነግገው የሕዝብ ተወካይ ነው፤ ዲሞክሪሲን የሚመሰርተው ሕዝብ ነው፤ ለምሳሊ የአሚሪካ ሕገ መንግሥት የመጀመሪያው ምዕራፍ የሚለውን እንመልከት፤ “የሕገ መንግሥቱን ሕግ የማውጣት ስልጣን ያለው ሕዝብ የመረጠው የምክር ቢቱ አባል ብቻ ነው” ይላል። ይህም ማለት መንግሥት የሚመሰረተው በሕዝብ ነው፤ ሕግ የሚወጣው በሕዝብ ነው። በሕግ በላይነት ወይም በሕዝብ በላይነት ዲሞክራሲ ይጠበቃል። ሕዝብን በማሰር፤ በመግደል፤ ከሚኖረበት በማፈናቀል፤ ዘር በማጥፋት፤ሃብት በመዝረፍ፤ 70 ቢሎዮን ዶላር ከአገር በማሽሽ ዲሞክራሲ አይመሰረትም። የወያኒ ዲሞክራሲ መስረቅና መዝረፍ ነው። ይህንን ለማስቆም መንግሥት በሕዝብ ለሕዝብ ብለህ ቆርጠህ መነሳት አለብህ፤ ከአንተ ሊላ ማንም ዲሞክራሲ ሊያመጣልህ አይችልም። ማንንም ማምለክ አይኖርብህም፤ አንድ ሰውን ማምለክን ስትጀምር መታሳር፤ መገደል፤ መፈናቀል፤ መናቅ፤ መሰደድ አብሮ ይጀመራል። ሕግን በባላይነት ስታይ፤ የወግንክን ስብአዊ መብት ስታከብር፤ ስታስከብር በነፃ መንፈስ ትሞላለህ፤ አገርህ ፍትህና የሚያልቅ ሰላም፤ ብልጽግና፤ ማርና ወተት እንደ ውሀ የሚፈስባት አገር ትፈጥራለህ፤ አይዞህ እንደምንም ብልህ ተነሳ፤ ሊላ ሰው እንዲያነሳህ አትተጠብቅ።

ክፍል አራትን ለማጠናቀቅ ያህል ስለ ጎሳ አጠር ያለ ውይይት ማድረግ ያስፈልጋል፤ በኢትዮጵያ ረጅም ግዚ ታሪክ የአንድ ጎሳ በላይነት በዚህ አይነት “ሁኒታ” ተደርጎ አይታወቅም፤ ጎሳዎችን በብሔር ከልሎ ራሱን በፊደራል አስተዳደር ስም ሰይሞ የጎሳዎች አስተዳዳሪ በመሆን በዓለም ታሪክ ውስጥ ተፈጽሞ የማያውቅ ውንጅልና የፈጽመ ከሰው ያልተፈጠረ ይመስል በሰው ልጅ ይህ ነው ሊባል የማይችል ውንጅልና ፈጽማል፤ የኢትዮጵያ ሕዝብ ይህንን ወንጀል በአገራችን ላይ ሁለትኛ እንዳይፈጸም መፋረድ ታሪካዊ ግዲታው ነው፤ ይህ በይቅርታ ሊትለፍ አይገባውም፤ የተዘረፈዉን ገንዘብ፤ ንብረት፤ የተነጠቀውን የከተማ መሪቶች፤ ተዘርፈው የተወሰዱትን የእንድስትሪ ሃብቶች፤ በፍርድ ቢት ወደ ባለቤቱ እንዲመለስ ማደርግ፤ በሕዝብ ገንዘብ የተከማቸውን የትግራይ ልማት ድርጅትን $12 ቢሊዮን ዶላር የሚገመተውን ሃብት ወደ መንግሥት እንዲገባ ማድረግ፤ ከዲያስፖራው ጋር በመተባበር እውጭ የተቀመጠውን ገንዘብ፤ በንብረትነት በተላያዩ ግለሰቦች የተያዙ ቤቶች፤ የንግድ አቃማት፤ በዓለም አቀፍ ሕግ መሰረት ማስመለስ፤ የሕዝብ መንግሥት ሳይመረጥ ምንም ዓይነት የሕዝብ ኢኮኖሚክ ተቃማዋት ወደ ግል ንብረትነት እንዳይዘዋወር ሕዝብ ማደረግ አለበት፤ እንዚህን ሁሉ በተመለከተ ሕዝብ ከኢሕደግ ጋር እየተወያየ ማስፈጸም አለበት፤ ጋዜጠኞችና የኢትዮጵያን ፖለቲካ ተኝታኞች እንዚህን ሁሉ በአጀንዳቸው ላይ አድርገው ሊወያዩበት ይገባል።

