Home News and Views ለውጡን ለማስቀጠል (አብርሃም በየነ)

ለውጡን ለማስቀጠል (አብርሃም በየነ)

ባሁኑ ሰዓት የኦረሞ ጉምቱዎች በሁለት ጎራ ተሰልፈዋል። በስውርና በይፋ። አንደኛው ከአቢይ ጋር ሲሆን ሌላኛው ከኦነግና ከወያኔ ቅሬቶች ጋር ቆሞ እየተፋተጉ ነው። በኦዴፓ ውስጥ ያሉ አክራሪ ኦረሞዎች ውስጥ ውስጡን የኦነግን ሥራ እየሠሩ አቢይን ህዝባዊ መሠረት ለማሳጣት እየጣሩ ነው። ኦነግና አክራሪዎቹ ዓላማየ ያሉትን የኦረሞን የበላይነት ማስረገጥ ሲሆን፤ ይህንንም ዓላማ ከግቡ ለማድረስ ጃዋር ከግብጽና ከአክራሪ እስላም ዐረብ አገሮች በሚያገኙት ዕርዳታ የኦረሞን የባላይነት ብቻ ሳይሆን እስልምናንም በማግነን ኢትዮጵያን እስላማዊ ኦረሚያ ማድረግ ነው። ኦነግም በተመሳሳይ ከፍ ብሎ ከተጠቀሱት አገራት በሚለገሰው ዕርዳታ የኦረሞን የበላይነት ለማረጋገጥ ኢትዮጵያን ማፈራረስ (deconstruct) የሚለውን መሠረታዊ ዓላማውን ግብ ለማድረስ እነጃዋርን በግንባር አሰልፎ በኦዴፓ ውስጥ ውስጥ ውስጡን ሥራውን ቀጥሏል። ለዓላማው ስኬትም

1ኛ ጠረፍ ዙሪያ ያሉ ኦረሞዎችን ሆን ብሎ አፈናቅሎ የተፈናቀሉትንም ወደ ነበሩበት ቀያቸው መመለስና ማስፈር ሳይሆን በከተሞች በተለይም በአዲስ አበባ ዙሪያ በማስፈር የከተማዎችን የህዝብ ስብጥር (demography) መለወጥ ነው:: ይህንን ሃሳብ ኦቦ ለማ በግልጽ ባደባባይ ተናግረውታል። ይህም በአንድ በኩል ኦረሞውን ሰብሰብ አድርጎ አንድ አይነት ህዝብ በክልሉ እንዲኖር በማድረግ ቅልቅል የሌለበት የኦረሞ ህዝብ መፍጠር ሲሆን በሌላ በኩልም የወደፊቱ ፖልተካ በከተማ እንጂ በገጠር ስለማይሆን የከተማው የህዝብ ስብጥር ኦረሞ አብላጫ ቁጠር እንዲኖረው ማድረግ ነው።

2ኛ ለዚህ ስኬት እንቅፋት ሊሆኑ ይችላሉ የተባሉትን ኦረሞ ያልሆኑትን ዜጎች ማፈናቀልና ቦታውን በኦረሞዎች መሙላት ነው። በቡራዩና በለገጣፎ የተከሰቱት ማፈናቀሎች ለዚህ ጥሩ ማሳዎች ናቸው።

3ኛ እንደሚታወቀው ኦነግ ከውጭ ሲገባ ይዞት የገባው ጦር ወደ ካምፕ ተወስዶ የተሃድሶ ስልጠና እየተሰጠው ነው። ሆኖም ግን ኦነግ በገባ አምስት ወር ባልሞላ ጊዜ ውሰጥ ከሁለት ሺህ በላይ ታጣቂ ጦር አፍርቶ አንድ ሳምንት ባልሞላ ጊዜ ወስጥ 18 ባንኮችን ዘርፎ ራሱን ሚሊየነር ሊያደርግ ችሏል። ይህም ሆን ተብሎ ሥራ አጥ ቄሮዎችን ወደ በርሃ በማስወጣት አስታጥቆ ተጠቃሚ እንዲሆኑ የተዘደ ዘዴ ነበር። እነለማ የኦነግን ጦር ሊመቱ ሲሉ በኦዴፓ ውስጥ ያሉት አክራሪ ኦረሞዎች እነሌንጮ ለታን ጨምሮ እየተቃወሙ ኦነግን አገነገኑት። የገነገነው ኦነግም በድርድር ወታደሮቹ ወደ መከላከያ እንዲጠቃለሉ ባባገዳዎቹ ፊት እነለማን ቃል አስገባ። በዚህ ሂደት ትናንት የትግሬ ጦር የነበረው መከላከያ ነገ የኦረሞ ጦር እንዲሆን ታልሞ ተሠራ። እግረመንገዱንም ሥራ አጡ ቄሮ የሥራ ዕድል ተከፈተለት። የነገዋ እስላማዊት ኦረሚያም የህልውና ዋስትናዋ የተርጋገጠ እንዲሆን ተቀየሰ። እንግዲህ ለነዚህ ዓላማዎች ስኬት ሲባል ነው ዛሬ ሆን ተብሎ ህዝብ በየቦታው የሚፈናቀለው። ይህም በራሱ በነገው ምርጫ የኦነግን አሽናፊነት እንዲያረጋግጥ ሆን ተብሎ የተቀመረ የፖእለቲካ ቀመር ነበር። ለነዚህ የፖለቲካ ስኬቶች ሁሉም የኦረሞ ልሂቃን በጥምረት እየሰሩ ናቸው።

እናስ ምን ይደረግ?

ድክተር አብይ እውውነተኛ የለውጥ ሰው ከሆነ ቶሎ ብሎ ወርቅንህ ገበየሁን እንደ አገለለው በኦዴፓ ውስጥ ያሉትን አክራሪዎች ማጽዳት ይኖርበታል። ቀጥሎም ጃዋርን በአሽባሪነት ወንጅሎ ለፍርድ ማቅረብና የኦነግን መሪዎችም በሚሠሩት ሥራ በህግ ተጠያቂ እንዲሆኑ ማድረግ ይጠበቅበታል። ባጠቃላይ ግን በደቡብ ህዝቦችና በአማራ ፓርቲዎች የተሰገሰጉትን የወያኔ ቅሬቶች በማጽዳት ዘመቻውን አጠናክሮ በርሱ ላይ እያዘቀዘቀ ያለውን የህዝብ አመኔታ (public confidence) መልሶ ወደነበረበት ማምጣት ይጠበቅበታል። ይህ ካልሆነ ግን አገዛዙ ባጭር ጊዜ ውስጥ ይናዳል። አገሪቱም መልሳ በጅቦች እጅ ትገባና የርስበርሱ ፍጅት የሩዋንዳን ታሪክ ሊደግም ይችላል። ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር መጋቢት 2011

አብርሃም በየነ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here