Home News and Views ዳንሻ ዲቪዥን የሰፈሩትን ከ30 ሺህ በላይ የድሮ የትህነግ(ሕወሓት) ተዋጊዎች መንግስት በአስቸኳይ ትጥቅ...

ዳንሻ ዲቪዥን የሰፈሩትን ከ30 ሺህ በላይ የድሮ የትህነግ(ሕወሓት) ተዋጊዎች መንግስት በአስቸኳይ ትጥቅ ያስፈታቸው !

መከላከያ ሰራዊቱ ዳግመኛ እንዳይጠቃ! – ጌታቸው ሽፈራው
መከላከያ ሰራዊቱ የተጠቃው መለዮውን በለበሱት፣ ከአሁን ቀደም አብረውት ጦር ግንባር በተሰለፉት፣ ወንድሞቸ ናቸው በሚላቸው ባንዳዎች ነው። አሁን ከዚህ የባሰ ስጋት አለበት። ዳንሻ “ዲቪዥን” የሚባለው የትህነግ ልዩ ኃይል ለቅቆ ወጥቷል። ይሁንና ዲቪዥን የተባለው ቦታ መከላከያ ሰራዊቱን ካጠቃው ከሃዲም፣ ከትህነግ ልዩ ኃይልም የባሰ አረመኔና አሸባሪ ኃይል ያለበት ቦታ ነው።
ዲቪዥን ከ30 ሺህ በላይ የድሮ የትህነግ ተዋጊዎች የሰፈሩበት ቦታ ነው። እነዚህ ሰዎች የሰፈሩት ከእነ ሙሉ ትጥቃቸው ነው። ይህ ብቻ ግን አይደለም። በርካታ ንፁሃን የሚገረፉበት፣ የሚገደሉበት፣ የሚሰቃዩበት ከዚህ አካባቢ ነው። እነዚህ የቀድሞ ታጋዮች ከእነ ሙሉ ትጥቃቸው የሰፈሩት ለትህነግ ደጀንነት ነው። ለረዥም ጊዜ ወደ አማራ ክልልም ሆነ ወደሌሎች አካባቢዎች በርካታ አሸባሪ የሚሰለጥንበት አካባቢ ነው። ከትግራይ ወደሌላው አካባቢ የሚሄውን አሸባሪ የሚያስጠልሉትና ከትግራይ የመጣውን የሚያስጠልሉበት እነዚህ ታጣቂዎች ናቸው።
ሰሞኑን አዲስ አበባ ውስጥ ለትህነግ የሚሰሩ ተገኙ ተብለዋል። አዲስ አበባ ላይ የተያዙት ሲቪሎች ናቸው። ዲቪዥን ላይ ያለው በቂ ትጥቅ የያዘ የእነ ስብሃት ነጋ ስነልቦና ያለው አጥፊ ኃይል ነው። በተመሳሳይ በየክልሉ በርካታ አሸባሪዎች ተያዙ እየተባለ ነው። አሸባሪዎቹ ከመቀሌና ከሌላው የትግራይ ክፍል ሲላኩ መጠጊያቸው ዲቪዥን ነው። አካባቢው ሙሉ በሙሉ በታጋዮች የተያዘ በመሆኑ ወልቃይት ውስጥም ሌላው አካባቢ የሚደረገው “ኦፕሬሽን” በሚስጥርና በአስተማማኝነት የሚሰራበት ቦታም ጭምር ነው።
እነ አባይ ፀሐዬን፣ ደብረፅዮን፣ ጌታቸው አሰፋ ወደ ሱዳን ሲያልፉ አምነው የሚቀመጡበት አካባቢ ይሄ ነው። ምን አልባት ከመቀሌም የተሻለ ብዙ ለእይታ ተጋላጭ የማይሆኑበት ይህ የታጋዮች ሰፈር ነው። ይህ ሰፈር ሌላ ወታደራዊ ሰፈር እንጅ የሲቪሎች መኖርያ አይደልም። መቀሌ ካለው የትህነግ አመራር ባልተናነሰ ትህነግ በአንድ ላይ ያለበት ይህ ሰፈር ነው። ወልቃይት ጠገዴን በነፃ ያገኘው ይህ ኃይል ደንበኛውና ለትህነግ እስከ ደም ጠብታ እዋጋለሁ የሚል ነው። ደብረፅዮን ሰራዊት አለው እንጅ በቀጥታ አይዋጋም። ይህኛው ግን ልክ እንደ ደብረፅዮን በድሮው የትህነግ ዘመን እያሰበው፣ መሳርያ ታጥቆ የሚንቀሳቀስ ነው። አባይ ፀሐዬ ሴራ ይጎነጉናል እንጅ አይዋጋም። ይህኛው ሰፈር ያለው ግን ሴረኞችን እያስጠለለ፣ ሽፋን እየሰጠም የሚዋጋ ያ የለየለት የቀድሞው ከአባይ በአስተሳሰብ የማይለው ትህነግ ነው። ይህ ሀይል ከእነ መሳርያው ነው።
