Home News and Views የታገቱ እህቶቻችን እና አክራሪ ብሄርተኞች

የታገቱ እህቶቻችን እና አክራሪ ብሄርተኞች [ ዶ¦ር በቃሉ አጥናፉ ታዬ፟፟ ኮተቤ ሜትሮፖሊታን ዩኒቨርሲቲ]

 

በአንድ ሉዓላዊት አገር ላይ አጋች ኃይል አቅም ፈጥሮ ዜጎችን ማገት ከቻል የአገሪቱን የመከላከያ አቅም ጥያቄ ውስጥ የሚያስገባ ጉዳይ ነው፡፡ የአጋች-ታጋች ክስተት አብዛኛውን ጊዜ የጨነገፉ አገራት መገለጫ ባህሪ ነው፡፡  ዳሩ ግን በእኛ አገር የሴት እህቶቻችን የዜግነት መብት ተገፎ በአጋቾች ስር ለሁለት ወራት ያህል መቆየታቸው የመንግስትንም ሆነ የመከላከያ አቅምን ጥያቄ ውስጥ የሚያስገባ ጉዳይ ሳይሆን ሸፍጥ የተሞላበትን የፖለቲካ ሂደት አመልካች ነው፡፡

የኢትዬጲያ ሰራዊት በዓለም አቀፍ የሰላም አስከባሪ በግንባር ቀደምትነት የሚጠቀስ ኃይል እንደሆነ ይታወቃል፡፡ ታዲያ ይህ ሰራዊት በተወሰኑ አክራሪ ብሄርተኞች የተያዙትን እህቶች ለማስለቀቅ አቅም ያንሰዋል ብሎ መገመት የኢትዬጲያ የተንኮል ፖለቲካ ካለመረዳት የሚመነጭ እሳቤ ነው፡፡ ይህ ጉዳይ በይበልጥ የሚመለከታቸው የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት እና የፌዴራል መንግስቱ መንግስታዊ ተቋማት (የመከላከያ ሚኒስቴር መ/ቤት፤ የፍትህ ሚኒስቴር) በጎሳ ፖለቲካ ጥብቆ ተኮትኩተው ያደጉ ስለሆን ብሄርን እንጅ ሰብዓዊነትን አያውቁም፡፡ አባቱ ዳኛ ልጁ ቀማኛ የሚለው ብሂል ለዚህ ጉዳይ ጥሩ ማሳያ ነው፡፡

የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት እና በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ውስጥ የሚገኘው የደንቢደሎ ዩኒቨርስቲ ኃላፊዎች ጉዳዩን እንደማያውቁት ሲገልፁ ሲሰማ ደግሞ በእኛ እና በነሱ የፖለቲካ ፅንፈኝነት ተጠልፈው ሰብዓዊነት ክዶዓቸው፣ ዕውነት ከአዕምሮዓቸው እንደፈረጠጠች እንረዳለን፡፡

ከረጅም ጊዜ ዝምታ በኃላ  የፌዴራል መንግስቱ ወይም የጠቅላይ ሚኒስቴሩ ፕረስ ሴክሬታሪያት ኃላፊ አቶ ንጉሱ ጥላሁን በሚዲያ ቀርበው ታጋቾች ተፈተዋል ብለው ስለቦታው ክብር ሳይጠነቀቁ ሲዋሹ ስንሰማ የስርዓቱ አስከፊነት እስከ አጥንታችን ዘልቆ ይሰማናል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ  የኢትዬጲያው የአጋች-ታጋች ሰቆቃ የዓለም አቀፍ የዘገባ ሽፋን እንዳያገኝ ጉዳዩን ለመሸፋፈን የሚደረገው ጥረት እጅጉን ያሳዝናል፡፡ እ.ኤ.አ.በ2014 በናይጀሪያ ፅንፈኛው የቦኩ-ሀራም ቡድን የታገቱትን ተማሪ ልጃገረዶች ለማስለቀቅ አለም አቀፍ ማህበረሰቡ ሰፊ ርብርብ አድርጎ ነበር፡፡ የኦባማ ባለቤት ሚሸን ኦባማም በሴት ልጆች ላይ የተካሄደውን ግፍ አውግዛ ነበር፡፡ ኢትዬጲያዊ ሴት ባለስልጣናት ምነው አፋችሁ ተለጎመ? ርዕሰ- ብሄርዋ ሴት ናቸው፣ የፍ/ቤት ፕረዘዳንትዋ ሴት ናቸው፣የሰላም ሚኒስቴሯ ሴት ናቸው)፣ ከ50% በላይ በሴቶች የተሞላ ካቢኔ እንዳለ ይታወቃል፤ ታዲያ ምነው ለነዚህ እህቶች መጮህ ተሳናችሁ? የእምነት ተቋማትስ የት ነው ያላችሁት? የተቃዋሚ ፓርቲዎችስ የት ገባችሁ? አዴፓስ እወክለዋለሁ የምትለውን አማራ ከማስጨረስ መቸ ነው የምትታቀበው? በርካታ አገር በቀል ሴት እና ወንድ ምሁራንስ የት ናችሁ?

