Home News and Views ኢትዮጵያ፤ አፋፍ ላይ የምትገኝ ሃገር – ዳዊት ወልደጊዮርጊስ

ኢትዮጵያ፤ አፋፍ ላይ የምትገኝ ሃገር – ዳዊት ወልደጊዮርጊስ

ምንጭ – Ethiopia: A Country on the Brinks
ተርጓሚ – ሚኪያስ ጥላሁን
‹‹ከመጠን በላይ ተክበዋል››

አለመረጋጋትና ሁከት በአብዛኛው የኢትዮጵያ ክፍል በተስፋፉበት ወቅት፣ በቅርቡ የሰሜን ሸዋ ዋና ከተማ አቅራቢያ የተፈፀሙት ጥቃቶች፣ ኢትዮጵያ ወደ አደገኛ የእርስ በርስ ጦርነት እንዳያስገባት፣ ኢትዮጵያውያንና የክልል መንግስታትን አስግቷል፡፡

የሰላማዊ ለውጥ አጀንዳን ይዘው ወደ ስልጣን የመጡት – ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ላይ የሁሉም ዓይኖች አርፈዋል፡፡ በእርሳቸው የአንድ ዓመት የጠቅላይ ሚኒስተርነት ቆይታ የሃገሪቷ ሁኔታ የእርስ በርስ ጦርነት የመከሰት ዕድል ያመዘነበትና ከድጡ ወደ ማጡ ያመራበት ነው፡፡

31ኛው የአሜሪካ ፕሬዝደንት ኸርበርት ሆቨር፣ 1928 (እ.ኤ.አ) ላይ የስራ ዘመናቸውን ሲጀምሩ፣ እጅግ በጣም ተወዳጅ ነበሩ፡፡ ከጥቂት ጊዜያት በኋላ ግን የፕሬዝደንትነት ዘመናቸው በ‹‹ታላቁ ድባቴ/ The Great Depression›› የተሞላ ሆነ፡፡ አሁን ፕሬዝደንቱ የሚታወቁት ለቀውሱ አስፈላጊውን ምላሽ ለመስጠት በመቸገራቸው ነው፡፡ እርሳቸው እንዲህ ይናገራሉ፣

‹‹ጓደኞቼ እኔን ከባድና ውስብስብ ችግርን መፍታት የምችል ልዕለ-ሰብ አድርገው ለአሜሪካ ህዝብ አቅርበዋል፡፡ ከፖለቲካዊ አቅም ያለፈ ችግር በመሬት ላይ በመከሰቱ፣ ህዝቡ ከእኔ የማይቻለኝን ነገር ሲጠብቅ ነበር፡፡ እኔ ራሱ የችግሩ ተጠቂ ልሆን እችላለሁ…እኔ ከመጠን በላይ ተክቤያለሁ፡፡››

ኸርበርት ሆቨር በአብዛኛው ከሚወቀሱበት ጉዳይ አንዱ፣ ‹‹ታላቁ ድባቴ››ን ለመፋለም በበቂ መልኩ አለመንቀሳቀሳቸው ነው፡፡ በርካታ የታሪክ ተመራማሪዎች እንደሚያምኑት ሆቨር የችግሩን አሳሳቢነት አቃልለው አይተውታል፡፡ ሆቨር ቀውሱ በጊዜ ሂደት ‹‹ይቃለላል!›› ብለው ቢያስቡም፣ በተቃራኒው ግን እየከፋ መጥቷል፡፡ ወደ ስልጣን ዘመናቸው ማገባደጃ ሰሞን (እርሳቸው በፕሬዝደንትነት ያገለገሉት እ.ኤ.አ ከ1929 እስከ 1933 ድረስ ነው፡፡)፣ ሆቨር አስፈላጊ የኢኮኖሚ ማሻሻያ ነጥቦችን ለማቅረብ ሞክረው ነበር፤ ግን አጅግ በጣም አርፍደው ነበር፡፡ ሆቨር በመጨረሻ ሰዓት ለመንቀሳቀስ ቢጥሩም፣ ብዙ አሜሪካውያን ግን ሃገሪቱ ልትበታተን ጫፍ ደርሳ ሳለ፣ ፕሬዝደንቱ ስራ ፈትተው እንደተቀመጡ አምነዋል፡፡ ፕሬዝደንቱ ለአንድ ዙር የስልጣን ዘመን ብቻ አገልግለዋል፡፡

አብይ ከመጠን በላይ ተክበዋል፤ አንደልዕለ-ሰብም ታስበዋል፡፡ ህዝቡ በከበባ፣ ባለመተማመን ስሜትና በላቀ የእርስ በርስ ጦርነት ስጋት ውስጥ በነበረበት ጊዜ፣ አብይ ወደ ስልጣን መጡ፡፡ የአብይ ቃላትና አንዳንድ ተግባራት፣ መፅናናትንና ተስፋን ለህዝቡ ሰጡ፡፡ ልክ እንደሆቨር፣ አብይም የኢትዮጵያን ችግሮች ጥልቀትና ውስብስብነት አቃልለው ተመለከቱ፡፡ ነገር ግን እንደሆቨር በችግሮቹ ላይ ሳይሳለቁ፣ ለተቸገረችው ሃገር አዳኝ እንደሆኑ የሚገልጥ ዓላማ ያዙ፡፡ አጤ ሃይለስላሴ፣ መንግስቱና መለስ – ሁሉም ራሳቸውን እንደልዕለ-ሰብ አድርገው ይቆጥሩ ነበር፡፡ የማስጠንቀቂያ ምልክቶችን ለመረዳት አልፈለጉም ነበር፡፡ የሁሉም መጨረሻ አሳፋሪ ሆነ፡፡ እናም፣ ዛሬ ሃገሪቱን አፋፍ ላይ ያቆመ ውርስ ትተው አለፉ፡፡

ለትናንት መሪዎች የሃገሪቱ አንድነት ቀዳሚ አጀንዳ ነበረ፡፡ በዚህ ረገድ ህዝቡን አላስከፉም፡፡ የአሁኑ ትውልድ የትናንት ስህተቶችን ለማስተካከልና ሃገሪቱን በአንድነቷ እንድትዘልቅ የሚረዱ አወንታዊ ምክንያቶችን ለማስቀጠል፤ የመሪነት ስፍራውን ይዟል፡፡ የአሁኑ ትውልድ ይህን ዓላማውን ለማሳካት ባለመቻሉ፣ የሃገሪቱ ህልውና አደጋ ውስጥ ገብቷል፡፡ በአሁኑ ሰዓት ኢትዮጵያ በተነዋወጠ ውሃ ላይ የምትገኝ መቅዘፊያ-አልባ መርከብ መስላለች፡፡

ኢትዮጵያ የከሸፈች ሃገር ነች

በሁሉም መለኪያዎች ኢትዮጵያ የከሸፈች ሃገር ነች፡፡ አሁን የሚያሳስበው ይህ ሁኔታ ምን ያህል ሊጋጋልና አሳዛኝ ሊሆን ይችላል የሚለው ነው፡፡ ለጥቂት ዓመታት አስጠንቃቂ ምልክቶች ሲታዩ ቆይተዋል፤ አሁን ደግሞ ሃገሪቷን እንዳያፈርሳት ያሰጋል፡፡ መሪዎችና ልሂቃኑ በገዢው ፓርቲ – የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዲሞክራሲ ግንባር (ኢህአዴግ) ለ28 ዓመታት ያህል ተቋማዊ ቅርፅን የተላበሰው የዘውግ ፖለቲካ፣ ሃገሪቷን የሚያስድኋት አለመርካቶችና ከባርነት ነፃ ያለመውጣት ስሜቶች ብቸኛ ምከንያት አድርገው ሲያቀርቡት ይደመጣል፡፡ መለስ ዜናዊና ተተኪዎቻቸው ችግሩን ለማሳወቅ አልፈለጉም፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ወደ ስልጣን ሲመጣ፣ ህዝቡ ለተቸገረችው ሃገር አዳኝ አንደሆነ አስቦ ነበር፡፡ የዛሬ አንድ ዓመት የሆነው ይህ ነበር፡፡ የደስታው ስሜት ተንኖ፣ አትዮጵያ በሚታና በፈጣን ሁኔታ የከሸፈች ሃገር ሆናለች፡፡

