Home News and Views የባህር ዳሩ ምዕራብ እዝና የጭልጋው 24ኛ ክ/ጦር ዋና አዛዦች ተቀየሩ!

የባህር ዳሩ ምዕራብ እዝና የጭልጋው 24ኛ ክ/ጦር ዋና አዛዦች ተቀየሩ!

የማዕከላዊ እዝ አዛዥ የነበረው አስራት ቢናሮ (ደቡብ) በከፍተኛ ሙስና እና ወንጀል የሚጠረጠረውንና ከቅማንት ኮሚቴዎች ጋር በመወገን አማራን ሲያስጨፈጭፍ የነበረውን ዮሐንስ ወልደ ጊወርጊሥ(ህውሃት) ተክቶ የምዕራብ እዝ አዛዥ  ሆነዋል።

ብርጋዴር ጀነራል ፈቃዱ ፀጋየ (አማራ) የ24ኛ ክ/ጦር አዛዥ ሆነው ሲሾሙ ብርጋዴር ጀነራል አበበ በየነ (ኦሮሞ) ደግሞ የ12ኛ ክፍለ ጦር አዛዥ ሆኖ ጅማ ተመድበዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ትግራይ የነበረው 22ኛ ክ/ጦር ወደ አሦሣ ተቀይሮ ጉዞ ጀምሯል። ይህንን ሰራዊት የጫኑ ከ30 በላይ አውቶቡሶች በመርዓዊ አልፈዋል። 22ኛ ክ/ጦር የወለጋ አካባቢን የፀጥታ ችግር ለመፍታት የተዛወረ ሲሆን ከኤርትራ ጋር ሰላም ስለተፈጠረ የሰሜኑ ክፍል ጠቅልሎ የያዘውን የሰውና የመሳሪያ ሀይል ወደመሃል አገር እንዲመልስ ሊደረግ ነው!

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here