ከብሄር እና ከሀይማኖት ማንነታችን ይልቅ ሰብዓዊ ማንነታችን በልጦብን ለተጠቁ ዜጎች ድምፅ መሆን ካልቻልነ፣የዜጎቻችንን ህመም እንደ ራሳችን ህመም፣ ቁስላቸውን እንደ ቁስላችን ሊሰማን ካልቻለ፣ በታገቱት ሴት ተማሪዎችና በቤተሰቦቻቸው ቦታ ሁነን ስሜቱን መጋራት ካልችልን፣ ሰው የመሆናችን ሚስጥር የቱ ጋ ነው?

ታጋች ሴት ተማሪዎችና ቤተሰቦቻቸው ክፉ ቀን ገጥሟው፣ ሰሚ ጀሮ አጥተው፣ ከደመና በታች ረዳት ርቋቸው፣ ለልባቸው ጥያቄ መልስ ተነፍጎዓቸው፣ የአንጀታቸውን ልቅሶ የሚያቋቁማቸው ጠፍቶ ግራ በተጋቡበት ጊዜ እንዴት ለድምፅ አልባዎች ድምፅ ለመሆን ቢያንስ እንዴት መጮህ አቃተን?   ወደድንም ጠላንም እንደ ሰው ማሰቡ ነው የሚሻለን፤ እባካችው ሁላችንም እንጩህ ድምጽ እንሁናቸው፡፡

 

2 COMMENTS

  1. Most of the abducted students are in a witness protection program living with a different identity at undisclosed locations , just for the sake of their safety . Since all the abducted students were single not married with no children of their own it was deemed that none of their loved ones should join them in the witness protection program .
    Few of them agreed to join the Ethiopian military training using their new identities .

  2. ONCE AGAIN AS ALWAYS ADDIS ABABA PEOPLE ARE DOOMED TO STAY PERMANENTLY DENIED FROM HOLDING PROTEST UNDER PROSPERITY PARTY. THE PROTEST ABOUT ABDUCTED GIRLS GOT DENIED BY PM ABIY AHMED.CLAIMING AFRICAN UNION SUMMIT WHICH IS A WEEK AWAY WILL BE DISRUPTED BY THE PROTEST SCHEDULED TO BE HELD A WEEK EARLY.

    ORTHODOX CHURCH , BALDRAS , ADDIS ABABA UNIVERSITY STUDENTS …. ARE DENIED PROTEST PERMITS BY PROSPERITY PARTY.

    IT IS TIME FOR ADDIS ABSBA PEOPLE TO START NON VIOLENT RESISTANCE (NVR) AGAINST PROSPERITY PARTY PP BY STAYING HOME FOR ONE DAY OR MORE DAYS AND DIASPORAS SHOULD START CAMPAIGN TO BOYCOTT SENDING REMITTANCE MONEY FROM DIASPORA UNTIL HUMAN RIGHTS OF ETHIOPIANS SUCH AS ADDIS ABABA PEOPLE’S FREEDOM OF EXPRESSION IS RESPECTED .

    https://www.ethiopianregistrar.com/amharic/የራሳቸውን-ሀይማኖት-በሚያስፋፉ-ባለስል/

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here