የከሸፈ ሃገር የሚያጠቃልላቸው ነጥቦች፡-

 • ነፃ የፖለቲካ ተሳትፎ አለመኖር
 • የሃገርን ዳር – ድንበር መቆጣጠር አለመቻል
 • የግዙፍ መፈናቀሎች መኖር
 • ማህበራዊ አገልግሎቶችን (ምግብ፣ ጤና፣ ቤት…ወዘተ) ማቅረብ አለመቻል
 • ከፍተኛ የሙስና መጠን
 • ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ከሃገር ለመውጣት የሚፈልጉ ስደተኞች መኖር
 • ምንም ወይም ደካማ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ

ኢትዮጵያ ከላይ የተጠቀሱትን – ሁሉንም ታሟላለች፡፡ ሃገራት ይወድቃሉ፣ ምክንያቱም አገልግሎቶችን ማቅረብ ስለማይችሉ፡፡ ወሳኙ ነገር የሰዉ ደህንነት መጠበቅ ነው፤ መንግስት ጥበቃና ከለላ ለህዝብ ካልሰጡ፣ በህዝቡ ዘንድ ያላቸው ቅቡልነት ይሟጠጣል፡፡ አስፈላጊ እርምጃዎችም በግለሰብ ወይም በቡድኖች ይወሰዳሉ፤ ህግን በራሳቸው መንገድ እስከማስፈፀም ድረስ፡፡ ሁኔታውና አለመረጋጋቱ እየከፋ ሲመጣ፣ የሃገር ውስጥና ውጭ አካላት የራሳቸውን ጥቅም ለማስከበር ይንቀሳቀሳሉ፡፡ ሃብቶችን ለመቆጣጠር የሚደረገው ሽቅድድም የጎበዝ አለቆችን ይፈጥራል፡፡ ከመጠን ያለፈ ጥላቻን አዝለው ከመንግስት ጋር ወይም እርስ በርሳቸው ይፋለማሉ፡፡

አዲስ ስታንዳርድ መጋቢት 26 (እ.ኤ.አ) እንዲህ ሲል ዘግቧል፣

‹‹የኢትዮጵያ መንግስትና የራሱ ክልላዊ መንግስታት ባለስልጣናት የጥበቃ ቁጥጥርና ስርዓትን ለማስከበር ከፍተኛ መሰናክሎች ተጋርጦባቸዋል፡፡ እንደሚታወቀው በርካታ አካባቢዎች ከማዕከላዊ መንግስቱ ጋር በአስተዳደር መዋቅር የተያያዙ አይደሉም፤ ነገር ግን ከፓርቲው በተገፉ አካባቢያዊ ቡድኖች ወይም በገዢው ጥምር ቡድን – ኢህአዴግ መዋቅር ውስጥ በተጠቃለሉ አፈንጋጮች እየተዳደሩ ነው፡፡››

ግጭትና ብጥብጥ በኦሮሚያ ክልል፣ በሰሜን ሸዋ፣ በወሎ፣ በደቡብ ኢትዮጵያና በሌሎች በርካታ አካባቢዎች – በሰፊው ተንሰራፍቷል፡፡ ዘበት በሚመስል አኳኋን፣ ሰላማዊው ቦታ ትግራይ ነው፡፡ ከኦነግ ጋር የተሳሰሩ የወንጀል ቡድኖች፣ ቄሮ (የኦሮሞ ወጣቶች ንቅናቄ)ና በግልፅ የማይታወቁ ቡድኖች፣ ሃገሪቱ ውስጥ በነፃነት በመንቀሳቀስ ግፍ የተሞላባቸው ወንጀሎችን እየፈፀሙ ናቸው፡፡ ህዝቡ ግድያዎችን፣ የመንገድ መዘጋቶችን፣ ዘረፋ፣ ማፈናቀሎችን፣ የመኖሪያ ቤቶችን ውድመት ለምዷል፡፡ ህዝቡ ሁልጊዜ ከዚህ የባሰ እንዳይመጣ በየጊዜው መፀለዩን ተያይዞታል፡፡ ነገር ግን የባሰው እየመጣ ነው፡፡

በቅርቡ አዲስ አበባ ላይ የተቋቋመ አንድ የሰብዓዊ መብቶች ድርጅት፣ አዲስ አበባ የሚገኘው – በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ መንግስት የተፈፀሙ የሰብዓዊ ጥሰቶችን የሚገልፅ መግለጫ አውጥቶ ነበር፡፡ ድረ-ገፁ ላይ እንደገለጠው፣

‹‹ይህ ሰነድ የጊዜ ቅደም-ተከተሉን እንደጠበቀ መዘርዝር የሚያገለግል ሲሆን፣ የኢትዮጵያ መንግስት አንድ አካል በሆኑት፣ በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ስር የተፈፀሙ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችንና ከባድ ቸልተኝነቶችን ያሳያል፡፡

የሪፖርቱ አርዕስተ-ጉዳይ፡-

 • የአዲስ አበባ ከንቲባ ህገ-ወጥ ሹመትና ውዝግቦቹ
 • የቡራዩ ጭፍጨፋና ውዝግቦቹ
 • አዲስ አበባ ውስጥ የሲቪክ ጥበቃ ቡድን ለማቋቋም የሞከሩ ግለሰቦች እስር
 • የአዲስ አበባ የነዋሪነት መታወቂያ ቅሌት
 • መንግስት ህዝብን ከለገጣፎ ማፈናቀሉ
 • የአዲስ አበባ ጥያቄ
 • የዴሞግራፊ ምህንድስና ››

እነዚህ አጋጣሚዎች በሃገሪቷ ማዕከል ላይ የተደረጉ ሲሆኑ፣ ወትሮም የተመሰቃቀለችውን ሃገር ወደ ሌላ ደረጃ ወስደዋታል፡፡ አጋጣሚዎቹ በተፈጠሩበት ወቅት፣ የጠቅላይ ሚኒስትሩ በዝምታ መዋጥ በጣም ግራ ያጋባ ነበር፡፡ ሃገሪቱ መሪ-አልባ እንደሆነች የሚያስመስል ስሜት ፈጥሯል፡፡ የሃገር መሪ በቀውስ ወቅት፣ የሃገሩን ጥቅም በደንብ የሚያስጠብቁ ከባድ ውሳኔዎችን ያሳልፋል፡፡ መሪ ነገሮች እንዳመጣጣቸው እንዲቀጥሉ አይፈቅድም፡፡ አሁን ኢትዮጵያ በልል የፌዴራል ስርዓት ውስጥ ብትገኝም፣ መሪው በተወሰነ መጠን የቁጥጥር አቅም ሊኖረው ይገባል፡፡ ጠ.ሚ. አብይ በግልፅ የቁጥጥር ሁኔታ ውስጥ አይደለም ያሉት፡፡ ዛሬ የኢትዮጵያ ማዕከላዊ መንግስት በደካማ አቋም ውስጥ ይገኛል፡፡

የአፍሪካ የስትራቴጂክና ፀጥታ ጥናቶች ተቋም (AISS) ለብዙ ጊዜ የኢትዮጵያ የክልል መሪዎችን፣ አትዮጵያ አደጋዎች እየተጋረጡባት መሆኗንና በክልላዊ መረጋጋት ላይ ቀጥተኛ ተፅዕኖ እንዳላቸው አሳስቦ ነበር፡፡ ተቋሙ የኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ ለምስራቅ አፍሪካና ከዚህ ውጭ ላለው አካባቢ የመረጋጋት ጠንቅ አድርጎ ያዬዋል፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ የሚፈጠረው የእርስ በርስ ጦርነት ያልተገመተ አሳዛኝ መከራና ውጥንቅጥ በቀጠናው የሚፈጥር ሲሆን፣ ከቀጠናው ውስጥና ውጭም ትርምስ ይፈጥራል፡፡