 

በመጨረሻም የጎሳን በላይነት የኢትዮጵያ ሕዝብ አጥብቆ መቃወም አለበት፤ በጎሳ የተደራጁ ኃይሎች አላማቸው የጎሳቸውን ድህንነት ከማስጠበቅ በላይ መሂድ የለበትም፤ ማንም ጎሳ ቢሆን ከሊላው ጎሳ የሚበልጥበት ምክንያት የለም፤ በ27 ዓመት ውስጥ ያየነውን “ጎሰኛነት” ሁለተኛ አገራችን ውስጥ ቦታ እንደሊለው የኢትዮጵያ ሕዝብ መስማማት አለበት። በተጨማሪ ለጠቅላይ ሚንስትሩና ለወይዘሮ ብርቱካን መተላለፍ ያለበት መልዕክት ምርጫውን በተመለከተ ነው፤ አጀማመሩ እጅግ በጣም ጥሩ ነው። ወይዘሮ ብርቱካን ከባድ ሃላፊነትን ተቀብለዋል፤ ይህንንም ሃላፊነት በክብር እንደሚያከናውንት ምንም ጥያቂ የለም፤ ነገር ግን ጠቅላይ ሚንስትሩ የሕገ መንግሥቱን አርቃቂ ኮሚሽነር በአስቸካይ ሰይመው ሕገ መንግሥቱ ተረቆ በብሒራዊ ሽንጎ [በሕዝብ] መጽደቅ ይኖርበታል፤ ይህ ከአልሆነ የወይዘሮ ብርቱካን ስራ ታጥቦ ጭቃ መሆን ነው፤ የነፃ ምርጫ ቦርድ፤ ነፃ የሆነ ፍርድ ቢት በሊለበት “ሁኒታ” የወይዘሮ ብርቱካን መደቅሳ ስራ ሊሳካ አይችልም። ከላይ እንደተጠቀሰው በውጭ አገር ያሉ ኢትዮጵያውያን ከወይዘሮ ብርቱካን መደቅሳ ጋር በመተባበር ዘመናዊ የሆነ ኢሊትሮኒክስ የምርጫ ሳጥን የምናገኝበትን ዘዲ ማማቻቸት ይኖርብናል።

መልካም ውይይት። አዲስቱ ኢትዮጵያ በሕዝብ ለሕዝብ ሆና በክብር ለዘለዓለም ትኑር።

Reference:

 1. Magna Carta, 1215
 2. English Bill of Rights
 3. Declaration Indepdence
 4. The United States Constituion
 5. Sirak Hiruy H. Sllasie: Rase Las: The Prince of Abysinia
 6. Philosophers who influenced the writing of the American Connstitution:
 7. a) Jean-Jacques Rousseau [1712-1778].
 8. b) Thomas Hobes [1588-1679]
 9. c) John Lock [1632 -1704]
 10. d) Voltaire [1694-1778]
 11. e) Montesquieu [1689-1755]

 

7, Zer’a Ya’qob [see the Nile Valley civilization፡ A Histriographical Commentary on Ancient Africa,

8, Stephen Oppenheimer [see the Nile Valley Civilizatio………….]

9. Amo West Afrian Philospe

1 COMMENT

 1. This is very educational. I hope this help Ethiopians understand the truth and liberty themselves from fictitious hateful teachings.

  Thank you for your work!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here