Home News and Views   6ኛው አገር አቀፍ የኅብረት ስራ ኤግዚቢሽን፣ ባዛርና ሲምፖዚም 2011 አስመልክቶ...

  6ኛው አገር አቀፍ የኅብረት ስራ ኤግዚቢሽን፣ ባዛርና ሲምፖዚም 2011 አስመልክቶ በፌደራል የኅብረት ስራ ኤጀንሲ የተዘጋጀ ፕሬስ ኮንፍረንስ  

6ኛው አገር አቀፍ የኅብረት ስራ ኤግዚቢሽን፣ ባዛርና ሲምፖዚም 2011 አስመልክቶ በፌደራል የኅብረት ስራ ኤጀንሲ የተዘጋጀ ፕሬስ ኮንፍረንስ

ቦታ ፡- በኢሊሊ ኢንተርናሽናል ሆቴል

ቀን ፡-ጥር 23 ቀን 2011 ዓ.ም

ሰዓት፡- ጠዋት 4፡00 ሰዓት

ጋዜጣዊ መግለጫውን የሚሰጡት የስራ ሃላፊ፡-

ክቡር አቶ ኡስማን ሱሩር የፌዴራል ኅብረት ሥራ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር

 

ጥር 23 ቀን 2011 ዓ.ም

አዲስ አበባ

 ቦታ ፡- በኢሊሊ ኢንተርናሽናል ሆቴል

ቀን ፡-ጥር 23 ቀን 2011 ዓ.ም

ሰዓት፡- ጠዋት 4፡00 ሰዓት

ርዕሰ ጉዳይ፡-

  • 6ኛው አገር አቀፍ የኅብረት ስራ ኤግዚቢሽን፣ ባዛርና ሲምፖዚም 2011 አስመልክቶ የሁነቱን ዓላማ ብሎም ሁነቱ ምን ምን ፕሮግራሞችን እንደያዘ ለሚዲያ ተወካይ አካላት ገለጻ ለማድረግ

በፕሬስ ኮንፍረንሱ ላይ የሚገኙ የሚዲያ ተቋማት፡-

  • በዋፋ ጥሪ የተደረገላቸው የመንግስትና የግል የሚዲያ ተቋማት ጋዜጠኞች፣

ጋዜጣዊ መግለጫውን የሚሰጡት የስራ ሃላፊ፡-

  • ክቡር አቶ ኡስማን ሱሩር የፌዴራል ኅብረት ሥራ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር

 

የሁነቱ ዋነኛ ዓላማ

የፌዴራል ኅብረት ስራ ኤጀንሲ የኅብረት ስራ ማህበራት ግብይት ለፍትሀዊነት ተጠቃሚነት” “Cooperative Marketing for Fairness”  በሚል መሪ ቃል ከጥር 30 እስከ የካቲት 6 ቀን 2011 ዓ.ም 6ኛው አገር አቀፍ የኅብረት ስራ ኤግዚቢሽን፣ ባዛርና ሲምፖዚም 2011 ለማካሄድ ዝግጅት በማጠናቀቅ ላይ ይገኛል፡፡

የኅብረት ስራ ማህበራት፣ ከማህበራቱ ጋር የሚሰሩ መንግስታዊ የሆኑና ያልሆኑ አቅም ገንቢዎች፣ የግብርና ግብዓት አቅራቢያዎች፣ የማምረቻና የፍጆታ እቃ አምራቾች/ አቅራቢዎች እና የፋይናንስ አገልግሎት የሚሰጡ ተቋማትን በማሳተፍ በኅብረት ስራ ማህበራት መካከል ጠንካራ የግብይት ትስስር መፍጠር እና የግብይት ተደራሽነታቸውን ለማሳደግ ብሎም የአገራችንን የኅብረት ስራ ዕድገት ደረጃ ለማሳየት እና ለማስተዋወቅ ያለመ፡፡

የሁነቱ ዝርዝር ዓላማ

በአገር ደረጃ ህብረት ሥራ ማህበራትንና ሌሎች ባለድርሻ አካላትን በማገናኘት፤ የእርስ በእርስና ቀጣይነት ያለው ጠንካራ የግብይት ትስስር እንዲፈጥሩ በማድረግና የገበያ ስርዓቱን በማሳለጥ የአምራችና ሸማቹን ፍትሃዊ ተጠቃሚነት ማረጋገጥና በማምረትና ግብይት የተሰማሩ ህብረት ስራ ማህበራትን ምርቶች ለሸማቹ ኅብረተሰብ በማስተዋወቅ በአምራቹና በሸማቹ መካከል የሚኖረውን ዘላቂ ግንኙነት በማጠናከር አምራቾችን ከሸማቾች ጋር በማገናኘት ቋሚ ደንበኝነትን እንዲፈጥሩ በማስቻል የገጠርና የከተማውን የኢኮኖሚ ትስስር በማጠናከር የጋራ ጥቅምን ማረጋገጥ ነው፡፡