በመንግስትና በተዋጊ ቡድኖች መካከል በተደረገ ግልፅ ያልሆነ ስምምነት በመተማመን ተዋጊዎችን ወደ ሀገር ማስገባት አንደኛው ትልቅ ስህተት ነበር፡፡

በጠቅላይ ሚኒስትሩ ፅ/ቤት በተዘጋጀ አንድ ስብሰባ ላይ የመልሶ ማቋቋም ፕሮዤ (የቀድሞ ተዋጊዎችን ትጥቅ የማስፈታትና መልሶ የማቋቋም ስራ) ሃላፊ፣ በመንግስትና በቡድኖች መካከል ምንም ዓይነት የፅሁፍ ስምምነት ባለመኖሩ ወደ ግጭት ማምራታቸውን ሲነግሩን፣ እዛው – በስፍራው ነበርኩ፡፡ ወደ አሁኑ ቀውስ የገፋን ይህ አንደኛው ትልቁ ስህተት ነው፡፡ ትጥቃቸውን አንዲፈቱና ወደ ማህበረ-ሰቡ እንዲቀላቀሉ የታሰቡት ተዋጊዎች ወደ ሃገር ቤት ሲገቡ ግን ትጥቃቸውን ፈትተው ሂደቱን እንዲቀላቀሉ፣ መደበኛ ህይወት እንዲጀምሩ አልተደረገም፡፡ ነአምን ዘለቀ ተዋጊዎችን እንደሰው ለመንከባከብና የሃገሪቱ የፀጥታ ስጋት አንዳይሆኑ ለማድረግ የመንግስት ፈቃደኛ አለመሆንን ወይም አለመቻልን በብርቱ ይተቻሉ፡፡ አሁን የተወሰኑቱ የዕውነትም ስጋት ሆነዋል፡፡ አፍሪካ ውስጥ ትጥቅ በማስፈታት ዙሪያ በርካታ ልምዶች አሉ፡፡ መንግስት ምክር ለመስማት ወይም ድጋፍ ለመቀበል አለመፈለግን መርጧል፡፡

ግልፅ ፍኖተ-ካርታ እንዲኖር ወይም ግልፅ ለማድረግ አለመቻል፣ ዋነኛው አሳሳቢና በጠ.ሚው በቀደምቶች መዘርዝር ውስጥ ያልተካተተ ጉዳይ ነው፡፡ ሽግግርን ለመጀመር አስፈላጊው ነገር ፍኖተ-ካርታ ነው፡፡ በርካታ ጉዳዮች ባልጠሩበትና አመራሩ ጉልህ ውሳኔዎችን መወሰን ባልቻለበት ሁኔታ፣ የሃገሪቷ ድንበር በውል ወዳለመታወቅ ቢንደረደር አይገርምም፡፡ መንግስት ከተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎችና ክልሎች የሚመጡ ሪፖርቶችን፣ ማንኛውም ሰው አይቶ የሚረዳውን ማስጠንቀቂያ ለመስማት ዝግጁ አይደለም፡፡

ዛሬ ኢትዮጵያ በአፍሪካ ውስጥ ከሚገኙ፣ ጥቂት የከሸፉ ሃገራት ወደሚጠቀሱበት መለኪያ መግባቷ እርግጥ ሆኗል፡፡ ስለከሸፉ ሃገራት ያጠኑት ሮበርት ሮትበርግ ፕሪንስተን ዩኒቨርሲቲ ፕሬስ ላይ (የሃገረ-መንግስታት መጥፋትና ውድቀት) በሚል ርዕስ እንዲህ ሲሉ ፅፈዋል፣

‹‹የከሸፉ ሃገራት በውጥረት የተሞሉ፣ በግጭት የታጠሩ፣ አደገኛ እና በተፋላሚ አንጃዎች መካከል የተካረረ ውጥረት አለባቸው፡፡ በብዙ የከሸፉ ሃገራት፣ የመንግስት ጦሮች ከአንድ ወይም ከዛ በላይ ተቀናቃኝ ታጣቂ አመጸኞች ጋር ይፋለማሉ፡፡ አንዳንድ ጊዜ በከሸፉ ሃገራት የሚገኙ ባለስልጣናት ሁለትና ከዛ በላይ አመፆችን፣ የተለያዩ የህዝብ አለመረጋጋቶችን፣ የተለያየ መጠን ያላቸውን የማህበረ-ሰብ እምቢተኝነቶችንና በመንግስትና መንግስት ውስጥ ባሉ ቡድኖች ላይ ያነጣጠረ ከመጠን ያለፈ ተቃውሞ ያስተናግዳሉ፡፡››

ማዕከላዊ መንግስት በርካታ አካባቢዎችን መቆጣጠር ያቅተዋል፤ የመንግስት መሰረታዊ ስራዎችን መስራት አይችልም፡፡ ህዝቡ የተቀናቃኝ አንጃዎችና የወንጀል ቡድኖች ሰለባ ይሆናል፡፡ በዚህ ሁሉ ውጥንቅጥ መሃል የውጭ ጣልቃ-ገብነት ስለመኖሩ፣ አስተውሎ መጠርጠር ያስፈልጋል፡፡ ኢትዮጵያ ላይ የሚታዬው የእርስ በርስ ጦርነት አዝማሚያ በአብዛኛው የዓለም የጦርነት ቀጣና ውስጥ እንደሚስተዋለው ብዙ ውጭ አካላት ሁኔታውን በራሳቸው ፍላጎት ለመዘወር ወደ ውክልና ጦርነት ሊገቡ ይችላሉ፡፡

የሚበተኑ ሃገራት መለኪያ (FSI) (በፊት ‹‹የከሸፉ ሃገራት›› ተብሎ ይታወቃል)፣ ‹‹የ178 ሃገራትን ደረጃ ያወጣል፡፡ የመበታተን ደረጃቸውን የሚወስኑ የተለያዩ የሚገጥሙ ግፊቶች ላይ ይመሰረታል፡፡ መለኪያው የሰላም ባለቤትነትን ለማረጋገጥ የሚፈስ ገንዘብ፣ በግጭት ግመታ ስርዓት (CAST) የትንተና ዘዴ ላይ ይመሰረታል፡፡ ሰፊ የማህበራዊ ሳይንስ ስነ-ዘዴ ላይ በመመስረት፣ ሶስቱ ዋና የመረጃ ግብዓቶችን – አሃዛዊ፣ ፅሁፋዊና የባለሙያ ተገቢነት – የሶስትዮሽ በማጣመርና ጥልቅ ግምገማ በማድረግ መለኪያው ይሰራል፡፡››

የሚበተኑ ሃገራት መለኪያ በተከታታይ እንደሚያሳዬው እ.ኤ.አ 2007 ላይ ኢትዮጵያ በአግባቡ ከማይሰሩ መንግስታት መካከል አንዷ ነበረች፡፡ በ‹‹ገንዘብ ለሰላም ተቋም›› (Fund for peace institute) ከ2007-17 የተሰሩ መለኪያዎችን ብናይ፣ 2008-16ኛ፣ 2009-16ኛ፣ 2010-15ኛ፣ 2012-17ኛ፣ 2013-19ኛ፣ 2014-19ኛ፣ 2015-19ኛ፣ 2017-15ኛ፣ 2018-15ኛ፡፡ የ2019 ሪፖርት ከዚህ የከፋ እንደሚሆን ይጠበቃል፡፡

አሁን ላይ የመለኪያው መሪ ሃገራት – አንደሶሪያ፣ የመን፣ ሶማሊያ፣ ደቡብ ሱዳን፣ አፍጋኒስታን፣ ዴሞክራቲክ ሪፑብሊክ ኮንጎና ማዕከላዊ አፍሪካ ሪፑበሊክ ምንም ወይም አነስተኛ የጦርነት መጠን ውስጥ ሁኔታው በዚህ ከቀጠለ፣ የመለኪያው መሪ ሃገር ልትሆን ትችላለች፡፡

