Home News and Views በመለስ ሞት ስቀሃል ተብሎ ከዳኝነት ስራው ተባሮ ወደ ግብርና የገባው ብዙአየሁ

በመለስ ሞት ስቀሃል ተብሎ ከዳኝነት ስራው ተባሮ ወደ ግብርና የገባው ብዙአየሁ

ይህ  ጋቢ ለብሶ ራሱን ሸብ አድርጎ በፎቶ ግራፍ የምታዩት ወንድማችን ብዙአየሁ ታዬ ይባላል። የትውልድ ቦታው እነብሴ-ሳር ምድር ወረዳ (ጎጃም)ይዝማ ቀበሌ ነው።

ብዙአየሁን የአገኘሁት ለስራ ወደትውልድ ቦታው በሄድኩበት ጊዜ ነው።በ2001ዓ.ም ከመቀሌ ዩኒቨርሲቲ በህግ በመጀመሪያ ዲግሪ ተመርቋል። በ2002 እና በ2003 ለሁለት ዓመት ያህል በባህር ዳር ለህግ ሙያ ስራ የሚያበቃውን ስልጠና ተከታትሎ አጠናቋል። በአጠቃላይ ብዙአየሁ ለ18 አመት ያህል በትምህርት ላይ ቆይቷል።

በ2004 ዓ.ም በምስራቅ ጎጃም ዞን ጎንቻ ሲሶ እነሴ ወረዳ ግንደ-ወይን ከተማ ፍትህ ጽ/ቤት አቃቤ ሕግ ሆኖ መስራት ጀመረ።

ብዙአየሁ ለእውነትና ለፍትህ የሚወግን አድልኦን የሚፀየፍ ጎበዝ ጀግና ልጅ ነው፤ፍርሃት የሌለው እውነትን በአደባባይ ደፍሮ የሚናገር ቢኖር ብዙ መከራና ግፍ የአየው ብዙአየሁ ነው።

አቃቢ ሕግ ሆኖ ሲሰራ የሚያስተውለውን ችግርና የመብት ጥሰት በአደባባይ ደፍሮ ማጋለጥና መናገሩ በወቅቱ በነበሩት የወያኔ አመራሮች ጥርስ ሊነከስበት ችሏል።

በተለይም ደግሞ መለስ ዜናዊ ሲሞት ስቀሃል ብሎም በስልክ ደውለህ እንኳን ደስ ያላችሁ ብለሃል ተብሎ ከፍተኛ የበቀል ቂም ተይዞበት ሲሰራበት ከነበረው ቦታ ያላግባብ በቅጣት በ2006 ዓ.ም ወደ ቢቡኝ ወረዳ ሄዶ እንዲሰራ ተደረገ።

ብዙአየሁ ምንም ሳይል ቢቡኝ ሄዶ ስራውን መስራት ጀመረ። ለምን ሳይል ስራውን መስራቱን ቢቀጥልም የበላይ አለቆቹና ካቢኔዎች ሴራቸውን አልተውለትም፤ያዋክቡት ጀመር። አቃቢ ሕጉ ለፍትህ የሚሰራው ብዙአየሁ ለራሱ ፍትሕን አጣ።

በሚገርም ሁኔታ በ2007 ዓ.ም መልሰው ቀድሞ ሲሰራበት ወደነበረበት ቦታ -ግንደወይን መልሰዉ አመጡት።አሁንም ብዙአየሁ ጓዙን ሸክፎ ወደ ግንደወይን መጥቶ ስራውን ጀመረ።
በቀለኛው ስርዓት ብዙአየሁን ትህሳስ 27/2008 ዓ.ም ከስራው በግፍ አባረረው።
እናም ብዙአየሁ ያላግባብ ከስራ ገበታው ከመባረሩም በላይ የደረሰበት የስነ ልቦና ስብራት እጅጉን ያማል።

ብዙአየሁ አሁን በከፋ ሁኔታ ላይ ይገኛል፤ሲያዩት ያሳዝናል ፤ሆድን ያንቦጫቡጫል፤እኔ በአካል አይቸዋለሁ ፤ከአንደበቱ ሁሉን ነገሩ ሰምቻለሁ። አሁን የሚኖረው ከደካማ ቤተሰቦቹ ጋር የግብርና ስራ እየሰራ ነው።

እናም ፍትሕ ለተረሳው ጀግና ብዙአየሁ ታዬ!!!!
ያላግባብ ከስራቸው የተባበሩ ወደ ስራቸው እየተመለሱ ስለሆነ ብዙአየሁም ወደስራው ይመለስ ዘንድ ለሚመለከታቸው ሁሉ በማድረስ እንተባበረው።በተለይም ደግሞ በጉዳዩ ላይ እውቅና ያላችሁ የእርሱ የቅርብ ጎደኞቹ እባካችሁ የሚቻላችሁን ሁሉ ታደርጉ ዘንድ አደራ እላለሁ።

