Home News and Views “የጎሳ ድርጅቶች”- በቀጣዩ ምርጫ የብርትኳን ራስ ምታቶች!

“የጎሳ ድርጅቶች”- በቀጣዩ ምርጫ የብርትኳን ራስ ምታቶች!

ምርጫው ይራዘም? ወይስ አይራዘም?

የጎሳ ድርጅቶች በሙሉ ምርጫው መራዘም የለበትም እያሉ ነው። በተቃራኒው  ብሄራዊ(አገር አቀፍ) ድርጅቶች ምርጫው መራዘም አለበት ሲሉ ይሞግታሉ።

በኔ እይታ የሃገራችንን ነባራዊና ወቅታዊ ሁኔታ ያገናዘበው አመለካከት በብሄራዊ(አገር አቀፍ) ድርጅቶች የሚገፋው አመለካከት ነው። ለዲሞክራሲያዊና ነጻ ምርጫ እውን መሆን የህግ የበላይነት መስፈን፤ የዜጎች መብት መከበር፤ ባጠቃላይ የሰላምና መረጋጋት እውን መሆን ግድ ነው።

ይህ እንዲሆን ደግሞ የፌዴራል መንግስቱ ህግ አስፈጻሚ ተቋማት በመላው አገሪቷ ውስጥ ያለውን ህገ-ወጥ እንቅስቃሴ፤ የመብት ጥሰትና የሰላም መደፍረስን የሚቆጣጠሩበት ቁመናና አቅም ሊኖራቸው ይገባል።

የምርጫውን ሂደት የሚቆጣጠረውና የሚመራው ብሄራዊ ምርጫ ቦርድም ቢሆን ሃላፊነቱን በተገቢው ሊወጣ የሚችለው የህግ አስፈጻሚ ተቋማቱን አስተማማኝ ደጀንነት ሲያገኝ ብቻ ነው።

የወቅቱ የሃገራችን ነባራዊ ሁኔታ ደግሞ ይህን የሚያመለክት አይደለም። በሃገሪቷ የተለያዩ ክልሎች የሰላም መደፍረስ ፤ የዜጎች መፈናቀል፤ ያለመረጋጋት እየተስተዋለ ነው። መንግስት በታጋሽነት የሚያልፋቸው ህገ-ወጥ እንቅስቃሴዎች እየበረቱ እንጂ እየቀነሱ አይደለም።

መንግስት ይህን አለመረጋጋት በመቆጣጠር ለምርጫ ምቹ ሁኔታን ለመፍጠር ምን ያህል ግዜ ይበቃዋል የሚለውን ጥያቄ በትክክል መመለስ ባይቻልም፤ ከችግሮቹ ውስብስብነትና ብዛት አኳያ ለምርጫው የቀሩት 16 ወራት በቂ እንደማይሆኑ መገመት ከባድ አይሆንም።

በተከታይ 16 ወራት መንግስት ሰላምና መረጋጋትን አስፍኖ ለምርጫው ምቹ ሁኔታን መፍጠር ቢቻል እንኳ ለምርጫው ቅድመ ዝግጅት ለማድረግ ሌላ ከ16 ወራት በላይ ያስፈልጋል። ይህ ማለት ደግሞ ምርጫው ቢያንስ ለ3 አመት ማራዘሙ የግድ ነው ማለት ነው።

የጎሳ ድርጅቶች ምርጫው እንዳይራዘም ለምን ፈለጉ፦

የሃገሪቷ ሰላምና መረጋጋት ግድ ሳይላቸው ምርጫው በግዜው ማለትም ከ16 ወራት በኋላ መደረግ አለበት የሚሉት የጎሳ ድርጅቶች ለዚህ አቋማቸው እንደ ምክንያት የሚጠቅሱት፤ ምርጫውን ማራዘም ህገ-መንግስቱን መጣስ ይሆናል የሚል ነው።

እንደኔ እይታ ግን ትክክለኛ ምክንያታቸው ይህ አይደለም። የጎሳ ድርጅቶች የጋራ የሆነው ባህሪያቸው እንወክለዋለን ለሚሉት ህዝብ ጠንካራ ጠላት ማዘጋጀት ነው።ይህ ጠላት ደግሞ ኢትዮጵያዊው ብሄርተኛ ነው። ይህን ማድረግ ካልቻሉ ጎሳቸውን ሊያሰባስቡ አይችሉም። የትግል ስልታቸውም ጎሳቸውን ካዘጋጁለት ጠላት ( ከኢትዮጵያዊው ብሄርተኛ) ጋር ሁሌ በቅራኔ ውስጥ እንዲኖር ማድረግ ነው። ጎሳቸውን በቅራኔ እስከጠመዱት ድረስ በምርጫ እንሸነፋለን ብለው አይሰጉም። ምክንያቱም የጎሳቸው ምርጫ እነሱና እነሱ ብቻ እንዲሆኑ አድርገዋልና ነው።