ከአፍሪካ ሃገራት በህዝብ ብዛት ሁለተኛዋ ሃገር፣ 100 ሚሊዮን ህዝብ ያቀፈች፣ ያልተረጋጋችና በአግባቡ የማትመራ፤ ስትራቴጂካዊ ቦታ ላይ መገኘቱና ሃብቶቿ ቀጠናዊ ግጭትና የውክልና ጦርነቶችን ሊያስነሱ ይችላሉ፡፡ የምዕራብ ሃገራት ኢትዮጵያን በውሸት – የተረጋጋች ሃገር ከፈጣን አዳጊ ኢኮኖሚ ጋር ያላት ሃገር አድርገው ይገልጣሉ፡፡ ዕውነታዎች ከምንጊዜውም በላይ ግልፅ ናቸው፤ ኢትዮጵያ ሊትበተን የደረሰች ሃገር ሆናለች፡፡

ኢትዮጵያ በሃገር ውስጥ የተፈናቀለ 3 ሚሊዮን ህዝብ አላት፤ በ2018፡፡ (ተጨማሪ ህዝብ ስለተፈናቀለ፣ 2019 ላይ ወደ 4 ሚሊዮን የሚጠጋ ተፈናቃይ ተመዝግቧል፡፡) በግጭቶች ምክንያት ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለዋል፡፡ 1.4 ሚሊዮን ህዝብ ቤቱን ጥሎ ተሰድዷል፤ ከቤቱ የተሰደደው የሶሪያ ህዝብ ግን 1.2 ሚሊዮን ነው፡፡

ዘ ጋርዲያን በቅርቡ የተፈፀሙ የሃገር ውስጥ መፈናቀሎች ላይ እንዲህ ብሏል፣

‹‹ጎቲቲ መንደር ውስጥ የሚገኘው አንድ መጠለያ ከ20-30,000 የጌዲኦ ተወላጆችን አስጠልሏል፣ ተወላጆቹ ከነሃሴ 2018 ጀምሮ የሰብዓዊ እርዳታ ተከልክለዋል – ከሁሉም በላይ የምግብ እርዳታ፡፡ በ2018 ከሚሊዮን የሚበልጡ ኢትዮጵያውያን በዘውግ ግጭት ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለዋል – በሃገር ውስጥ ተፈናቃይ ብዛት ከማንኛውም ሃገር በላይ የላቀ ነው፡፡ አስከፊው ጁኔታ የደረሰው ደቡብ ላይ ሲሆን፣ ከሃገሪቱ ታላቅ ክልል – ከኦሮሚያ፣ ምዕራብ ጉጂ ዞን – 800,000 ገዲኦዎች ተፈናቅለዋል፡፡ የተፈናቃዩ ቁጥር እጅግ ከፍተኛ መሆኑ ሲታወቅ፣ በ2017 ማይናማር ውስጥ ከተፈጠረው የሮሄንጊያ ቀውስ ጋር በሚመሳሰል ሁኔታ፣ በአጭር ጊዜ ውስጥ በርካቶች ተፈናቅለዋል፡፡ እንደእሳተ-ገሞራ ፍንዳታ ሞልቶ የፈሰሰ በርካታ ህዝብ በቀውሱ ምክንያት የምግብ አቅርቦት እየጠበቀ ነው፡፡ ጌዲኦዎችና ኦሮሞዎች በሃገሪቱ ውስጥ በከፍተኛ የህዝብ ጥግግት የሚታወቀውን የእርሻ መሬት ሲጋሩ፣ ሁለቱ ዘውጎች በቁጥ ዕኩል እያደጉ ነው፡፡ አሰቃቂ የህገ-ወጥ ግድያዎች፣ አስገድዶ መድፈሮች፣ አንገትን የመቅላት ተግባራት እና በአካባቢው ባለስልጣናት፣ ፖሊስና ሚሊሺያ የሚታዬውን ውትብትብነት የሚገልጡ ሪፖርቶች፣ ሁናቴው የተደራጀ የዘር ማፅዳት ዘመቻ እንጂ ተራ የጎሳ ግጭት እንደማይመስል ያስረዳሉ፡፡››

በኢህአዴግ የተረቀቀው ህገ-መንግስት የተወሰኑ የዘውግ ቡድኖች (አማራ፣ ኦሮሚያ፣ ትግራይ፣ ሶማሊ፣ ጋምቤላ፣ አፋር) የራሳቸው ክልል እንዲኖራቸው ተፈቅዷል፡፡ የኢትዮጵያ ከ80 በላይ የዘውግ ቡድኖች የራሳቸውን የክልል መንግስት ለማቋቋም ፍቃድ እየጠየቁ ነው፡፡

በእነዚህ ክልሎች ውስጥ የአካባቢው ተወላጅ ያልሆነ ህዝብ የክልሉ ባለቤት ስላልሆነ፣ በሃይል እንዲፈናቀል ይደረጋል፡፡ መስከረም አበራ በቅርቡ – በደቡብ ኢትዮጵያ የተፈፀሙ አሰቃቂ የግብረ-ሰይልና ዕልቂት ተግባራትን በዝርዝር ገልፃቸዋለች፡፡

ለ100 ዓመታት ባለብዙ ህብር ኢትዮጵያውያን መካከል የዘለቀው መከባበርና መቻቻል፣ የፍቅርና አንድነት መፈክርን አንግበው በመጡት ጠ.ሚ አብይ ፊት እየተናደ ነው፡፡ እነዚህ መፈክሮች በእነዚህ ጭካኔዎች ፊት ባዶ ናቸው፡፡ ዛሬ እንደምናውቀው፣ ሃገሪቱን ከሚነቀንቀው ሰፊ ያለመረጋጋት ስጋት ጋር አስፈሪ የሞትና የውድመት መልዕክቶች ከተለያዩ ጥጎች እየተደመጡ ነው፡፡

እንደየረሃብ ቅድመ-ማስጠንቀቂያ ስርዓት መረብ (FEWS NET) ገለፃ ከሆነ፣ ከጥቅምት እስከ ታህሳስ በደቡብ ኢትዮጵያ የዘነበው የበልግ ዝናብ ከአማካይ በታች በመሆኑ፣ የውሃ መኖር ላይ ሊፈጥር፣ የተወሰኑ አርቢዎች ቶሎ እንዳያገግሙና የግጦሽ ሳር እንዳያገኙ ሊገድባቸው ይችላል፡፡ በዚህም ምክንያት በከብት አርቢ አካባቢዎች ቀውስ ይፈጠራል ተብሎ ሲጠበቅ፣ ደረጃ 3 (IPC 3) የተሰኘ ሃይለኛ የምግብ ዕጥረት ሊከሰት አንደሚችል የመረቡ (FEWS NET) ሪፖርቶች ያሳያሉ፡፡

የየካቲት የUSAID የምግብ ዋስትና ሪፖርት የሚመጡት ወራት ለኢትዮጵያ ጨለምለም ያለ መልክ እንዳላቸው ይናገራል፣

‹‹በኢትዮጵያ የተከሰተው የምግብ ዋስትና ችግር ተፈናቃዩን ህዝብ ጉዳተኛ አድርጎ፣ ሰብዓዊ ዕርዳታዎችን የሚያስገኝ ቢሆንም፣ ድርጅቶች ግን የህይወት-አድን እገዛ ከመስጠት ይስተጓጎላሉ፡፡ ከ2.9 ሚሊዮን ተፈናቃዮች መካከል፣ ከ80 በመቶ በላዩ ለመፈናቀል ገፊ ምክንያት የሆነበት በሃገረቷ የሚታዬው ግጭት ነው፡፡ የዕርዳታ ድርጀቶች አጋጅ መሰናክሎችን – ለምሳሌ፡- ደካማ የመሰረተ-ልማት መኖር፡ – እያለፉ እንደዋስትናው ሁኔታ ሄደው ለተጋላጭ ህዝቦች ዕርዳታ እየሰጡ ነው፡፡ እንደየረሃብ ቅድመ-ማስጠንቀቂያ ስርዓት መረብ (FEWS NET) ገለፃ ከሆነ፣ ከጥቅምት እስከ ታህሳስ በደቡብ ኢትዮጵያ የዘነበው የበልግ ዝናብ ከአማካይ በታች በመሆኑ፣ የውሃ መኖር ላይ ሊፈጥር፣ የተወሰኑ አርቢዎች ቶሎ እንዳያገግሙና የግጦሽ ሳር እንዳያገኙ ሊገድባቸው ይችላል፡፡››

