የአፍሪካ መሪዎችና ታላላቅ የዓለም ሰዎች በሚገኙበት ሥነሥርዓት ላይ የአፄ ኃይለሥላሴ መታሰቢያ ሃውልት ይቆማል ያለው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ነው፡፡ ቃል አቀባዩ ነቢያት ጌታቸው ዛሬ እንደተናገሩት አፄ ኃይለሥላሴ ለአፍሪካ አንድነት እና ለአፍሪካ ሕብረት ለሰሩት ስራ መታሰቢያነት በህብረቱ ጊቢ በግልፅ በሚታይ ቦታ በ32ኛው የሕብረቱ የመሪዎች ጉባዔ ወቅት ይተከላል ብለዋል፡፡ 32ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባዔ የካቲት 3 ቀን 2011 ዓ.ም በህብረቱ አዳራሽ ይከፈታል ተብሏል፡፡
ሸገር ሬድዮ