ለዚህም ነው የጎሳ ድርጅቶች በሃገሪቷ የሰፈነው አለመረጋጋት ግድ ሳይላቸው ምርጫው እንዳይራዘም የሚሞግቱት። ሰላምና መረጋጋት ለጎሳ ድርጅቶች ጥሩ የጨዋታ ሜዳ አይደለም።ሰላም ያለው ህዝብ ማሰብ ይችላል፤ የሚያስብ ህዝብ ደግሞ ከደምና አጥንት ቆጠራ ተሻግሮ ጥሩን ከመጥፎ ይለያል።ይህ ማለት ደግሞ ህዝብ በሃሳብ ዙሪያ እንጂ በደም መሰባሰብን ይጠየፋል።

የጎሳ ድርጅቶች የጋራ ባህሪያት

ይህን ትንታኔ መሬት አውርደን ከሃገሪቷ ወቅታዊ ሁነቶችና ክስተቶች ጋር አጎዳኝተን እንየው። ኦነግ፤ ህወሃትና አብን ሶስት የተለያዩ ብሄሮችን እንወክላለን የሚሉ ድርጅቶች ቢሆኑም በበርካታ ጉዳዮች ላይ ግን አንድ አይነት አቋም ያራምዳሉ።

  1. ሶስቱም የጎሳ ድርጅቶች ምርጫው እንዳይራዘም ይፈልጋሉ።
  2. ሶስቱም የጎሳ ድርጅቶች አርበኞች ግንቦት ሰባትንና መሰል ህብረ ብሄር ድርጅቶችን የጎሳቸው ጠላት አድርገው ፈርጀዋል።
  3. ሶስቱም በአሁኑ ወቅት የሃገሪቷን ሰላም ለማደፍረስ ሌት ተቀን እየሰሩ ናቸው።

ከነዚህ ተጨባጭ ሁነቶች ተነስተን ስንመረምር የምንደርስበት ሃቅ የጎሳ ድርጅቶች ህልውና የተመሰረተው ኢትዮጵያዊነትን የሚያቀነቅኑ ህብረ ብሄር ድርጅቶችን እንወክለዋለን ከሚሉት ህዝብ ጋር በማጣመድ ላይ መሆኑን ነው። ለዚህም ነው የኦነግ ደጋፊዎች አግ7ን በኦሮሚያ ክልል አንይ እያሉ የሚገኙት። ለዚህም ነው አብን የተሰኘው ድርጅት ደጋፊዎች በተመሳሳይ በአማራ ክልል አግ7 እግሩ አይረግጥም የሚሉት። አግ7 ትግራይ አልሄደም እንጂ ቢሄድ ኖሮ የሚጠብቀው ነገር ከዚህ የተለየ አይሆንም።

የጎሳ ድርጅቶች – የምርጫ ቦርድ ፈተና

ከላይ ለመግለጽ እንደሞከርኩት በብሄራዊ ደረጃ የሚደረገውን ምርጫ ፍትሃዊና ዲሞክራሲያዊ ለማድረግ የዜጎች መብትና የህግ የበላይነት መከበራቸው የግድ ነው። የትኛውም የፖለቲካ ድርጅት በፈለገበት ክልል ሄዶ እንዲወዳደር ሙሉ መብት ሊኖረው ይገባል። ማንም ግለሰብ የፈለገውን ድርጅት የመምረጥ መብቱም ሊጠበቅለት ይገባል። ውድድሮችም በሃሳብና በአመለካከት ፍትጊያ እንጂ ሽመል መዞ በክልሌ አትድረስ በሚል አምባ ጓሮ ሊሆን አይገባውም፡፤

ምርጫውን የሚመራው ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ የሰለጠነ የፖለቲካ ውድድር እንዲከናወን ማድረግ የሚችለው የፌዴራል መንግስት ህግ አስፈጻሚ ተቋማትን ሙሉ ድጋፍ ሲያገኝ ብቻ ነው። ይህ እውን ሊሆን የሚችለው ደግሞ የፌዴራል መንግስት ህግ አስፈጻሚ ተቋማት የሃገሪቷን ሰላምና መረጋጋት ማስጠበቅ እስከቻሉ ድረስ ብቻ ነው።

ከምርጫው በፊት የሃገሪቷ ሰላምና መረጋጋት መረጋገጥ አለበት የሚሉት ወገኖች ትክክል ናቸው የምለው ለዚህ ነው።

አሁን እንደሚታየው የታጠቁ ኃይሎች በየክልሉ ያሹት እያደረጉ፤ የጠሉትን እያፈናቀሉ ባሉበት ሁኔታ ምርጫ ማድረግ የማይታሰብ ነው። የፌዴራል መንግስቱ ህግ አስፈጻሚ ተቋማት ከየክልሉ የጸጥታ ኃይሎች ጋር በጥምረት እስካልሰሩ ድረስ ምርጫው ቅርጫ እንጂ ምርጫ አይሆንም።