ይህ ውስብስብ አደጋ የሚባለው ነው፤ የተፈጥሮ አደጋ (ድርቅ)ና የሰው-ሰራሽ ጥፋት (ግጭትና በሃይል ማፈናቀል) ሲቀናጁ፡፡

ይህ ሁኔታ – ሚሊዮኖች እየተፈናቀሉና ለጥቃቅን ሃብቶች የሚደረገው ፉክክር ከቀጠለ፣ የተንጋደደውን የፀጥታ አቋም ይበልጥ ያንጋድደዋል፡፡ ኢትዮጵያ ከአንጎላ በመቀጠል፣ ሁለተኛዋ የቻይና ተበዳሪ ስትሆን፣ 13.7 ቢሊዮን ዶላር ዕዳ አለባት – የ2018 ሪፖርት እንድሚገልጠው፡፡ ከዚህም በላ ኢትዮጵያ በተቀመጠላት ገደብ ዕዳዋን መክፈል እንዳልቻለች ጭመጭምታ ይሰማል፣

‹‹ዕዳው የሃገሪቱን ሃገራዊ የምርት መጠን (GDP) 59 በመቶ ያህል በመድረሱ ኢንቨስተሮች ተጨንቀዋል፡፡››

አዲስ አበባ የሚገኘው በአፍሪካ ህብረት የቻይና ሚሲዮን ነሃሴ ድረ-ገፁ ላይ እንዲህ ሲል ተናግሯል፣

‹‹በሃገሪቱ የሚካሄደው የቻይና የኢንቨስትመንት ተቀዛቅዟል፤ የቻይና የውጭ ንግድና ብድር ኢንሹራንስ ኮርፖሬሽንም የኢንቨስትመንት ስራውን ቀንሷል፡፡››

ገዢ ናገር ደሴ መጋቢት 27፣ 2019 ለፋይናንስ ቋሚ ኮሚቴ ባቀረቡት የብሔራዊ ባንክ የስራ አፈፃፀም እንዳረጋገጡት፣ ኢትዮጵያ በወጪ ንግድ 1.64 ቢሊዮን ዶላር ስታገኝ፣ ለገቢ ንግድ ግን 10.5 ቢሊዮን ዶላር አውጥታለች፣ ወደ 5000 በመቶ የሚጠጋ ጉድለት ታይቷል፡፡ ምንም እንኳ ከፍተኛ የወጪና ገቢ ጉድለት ቢኖርም፣ ሃገሪቷ የመሰረታዊ ፍላጎቶች፣ የመድሃኒትና ጥሬ ዕቃዎች ዕጥረት ያሰጋታል፡፡ የመጋቢት 31ዱ ‹‹ሪፖርተር›› ጋዜጣ እንደዘገበው፣ የብሔራዊ ባንክ ገዢ የውጭ ምንዛሬ ክምችቱ አነስተኛ እንደሆነና ባሁኑ ሰዓት ሃገሪቷ መድሃኒትና ነዳጅ ብቻ መግዛት እንደምትችል፣ ሁኔታው አስደንጋጭ መሆኑን ገልጠዋል፡፡ የውጭ ምንዛሬው ከውጭ በሚላክ ገንዘብ፣ በኢትዮጵያ አየር መንገድና በውች ብድርና እርዳታ እንደተሸፈነ ተናግረዋል፡፡ ሃገሪቱ ተጨማሪ ብድሮችን ካላገኘች፣ ምንም ነገር መስራት እንደሚከብዳት ገዢው ተናግረዋል፡፡ በሌላ ቋንቋ፣ ገዢው ሃገሪቷ እንደከሰረች ለፓርላማው አርድተዋል፡፡

በተንሰራፋው አለመረጋጋትና የእንቅስቃሴ ገደብ፣ በሃገሪቱ ዕምነት ማጣት ምክንያት፣ ኢንቨስተሮች ኢትዮጵያ ውስጥ መዋዕለ-ንዋያቸውን ለማፍሰስ ፈቃደኞች አይደሉም፡፡ ገዚው አክለውም 100 ዓመት ያስቆጠረው ልማት ባንክ ኪሳራ ውስጥ ለመዘፈቅ እንደተቃረበ ገልጠዋል፡፡ እንደእርሳቸው አገላለፅ፣ ከ46.17 ቢሊዮን ብድር ውስጥ 39.45 በመቶው የማይመለስ ብድር ነው፤ ይህ በሃገሪቱ ያለውን የሙስና ጥግ ያሳያል፡፡ በመጀመሪያዎቹ 3 የበጀት ወራት 344 ሚሊዮን ብር ማጣቱን አስረድተዋል፡፡ ሲያጠቃልሉም፣ ባንኩ ተሟግቶ ብድሩን ለማስመለስ አቅም እንዳጠረው ተናግረዋል፡፡

የጃዋር ያልተለመደ ሁናቴ

ጠ.ሚ አብይ በተሰላ ውሳኔ፣ በፓርቲያቸው ውስጥ የሚገኙ አፈንጋጮችን ለማባበል የዘውግ ፖለቲካን ካርድ እየተጠቀሙ ናቸው፡፡ በዚህም ምክንያት የእርሳቸው የዘውግ መሰረት ተነቃቅቶ፣ የተሰጣቸው ግምት ከፍ ብሏል፡፡ በጋለ ስሜት የዘውግና የሃይማኖት ፅንፈኝነትን የሚያራምደው፣ የእርሳቸው ባልደረባ ጃዋር መሃመድ በህጋዊ መንገድ ኢትዮጵያ ውስጥ እንዲንቀሳቀስ ከአሜሪካ፣ ሚኒሶታ ተጋብዞ መጥቷል፡፡ ኦሮሞ ሚዲያ ኔትዎርክ (OMN) በሚሊዮን የሚገመቱ ተከታዮች አሉት፡፡ ሚሊዮናት ኢትዮጵያውያን ጣቢያው አንዲዘጋ ያቀረቡት ልመና ቢኖርም፣ ጠ.ሚ አብይ አንድም ቀን ጣቢያውን ተችተው አያውቁም፤ ጣቢያው እንደፈለገው እንዲንቀሳቀስ ትተውታል፡፡

አብይ የሚዲያውን ስራ አስፈፃሚ፣ ጃዋር መሃመድና OMNን በህጋዊ መንገድ ተመዝግበው በዘውግና ሃይማኖት የተቃኘ የጥላቻ ንግግር እንዲያሰራጩ ፈቅደውላቸዋል፡፡ ጠ.ሚ አብይ ጃዋርን መታገሳቸው ግራ ያጋባል፡፡ እንደጃዋር ለመሰሉ ፅንፈኞች ያልተረጋገጠ የፖለቲካ ሃይል መስጠት፣ የፖለቲካውን ምህዳር ውጥረት ይበልጡኑ ከማባባስ በቀር፣ ምንም አይፈይድም፡፡ የተወሰኑ የፖለቲካ ታዛቢዎች እንደሚጠረጥሩት፣ በጠ.ሚውና በጃዋር መካከል፣ ግልፅ የሆነ ወይም ያልሆነ መናበብ አለ፡፡ ነገሩ አንዲህ ከሆነ፣ ጠ.ሚ አብይ የጃዋር ፅንፈኛ አስተሳሰብ ወጣቱን – በተለይ ኦሮሞ ክልል የሚኖረውን – እንዲያነሳሳ ፈቅደዋል ማለት ነው፡፡ በሌላ ሃገር፣ ጃዋር በፈፀመው የማነሳሳት ወንጀል፣ እናም በሽብርተኝነት ተከስሶ፣ ዕድሜውን እስር ቤት ይጨርስ ነበር፡፡