Shegaw Dagnew

2 COMMENTS

 1. Is the real Meles really dead? Legese died but many say the now “Getachew Assefa” is the real Meles This man was a victim of huge physical loss during the pre1991 civil war,at the time of his physical loss in the jungle he only got poor medical surgery procedure that put together his arms and hands all crooked bent rotated the wrong way, he was paralyzed for many years after that. There is a possibility he might still be paralyzed. He was seen only at few funerals in early 1990’s. In early to mid 1990’s he got an expensive medical reconstruction who many believe included facial plastic surgery, he was never seen in public after that even if he did appear in public there is huge chance no one recognized him since all his arms hands face was reconstructed. The ones who seen him before the reconstruction procedures say he looked very much like Meles (Legesse) Zenawi with same goatie and mustache the resemblance was detected by many. Some even said this man the now AKA Getachew Assefa is the real Meles, the real Meles that everyone thought was dead killed by derg.Many say he wasn’t dead he just was physically dismembered but survived with Legesse taking orders from him TPLF continued .The Orthodox Church priests especially those with funeral services remember him since he was a funeral junkie, with not a sound coming out of him, wheelchair sitting, Meles Zenawi looking and unusually constantly observant of his surrounding person..

 2. የቀድሞ ጠቅላይ አቃቢ ህግ ጌታቸው አምባየና ሚኒስትር ከበደ ጫኔ በኢትዬጵያ ለተፈጸሙ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ዋና ተጠያቂ ናቸው ተባለ
  January 26, 2019 – Konjit Sitotaw — Comments ↓
  FacebookTwitterGoogle+EmailShare
  የፌደራል መንግስት በሰብዊ መብት ጥሰት መረጃ እያጠናከርኩ ነው።

  የአማራ መንግስት ብዙ መወራረድ ያለበት ጉዳይ አለኝ። የቀድሞ ጠቅላይ አቃቢ ህግ ጌታቸው አምባየ በኢትዬጵያ ለተፈጸሙ የስባዊ መብት ጥሰቶች ዋና ተጠያቂ ነው። በአዲስ አበባ ከተማ የቡና ውጭ ላኪዎችን በማሰር 7 ሰዎች ከ20 ሚሊዮን ብር በላይ መቀበሉ ተረጋግጡል።

  የጥረት የቦርድ አባል የተለያዩ የካምፓኒ ገዥዎች ላይ እጁ አለበት።

  በአማራ ክልል ከ170 ዳኞችና ዓቃቢ ህጎችን ከስራ አፈናቅሏል፣ ተባረውም በጥብቅና ስራ ፍቅድ እንዳያገኙ አድርጉል። በአዲስ አበባ የገነባቸው ውድ መኖሪያ ቤቶች ምስክር ናቸው።

  ከበደ ጫኔ የአማራ አስተዳደር ጋር በጋራ ወንቅሸት ገብርኤል ገዳም ከነሱ ጋ ተጣልተው 2 አማኞች ገዳሙ ውሥጥ አንዱን እንዲገደል እና እዛው እንዲቀበር አድርገውት ሌላኛውም አስረው መረጃ እንዳያወጣ አስጠንቅቀው ለውታል ።

  በወቅቱ መረጃ የነበረው አማራ ፓሊስ ኮሚሽን የተደራጁ ገድዮችን ይዞ በምርመራ ፍርድ ቤት ይከስሳሉ ከዛም ባስቸኩዋይ ክሱ እንዲቋረጥ በከበደና በጌታቸው ተደርጉዋል ።

  የዚህ መዝገብ አማራ ፓሊስ ኮሚሽን ይግኛል አዴፓ ይህንን ጉዳይ ዳር እንዲያደርስ የንጹህ ደም ይጣራል በአቶ አስመላሽ አማክኝነት የህውሃት ቀጥተኛ ጉዳይ ፈጻሚ ጌታቸው አሰፋ ጋር የአባት ስም ብቻ ነው ልዩነታቸው ምግባራቸው እንደ ስማቸው አንድ ነው።

  የታራሚዎችን ይዞታ በየ ጊዜው ለሚጎበኘው ያለመረጃ የማያስረው የዋና ዓቃቢ ህግ ብርሃኑ ጸጋየ ቀጣዩ ስራ!

  https://mereja.com/amharic/v2/87785

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here