መከላከያ ሰራዊቱን ያጠቁት በድሮዎቹ ታጋዮች የተጠለፉት የትግራይ ተወላጅ መከላከያ ሰራዊትና የልዩ ኃይል አባላት ናቸው። በአስተሳሰብ ያጠመቃቸው የድሮው ትህነግ ነው። ዲቪዥን ላይ ያለው ግን ራሱ ትህነግ ነው። ይህ ኃይል ባለመሳርያ ነው። ከእነ ክፉ አስተሳሰቡ ያለ ኃይል ነው።
ዲቪዥን ያለው ኃይል ለመከላከያ ሰራዊቱም ለመንግስትም አስጊ ኃይል ነው። ይህ ኃይል ለነገ የትህነግ የሽብር ተግባር አንደኛው ምንጩ የሚሆን ነው። ይህ ኃይል ነገ ተዘጋጅቶ መከላከያ ሰራዊቱን የሚወጋ ኃይል ነው። ዲቪዥን ላይ መንግስት የተወሰነ ነገሮችን ማድረግ አለበት!
1) ጥብቅ ቁጥጥር ያስፈልጋል። ምን አልባትም ጌታቸው አሰፋን እንኳ ባይሆን ከእነ ጌታቸው አሰፋ ቀጥሎ ያለው የሴረኛ ቡድን ማዘዥያ ጣቢያ ነው። በመሆኑም በየ ክልሎቹ የሚፈፀመውን ሽብር የሚያቀነባብር በርካታ ኃይል በዚህ ሰፈር ያገኛል።
2) ባለፉት 27 አመታት በርካታ ንፁሃን እየታፈኑ ሲገረፉበት የነበረ ሰፈር ነው። ምርመራ ቢደረግ ትህነግ ኢትዮጵያውያን ላይ የፈፀመውን ሰቆቃና ዘር ማጥፋት ማስረጃ ምልክቶችን ያገኝበታል።
3) ዋናዎቹ የትህነግ አባላት የተሰባሰቡበት ይህ ሰፈር በርካታ ሕገወጥ ንግዶች የሚካሄዱበት ነው። ነዋሪዎቹ ከዋና ዋጋዎቹ የትህነግ አመራሮች ጋር ቅርበት ያላቸው በመሆኑ ወደ ሱዳንም ሆነ ወደቀሪው ኢትዮጵያ ክፍል የሚደረጉትን ሕገወጥ ንግዶች የሚያካሂዱ ሞልተዋል። ትህነግ ሕገወጥ ንግድ የሚሰራበትን መስመር ማግኘት ይቻላል። የመሳርያ፣ የገንዘብ ዝውውርና ሌሎችም መስመሮችን ለማግኘት ያስችላል።
4) ከምንም በላይ ግን ይህ ኃይል በርካታ መሳርያ ያለው ኃይል ነው። መከላከያ ሰራዊቱን ዳግመኛ ከኋላው እንዳይመታ ካስፈለገ ይህን ኃይል መሳርያ ማስፈታት አማራጭ የሌለው ጉዳይ ነው። መንግስት ሞኝ ካልሆነ በስተቀር ዋናውን የትህነግ ምሽግ ከኋላው አስቀምጦ ወደመቀሌ ሊገሰግስ አይችልም። ይህ ኃይል መከላከያ ሰራዊቱን ከማጥቃት ባሻገር ዋነኛው የትህነግ የሽብርተኛ ማሰማርያ ዕዝ ሆኖ እንዳይቀጥል ያሰጋል።
ትህነግ ነገ ከነገ ወዲያ ወደተበታተነ ትግል ቢገባ ይህ ኃይል በእጅጉ ይጠቅመዋል። መንግስት መከላከያ ሰራዊቱ ዳግመኛ እንዳጠቃ ከፈለገ በዚህ የትህነግ ማዘዥያ ሰፈር ላይ አንድ ነገር ማድረግ አለበት!
መከላከያ ሰራዊቱን ዳግመኛ እንዳታስጠቁት፣ ዳግመኛ እንዳታስጠቁን! – ጌታቸው ሽፈራው

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here