ቀደም ብዬ በፃፍኩት ፅሁፍ፣ OMN የሩዋንዳን የዘር ፍጅት ያጋጋለው የጥላቻ ራዲዮን – Radio Television Libre Milles Collines (RTLM)ን አንደሚያስታውሰኝ ገልጬአለሁ፡፡ የራዲዮ ጣቢያው ዓለም ‹‹የሩዋንዳውያንን ህብራዊ ልማት መፍጠር›› ቢሆንም፣ ዓላማው ግን ከዕውነታው ጋር የተራራቀ ነው፡፡ የተቋቋመውና በገንዘብ የሚደገፈው በሁቱ ፅንፈኞች ሲሆን፣ የሩዋንዳን ህዝብ ጥላቻና ግጭት በመንዛት ለዘር ፍጅት ለማዘጋጀት የታሰበ ነው፡፡ አደጋውን የተረዱ ወገኖች ስርጭቱ እንዲቋረጥ ለዓለም-አቀፍ ማህበረሰብ የእገዛ ጥሪ አቅርበው ነበር፡፡ ነገር ግን የምዕራብ ዲፕሎማቶችን አሳምኖ፣ ጉዳዩ በአንክሮ አንዲታይ ማስደረግ አልተቻለም፡፡ እንዲያውም ጣቢያውን ከቁብ አልቆጠሩትም፣ ካናዳዊው ጄኔራል ሮሚዮ ዳላየር – በሩዋንዳ የተመድ የሰላም አስከባሪ ሰራዊ አዛዥ – በዘር ፍጅቱ ወቅት – ‹‹ስርጭቱን አስቁመን፣ በሰላምና እርቅ ላይ ያተኮሩ መልዕክቶችን ብናስተላልፍ፣ በሚፈጠሩ ሁኔታዎች ላይ ጉልህ ተፅዕኖ ያሳርፋሉ፡፡›› ብሎ ቢናገሩም፣ ምክራቸው ተቀባይነትን አላገኘም፡፡ ተመድና ዓለም-አቀፉ ማህበረ-ሰብ ቀድመው የዘር ፍጅቱን ለመከላከል እርምጃ ባለመውሰዳቸው፣ ውርደትና እፍረት ጋር ሲፀፅታቸው ይኖራል፡፡ ሃሳብን በነፃነት በመግለፅና በጥላቻ ንግግር፣ በንግግርና በመቀስቀስ መካከል፣ ቀይ መስመር አለ፡፡ በዓለም-አቀፍ የህግ ማዕቀፎች ውስጥ በደንብ ተገልጧል፡፡

ጃዋር ለተከታዮቹ ክርስቲያኖች ስጋት እንደሆኑ ሲናገር ተቀድቷል፡፡ ሩዋንዳ ውስጥ እንደነበረው ‹‹ኢንተርሃምዌይ›› ዓይነት፣ ጃዋር ራሳቸውን ‹‹ቄሮ›› ብለው የሚጠሩ ወጣት ኦሮሞዎችን በመመልመል፣ ግድያን፣ ዘረፋንና በሃገሪቱ የፍርሃት ድባብ ማስፈንን – የመሳሰሉ ቆሻሻ ድርጊቶችን እንዲፈፅሙ አደራጅቷቸዋል፡፡

አንድ መኩሪያ የሚባሉ ኢትዮጵያዊ ECADF ድረ-ገፅ ላይ እንደፃፉት፣

‹‹የቄሮ ወጣቶች ቆንጭራና ሌሎች የቤት ውስጥ መሳሪያዎችን ሲያወዛውዙ የሚያሳዩ ምስሎችን መመልከት፣ እጅግ ይዘገንናል፡፡ እጃቸውን ከጭንቅላታቸው በላይ አጣምረው – በሌሎች ኢትዮጵያውያን ከተወደዱና ከተሞገሱ – ሰላማዊ ሰልፍ ካደረጉ ወጣቶች ይልቅ ጨካኙን – ቦኮ ሃራምን ትዝ ያስብላሉ፡፡ የቄሮ ወጣቶች ኢትዮጵያውያን፣ ነገር ግን የሌሎችን ቆሻሻ ስራ ለመስራትና በዛው ጉዞ  መጉደፍ የሚፈልጉ ናቸው፡፡ ዕድሜ ለጃዋር የሚመቻቸውን ሰፈር አግኝተዋል፡፡››

በሺህዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ‹‹ኢትዮጵያ ውስጥ የዘውግ ግጭት የሚቀሰቅሰው OMN ሚዲያ እንዲታገድና ስራ አስፈፃሚው ጃዋር መሃመድ ለሰራው ስራ ተይዞ እንዲጠየቅ›› ፊርማ አሰባስበው ለሚኒሶታ አቃቤ ህግ ፅ/ቤትና ለአሜሪካ አቃቤ ህግ ፅ/ቤት አስገብተዋል፡፡

አብይ አህመድ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ከሆኑ ጀምሮ፣ የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ መንግስት ከሁለት ሃይል የሚመነጭ የተዛመተ ስርዓት-አልበኝነትን መቆጣጠር ባለመቻሉ፣ ኢትዮጵያውያን በጉልህ ተሰላችተዋል፡፡ በጃዋር መሃመድ የሚመራው የ‹‹ቄሮ›› ንቅናቄ በተጨባጭ የሚታይ ሃይል አሳርፎ፣ በተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች – በፈቃዱ – የመንግስትን ሃይል እየተፈታተነ ነው፡፡

የወደፊቱ መንገድ

ያለጉልህና በደንብ የታሰበባቸው ውሳኔዎች፣ ከዚህ አሳዛኝ ሁኔት መውጣት አይቻልም፡፡ ውሳኔዎቹ በርካታ የሚያስከትሏቸው ውጤቶች ቢኖሩም፣ ግን የትክክለኛና ምክንያታዊ ውሳኔዎችን መጪ-ውጤት መቆጣጠሩ ይሻላል -የእርስ በርስ ጦርነትና የዘር ፍጅትን ለመቆጣጠር ከመሞከር ይልቅ፡፡ ጠ.ሚ አብይ ስለፍቅርና ‹‹መደመር›› ስለሚሰኘው – ትርጓሜውም ‹‹አብሮነት›› ስለሚለው ፍልስፍና የሚሰጧቸው ሰበካዎች ህዝቡን አሰልችተዋል፡፡ አንዳንድ ሶች ስለፍቅርና ‹‹መደመር›› የሚሰጧቸው ሰበካዎች ማታለያ እንደሆኑ ይናገራሉ፤ ህዝቡን ከጎናቸው ለማሰለፍ የተጠቀሟቸው የማዘናጊያ ሰበካዎች ናቸው፡፡ በአሁኑ ጊዜ፣ እርሳቸው በዕውናዊው ዓለም ውስጥ ያሉ አይመስሉም፤ ፍቅርና ‹‹መደመር›› ገዢ ፖሊሲዎች ሊሆኑ አይችሉም፡፡ በዕውናዊው ፖለቲካ፣ ሃገረ-መንግስታት በብሔራዊ ጥቅም (የህዝብ ፍላጎቶች) የተቃኙ ናቸው፡፡ እንደዚህ ዓይነት ረቂቅ ዕሴቶች የብሔራዊ ጥቅሞችን አስፈላጊነት ለማሳዬት የሚጠቅሙ እንጂ ፖሊሲዎች አይደሉም፡፡ እነዚህ በዕውናዊው የፖለቲካ ጨዋታ ውስጥ የሌሉ ተረታዊ ሃሳቦችና መፈክሮች ናቸው፡፡ እነዚህ በዕምነት ሰዎች ዘንድ ያሉ ናቸው፡፡