ስለሆነም የግብርና ምርቶችን በማምረትና እሴት በመጨመር በአምራቾች፣ በሸማቾችና በግብይት በተሰማሩ ኅብረት ሥራ ማህበራትና የግሉ ዘርፍ የግብርና ምርት በማቀነባበር ተግባር ከተሰማሩ ኢንዱስትሪዎች መካከል ጠንካራና ዘላቂነት ያለው የግብይት ትስስር በመፍጠር በከተማው ኅብረተሰብ የሚፈለገውን የምግብ ሰብል አቅርቦት በጥራትና በዋጋ ፍትሃዊና አስተማማኝ በማድረግ የተረጋጋና ጤናማ የግብይት ሥርዓት መፍጠር ይጠበቃል፡፡ በሌላ በኩል በአርሶ አደሩ የሚፈለጉ ልዩ ልዩ የኢንዱስትሪ ምርቶች ከአምራች ኢንዱስትሪዎች ጋር ሕብረት ስራ ማህበራቱ ዘላቂነት ያለው የገበያ ትስስር ፈጥረው በመውጣት ለአርሶ አደሩ የኢንዱስትሪ ምርቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ በማቅረብ የሁለቱንም ወገኖች ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ሌላው የሚጠበቅ ውጤት ይሆናል፡፡ በመሆኑም የህብረት ስራ ማህበራት የግብርና ምርቶች ላይ የሚኖራቸውን የግብይት ድርሻ ለማሳደግና የተዋንያንን ፍትሃዊ ተጠቃሚነት ስኬታማ ለማድረግ በሚደረገው እንቅስቃሴ የሚዲያ አካላትን ጨምሮ የሁሉንም አካላት የተቀናጀ ጥረት ይጠይቃል፡፡ 

ጥር 30/2011 ዓ.ም በኩነቱ የመጀመሪያ ቀን በአፍሪካ ህብረት የተባበሩት መንግስታት የኢኮኖሚ ኮሚሽን አዳራሽ ከሀገር አቀፍ እና ከአለም አቀፍ የዘርፉ ባለድርሻ አካላት ጋር ሲምፖዚየም የሚካሄድ ይሆናል፡፡ በሲምፖዚየሙ የሀገር ውስጥና የውጭ ሀገር ስኬታማ ኅብረት ሥራ ማህበራት ምርጥ ተሞክሮዎች የሚቀርቡበት፣ የዕውቀትና ክህሎት ሽግግር የሚከናወንበት፣ እርስ በርስ በመማማር በቀጣይ የኅብረት ሥራ ማህበራትን ወደ ላቀ ስኬትማነት ለማሸጋገር የሚያስችል ልምድ የሚለዋወጡበት መድረክ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ከየካቲት 1-6 ቀን 2011 ዓ/ም ድረስ ኤግዚቢሽኑና ባዛሩ በሚካሄድበት የአዲስ አበባ የኤግዚቢሽን ማዕከል ከመላ ሀገሪቱ የተውጣጡ 225 የኅብረት ስራ ማህበራት ምርቶቻቸውን እና አገልግሎታቸውን ለሸማቹ ህብረተሰብ  ለግብይት የሚያቀርቡ ይሆናል፡፡ በአዲስ አበባና በዙሪያዋ የሚገኙ ሸማቾችና አምራቾች ያለማንም ጣልቃ ገብነት ግብይት ይፈጽማሉ፡፡

በመጨረሻም ጥሪያችንን አክብራችሁ የመጣችሁ የመገናኛ ብዙሃን ጋዜጠኞች በፕሬስ ኮንፈረንሱ ላይ መገኘት በመቻላችሁ ምስጋናችን እያቀረብን፣ ከዚህ በታች በተዘረዘረው የ6ኛው አገር አቀፍ የኅብረት ስራ ኤግዚቢሽን፣ ባዛርና ሲምፖዚም ፕሮግራም መሰረት በመታደም ሁነቱን ለሕዝብ ጆሮና አይን ታደርሱልን ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃለን፡፡

  1. ጥር 29 ቀን 2011 ዓ.ም የመኪና ትርኢትና ቅስቀሳ በመዲናችን አዲስ አበባ፣
  2. ጥር 30 ቀን 2011 ዓ.ም በተባበሩት መንግስታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ሲምፖዚየም (ECA-UN፣
  3. የካቲት 1 ቀን 2011 ዓ.ም በአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል ከቀኑ 6፡00 ሰዓት ጀምሮ የኤግዚቢሽንና ባዛሩ መክፈቻ ስነ-ስርዓት
  4. የካቲት 6 ቀን 2011 ዓ.ም በአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል ከቀኑ 5፡00 ሠዓት ጀምሮ ኤግዚቢሽንና ባዛሩ መዝጊያ ስነ-ስርዓት ይካሄዳል፡፡
  5. ከየካቲት 1 እስከ 6 ቀን 2011 ዓ.ም በአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል ሸማቹና አምራቹ ይገበያያል፣ ዘላቂነት ያለው የገበያ ትስስር አምራቹ፣ ከሸማቹ እና ከግብርና ምርት አቀናባሪዎች ጋር ያካሂዳሉ፣

በመሆኑም ከላይ የተገለጹትን ሁነቶች በመዘገብ ለህዝብ ጆሮና አይን እንድታደርሱልን የተለመደ ትብብራችሁን እንጠይቃለን፡፡

ለበለጠ መረጃ

ወ/ሮ አያልሰው ወርቅነህ 0911-06 09 23

ወ/ሮ ጫልቱ ታምሩ    0923- 56 70 07

አቶ ዳንኤል አበበ      0978-6703087

(የኤጀንሲው ሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት)

የፌዴራል ኅብረት ስራ ኤጀንሲ ህዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here