የጎሳ ድርጅቶች ለምርጫ የሚያደርጉት እንቅስቃሴ በአብዛኛው በክልላቸው አጥር የተወሰነ በመሆኑ በአገር አቀፍ ደረጃ የሚከናወነውን የምርጫ ሂደት ለሚመራው ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ዋንኛ ፈተና ናቸው።ምክንያቱ ደግሞ ህብረ ብሄር ድርጅቶች ለምርጫ የሚያደርጉት እንቅስቃሴ ክልል ዘለል በመሆኑ በየክልሉ ከከተሙት የጎሳ ድርጅቶች የሚገጥማቸውን ህገ-ወጥ ፍጥጫና ወከባ ነው። ይህን ወከባ የማስቆም ሃላፊነት የወደቀበት ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ የፌዴራል መንግስትን የፈረጠመ ክንድ በደጀንነት ካልያዘ ፈተናው ያይላል ያልኩትም ለዚህ ነው።

ከዚህ በመነሳት የምንደርስበት ድምዳሜ ምርጫው የግድ መራዘም አለበት የሚል ሊሆን ግድ ነው። እስከ መቼ? ለሚለው ጥያቄ መልሱ፦ ፌዴራል መንግስት የሃገሪቷን ሰላምና መረጋጋት፤ የህግ የበላይነትና የዜጎች መብት መከበርን እስኪያረጋግጥ የሚል ይሆናል።

በርግጥ ከቅራኔ ባህር ውጭ መዋኝትም ሆነ መተንፈስ የማይችሉት የጎሳ ድርጅቶች መንግስት ሰላም ለማስፈን የሚያደርገውን ጥረት ለማክሸፍ ሌት ተቀን እንደሚተጉም የሚጠበቅ በመሆኑ የመንግስት ጥረትና ስኬት በግዜ ገደብ ለማስቀመጥ ይቸገራል ።

ይሁን እንጂ የፈጀውን ግዜ ፈጅቶ ሰላም ወዳዱ ኢትዮጵያዊ ከለውጥ አራማጁ ኃይል ጎን በመቆም ለዘመናት ያጣናቸውን ፍትህ፤ ዲሞክራሲና ሰላምን በአስተማማኝ ለማስፈን መሰረት የሚጥለውን ዲሞክራሲያዊ ምርጫ እውን እንደሚያደርግ እምነቴ የጸና ነው።

ሰላማችንን አፍጥንልን
ልቡ ለተደፈነም ማስተዋሉን ስጥልን!

ቸር እንሰንብት

2 COMMENTS

  1. TPLF is in Tigray waiting for Gerd dam to start getting filled with water hoping their plan comes true and the GERD dam will collapse flooding some Amara and some Benisgangul people bringing Benishangul’s and Amara’s fertile soil to Tigray. At the time of fertile Tigray TPLF is intending to declare referendum. TPLF threatened Engineer Simegnew that they will kill him along with his loved ones including his children if he told about the low safety standard METEC put in the GERD dam foundation. Engineer Simegnew decided to shoot his own head to take his own life so his loved ones live.The GERD foundation is intentionally made below safety standard hoping the dam collapses and flood water with fertile soil of Benishangul and Amara’s fertile soil will flow to Tigray. The plan is to make Tigray covered with fertile soil so Tigray can get to be self sufficient with food and in the process take out as many Amara and Benishangul people life to help with TPLF’s ethnic cleansing so Tigray officials can live with no worry of prosecution for their countless crimes .

  2. There is no political class in USA. Nanci Pelosi And Donald J. Trump are politicians elected democratically with different views from different class that co-exist. In Tigrai TPLF is the only political class..Even in the rest of Ethiopia there is no single political class anymore.People everywjere outside Tigrai are having exposure to the 20th century.There has been no electoral board institution to cultivate democracy for the last 28 years, Assefa Birru designed the institution to be TPLF’s playground. Because of Assefa Birru sellout Amara Ethiopians were unable to hold free elections so far, since TPLF thought Abay Tsehaye was the only political class for the last 28 years.For few years since 1991 TPLF thought that Meles Sebhat Abay & Co. was the only political class, times changed now even TPLF is not a class, actually TPLF seems to be slowly but surely in the process of learning how to exist with other politicians (OLF) eventhough TPLF is full of thick headed timkhetegna cadres that are determined to cheat Tigrayan people out of our right to human dignity .Tigraians need help since TPLF is fully operating in Tigrai terrorizing us back into the 5th century right now in the 2oth century.People are starving weak powerless in Tigrai right now.

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here