የፖለቲካ መሪዎች የተግባር ሰው መሆን አለባቸው፡፡ መሪው የሚያረቅቀው ንድፈ-ሃሳብ አዋጪና ተሰሪ መሆን አለበት፡፡ ተግባራዊነት አመክንዮና ምክንያት ላይ መመስረት አለበት፤ ረቂቅ ሃሳቦች ላይ ሳይሆን፡፡ የሚያስፈልጉት ጉልህ ውሳኔዎች ናቸው፡፡ ጠ.ሚው መጀመሪያ ራሳቸውን ከዘውግ ፖለቲካ ማውጣት አለባቸው፡፡ የኢትዮጵያን አጀንዳ መቅረፅና ምሳሌ ማድረግ አለባቸው፡፡ ቀላል ውሳኔ ባይሆንም፣ ግን እጅግ አስፈላጊ ነው፡፡ በቀውስ ሰዓት ስልጣን ላይ የሚሰየሙ መሪዎች ዋና ችግር ይሄ ነው፡፡

ጠ.ሚ አብ ከአንድ ዓመት በኋላ ምርጫ ለማካሄድ ቃል ገብተዋል፡፡ በአብዛኛው ሰዉ የተስማማው፣ በዚህ ወቅት ምርጫዎች እንደማይካሄዱ ነው፡፡ ምርጫዎችን ህዝቡ ለአስርት ዓመታት እንዲወገድ በተፋለመበት – በአሁኑ ህገ-መንግስት ማካሄድ ቢቻል እንኳ፣ የኢትዮጵያን ውስብስብ ችግር መፍታት አይቻልም፡፡

ብዙ ኢትዮጵያውያን አማራጮች እንደሌሉ አስበው ይፈራሉ፡፡ አማራጮች አሉ፡፡ ህዝቡ የረዳት-አልባነት ስሜት ሊሰማው አይገባም፡፡ ከመዘግየቱ በፊት፣ አማራጮች ከነፃና ክፍት ውይይትና ክርክር ይመነጫሉ፡፡ በፀረ-ዲሞክራሲ ወይም በፍፁም አምባገነን መንግስታት – ልክ ኢትዮጵያ እንደነበረው – ፍርሃትና መጠራጠርን በማንገስ፣ ህዝቡ አሁን ካለው ሁኔታ የሚሻል አማራጭ እንደሌለ እንዲያምን ያደርጋሉ፡፡ በነዚህ ሃገራት የሚገኙ በቂ አማራጮች የሉም፡፡ ይህ በኢትዮጵያና በሌሎች ሃገራት የታዬ ታሪክ ነው፡፡ ነገር ግን ይህ ሰበብ ብቻ ነፃና ክፍት ውይይቶች እንዳይካሄዱ ዕንቅፋት አይሆንም፤ በግልፅ ሁኔታ፡፡ አማራጮች ከእንደዚህ ዓይነቶቹ ውይይቶች ይመነጫሉ፡፡ የሲቪል ማህበረ-ሰቦችና ተቺ ቡድኖች ይህ እንዲካሄድ ያስችላሉ፡፡ የሲቪል ማህበረ-ሰቡና ነፃው ፕሬስ እንዲህ ዓይነት ስብሰባዎች እንዲደረጉ መወትወትና ኢትዮጵያ አሁን ላለችበት ሁኔታ የሚጠቅም ተቺ አማራጮችን ማቅረብ አለባቸው፡፡

ኢትዮጵያ የሚያስፈልጋት የኢትዮጵያን አንድነትና ኢትዮጵያዊነትን የሚያራምድ መሪ ነው፡፡ ኢትዮጵያ ሰፊ ልቦና፣ ትጉህ፣ አሳቢና ግልፅ የሆነ፣ ትሁትም የሆነ ፕሬዝደንት ያስፈልጋታል፡፡ አብይ ወደ ስልጣን የመጡት ለውስብስብ የኢትዮጵያ ችግሮች ቀላል መፍትሄ ይዞ ነው፡፡ ላለፉት ጥቂት ዓመታት በአመፅ የተከፈለው የብዙዎች ነፍስ ወደ ዴሞክራሲ ሽግግር እንዲደረግ ነው፡፡ አብይ በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ ሃይለኛ ድጋፍ ተችሯቸው፣ ዕድል ተሰጥቷቸው ነበር፡፡ የህዝቡን ድጋፍ ፅንፈኝነትንና የዘውግ ፖለቲካን የሚያስወግድ አጀንዳን ለማስፈፀም አልተጠቀሙበትም፡፡

የኢትዮጵያ ችግር በፊትም – አሁንም ውስበስብ በመሆኑ፣ ሰፊ አጀንዳ፣ ጥበብና አቅም ያለውና ምክር ለመቀበል ፈቃደኛ የሆነ፣ የሚከራከርና የኢትዮጵያን ህዝብ የሚያፀና ሃሳብ የሚያራምድ መሪ ያስፈልጋል፡፡ ስብከቶችን የማይሰማ መሪ ያስፈልጋል፡፡ በዕድሜና በልምድ የበሰሉ፣ እርሱን/ እርሷን መሞገት የሚችሉ የባለሙያዎች ስብስብ የሚያሰባስብ/ የምታሰባስብ መሪ ያስፈልጋል፤ ለመማርም ዝግጁ የሆነ፡፡ ጠ.ሚው ህገ-መንግስቱንና ፓርላማውን እንዳለ ማቆየትና አሁን ባለው ሁኔታ እንዲረጉ ይፈልጋሉ፡፡ ከምርጫ በኋላ፣ ህገ-መንግስቱ የተወሰነ እንደሚሻሻል ቃል ገብተዋል፡፡ ግን ህዝብ የሚፈልገው በራሱ ተዘጋጀና የሚቀበለው ህገ-መንግስትና በህገ-መንግስቱ መሰረት የሚካሄድ ምርጫን ነው፤ ከዚህ በጠ.ሚ መለስ ዜናዊ ጊዜ እንደተደረገው ምርጫ አይደለም የሚፈለገው፡፡

በፓርቲያቸው አቋም ምክንያት፣ ጠ.ሚ አብይ ህገ-መንግስቱ እንዲዘልቅ ይፈልጋሉ፡፡ ህገ-መንግስቱ እንዲዘልቅ ይፈልጋሉ፡፡ ህገ-መንግስቱን መቀየር ምናልባት የዘውግ ፌዴራሊዝሙን ሊያጠፋ ይችላል፡፡ ይህ ደግሞ ፓርቲው አይፈልገውም፡፡

ጠ.ሚ አብይ ሁለት አጀንዳዎችን ማስሄድ አይችሉም፤ በዘውግ የተደራጀው ፓርቲያቸውን (ኦዴፓ)ና የኢትዮጵያ አጀንዳ፡፡ እዚህ ላይ ነው ለሰላምና መረጋጋት ሲባል የሚወሰኑ ውሳኔዎች፣ ጥበብና ጀግንነት የሚጠይቁት፡፡ ለዚህም ነው የመጀመሪያው – ለሃገሪቱ አስፈላጊው ውሳኔ ጠ.ሚ አብይ ከስልጣናቸው መልቀቅና ኢህአዴግ ኦሮሞም – አማራም ያልሆነ መሪ በመምረጥ ሃገሪቷን ማሸጋገር ያለበት፡፡

ጠ.ሚ አብይ ራሳቸውንና ሃገሪቷን ማዳን ከፈለጉ ጥሩው አማራጭ ይህ ነው፡፡ ይህ ውሳኔ ሁኔታውን በተረጋጋ ስሜት መገምገምና ባለመወሰኑ የሚመጡ ውጤቶችን ማጥናት ያስፈልጋል፡፡ ጠ.ሚ አብይና ኦዴፓ ይህንን አማራጭ መቀበል ካልፈለጉ፣ ባለፈው ታህሳስ አዲስ አበባ 7ኛው የቪዥን ኢትዮጵያ ስብሰባ ላይ ያቀረብኩት ፍኖተ-ካርታ፣ ሁለተኛውን አማራጭ መተግበር ይችላሉ፡፡ ጠ.ሚው ህገ-መንግስቱን መሻር፣ ፓርላማውን መበተንና በአዋጅ የተቋቋመ የሽግግር መንግስት መምራት አለባቸው፡፡ እርሳቸው የዘውግ አጀንዳ እንዲተው፣ አንድ የሚያደርግ አጀንዳ እንዲይዙና በእርሳቸው ሳይሆን አዲስ በተመረጠው የሽግግር መንግስቱ ጉባዔ በተረቀቀ ፍኖተ-ካርታ እንዲመሩ ይደረጋል፡፡ እነዚህ ጉልህ እንቅስቃሴዎች ሲሆኑ፣ ከዘውግ መሪዎችና ህዝቡ ጋር የምስጢር ድርድሮችና ግልፅ ውይይቶች ያስፈልጋሉ፡፡

ይህ የማይደረግ ከሆነ፣ የመጨረሻው አማራጭ በአፍሪካ ህብረት፣ በተመድና በዓለም-አቀፉ ማህበረ-ሰብ አስማሚነትና ጫና-ፈጣሪነት ተስፋ በማድረግ ተቀናቃኝ ሃይሎች ወደመተባበር እንዲመቱና በሃገሪቱ የእርስ በርስ ግጭትን የማድረግ ጉዳት በማስገንዘብ አወያይቶ የሽግግር መንግስት እንዲቋቋም ማድረግ ነው፡፡

ማጠቃለያ

25ኛውን የሩዋንዳ የዘር ፍጅት መታሰቢያ ለመታደም፣ ባለፈው ሳምንት ጠ.ሚ አብይ አህመድ ሩዋንዳ ነበሩ፡፡ በሚሊዮናት የሚቆጠሩ ሩዋንዳውያን በዘር ማፅዳቱ ከመገደላቸው በፊት፣ ሩዋንዳ ውስጥ ስለነበረው በጥላቻ የተሞላ የፖለቲካ ምህዳርና ስላመጣቸው ችግሮች፣ ጥሩ ንቃት እንዳገኙ ተስፋ አለኝ፡፡

የዛሬ 25 ዓመት ሩዋንዳ ነበርኩ፡፡ በጣም አሳዛኝና አስጨናቂ የህይወት ልምዴ ነበረ፡፡ በግሌ ብዙ ተምሬአለሁ፡፡ ጠ.ሚ አህመድ ከተማሯቸው ትምህርቶች ጋር እንደተመለሱ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡ በሃያዎቹ የዕድሜ መጀመሪያ እያሉ፣ የተመድ ሰላም አስከባሪ ሆነው፣ እዛው ነበሩ፡፡ ያኔ በጣም ወጣትና በውትድርና ስራ ላይ ሆነውም፣ የዘር ፍጅቱን ስረ-ምክንያት ለማወቅ ሞክረው ይሆናል፡፡ አሁን ላይ ህዝቡ ከእርሳቸው ኢትዮጵያን ከዚህ አሰቃቂ ልምድ የሚያወጣ ፈጣን ውሳኔዎች እንዲወስኑ ይፈልጋል፡፡ ፖል ካጋሜ ያደረጉት ይህንን ነበር፡፡ አስፈላጊ ውሳኔዎችን በመወሰን፣ ብጥብጦችንና የዘር ፍጅትን በመከላከል፣ መላ ሃገሪቱን ተቆጣጥረው ነበር፡፡ ለውሳኔዎቻቸው በገሚሱ ወገን ከፍተኛ ዕውቅና ባይሰጥላቸውም፣ ነገር ግን ሩዋንዳን ከአሰቃቂው ገጠመኝ ከወጣች በኋላ የምታብረቀርቅ ሃገር አድርገዋታል፡፡ ጠንካራና ወቅቱ የሚፈለገው ዓይነት መሪ ነበሩ፡፡ ህዝቡን ዕኩል የሚያስተዳድሩና ቀናዒ የሆኑ ሰዎች በዙሪያቸው አሉ፡፡

የሩዋንዳን የዘር ፍጅት ቀድሞ መከላከል ይቻል ነበር፡፡ ከቁጥጥር የወጣ ጥላቻና ውጥረት ውጤት አይደለም፡፡ የጌታ ቁጣም አይደለም፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ እንዳለው፣ ሆን ተብሎ በልሂቃኑ ፍላጎት፣ በስልጣን ላይ ለመቆዬት ሲባል፣ ጥላቻን፣ ፍርሃትንና መከፋፈልን በማዛመታቸው የመጣ ውጤት ነው፡፡ ሂዩማን ራይትስ ዎች 2017 ላይ እንደገለፀው፣

‹‹ሃገሪቷን በጥብቅ ተቆጣጥረው፣ የራሳቸውን መዋቅርና ስልጣን ተጠቅመው ነበር ጭፍጨፋውን የፈፀሙት፡፡ እንደአስተባባሪዎቹ ፍጅቱን የሚፈፅሙት ገዳዮች፣ መንፈስ አልነበሩም፣ ለሚያዝዟቸው ሃይሎች የሚገዙ ሎሌዎች አልነበሩም፡፡ የሰይጣንን ስራ ለመስራት የመረጡ ሰዎች ነበሩ…እነዚህ ጥቂቶች የዘውግ ክፍፍል ስትራቴጂን ወደ ዘር ፍጅት ለወጡት፡፡ አስር ሺህዎች በፍራቻ፣ በጥላቻ ወይም ጥቅም ለማግኘት ሲሉ፣ ምርጫቸውን በቶሎና በቀላሉ መረጡ፡፡ ለግድያ፣ ለአስገድዶ መድፈር፣ ለዘረፋና ለውድመት የመጀመሪያዎች ነበሩ፡፡ ያለምንም ማቅማማትና ፀፀት ቱትሲዎችን በየጊዜውና እስከመጨረሻው ድረስ ሲያጠቁ ነበር፡፡ ብዙ ተጠቂዎችን ስጋት ውስጥ ጥለው፣ እነርሱ ድርጊቱን በመፈፀም ይደሰቱ ነበር፡፡››

የሩዋንዳ የዘር ፍጅት ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት ዕልቂትን (ሆሎከስትን) ‹‹አይደገምም!›› ከተባለ በኋላ፣ ምን ያህል ሰዎች ለዘር ፍጅት እንደሚነሳሱ ያሳዬ ነበር፡፡ በዚህ ኢትዮጵያ ውስጥ መረጋጋት በሌለበት ወቅት መሪዎች ከፍተኛ ሃላፊነት አለባቸው፡፡ ተጨማሪ የፖለቲካ ጥበብና ከፍተኛ የሃላፊነት ስሜት ያስፈልጋቸዋል፡፡

የኢትዮጵያ ህዝብ ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ጎን እንዲሰለፍ ፅሁፍ ከፃፉ ሰዎች፣ አንዱ ነበርኩ፡፡ እንደብዙ ሰው፣ ሁኔታዎች በጥልቀት ከተመለከትኩ በኋላ፣ ጠ.ሚው ላለፈው አንድ ዓመት ያራመዱት ፖሊሲዎች መተቸት እንዳለባቸው አምኛለሁ፡፡ ለመናገር ጊዜው አሁን ነው፡፡ ፅፌው በብዙ የኢትዮጵያ ድረ-ገፆች ላይ ግንቦት 31፣ 2018 የወጣው ፅሁፍ ላይ እንዲህ ብዬ ነበር፣

‹‹የፍሃትን መሰናክል በደ/ር አብይና ከጎናቸው ባለው ህዝብ፣ እንዲሁም እርሳቸው በህዝቡ ላይ ያሳደሩት ዕምነት መዘለሉ፤ የመጨረሻው ስኬት የሚመሰረትበት ነው፡፡ የኢትዮጵያ ህዝብ ያንን ፍርሃት አልፎታል፡፡ አሁን ጥያቄው ‘ጠ/ሚ አብይና ቡድናቸው ፍርሃቱን አልፎ፣ የተወሰኑ ሂደቶችን ተሻግሮ ወደ ዴሞክራሲያዊ ሽግግር ማምራት ይቻላል?’ የሚል ነው፡፡ እርሳቸው ከወደቁ ማንም ሰው ማንንም ሳይሆን ራሱን መውቀስ አለበት፡፡ አብዛኛው ህዝብ ከምንጊዜውም በላይ አንድ ሆኗል፤ እንዲሁም የመጨረሻና የመደምደሚያ ውጤቱን እስኪያይ ድረስ፣ ትግሉን ከመቀጠል ወደኋላ አይ

1 COMMENT

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here