Home News and Views እጅ የሰጡ የጁንታው አባላት አሉ፤ ቀሪዎችንም በቁጥጥር ስር ለማዋል እየተሰራ ነው።” የምዕራብ...

እጅ የሰጡ የጁንታው አባላት አሉ፤ ቀሪዎችንም በቁጥጥር ስር ለማዋል እየተሰራ ነው።” የምዕራብ ዕዝ ዋና አዛዥ ሜጀር ጄኔራል መሰለ መሰረት

1 COMMENT

  1. በራስ ለራስ ውድቀት የተቀነባበረ የሮም አወዳደቅ ይሉሃል ይሄ ነው። አይ ወያኔ የመንፈቅ ልጅ የማያስበውን አስበው ጭላንጭል ታሪካቸውን አጠልሽተው ወደ መቃበር ሄድ። እስይ እንኳን ሆነ። የሚገርመው ግን የውጭ ሃይሎች ከእውነት የራቀ ጩኽት ነው። በተራዶኦ ድርጅት ስም በሃገሮች ጉዳይ ጣልቃ እየገቡ ሲፈተፍቱ ማየት እጅግ ያሳዝናል። የተመድ ጉዳይ ድሮም ቢሆን ሸፋፋ ስለሆነ መተው ነው። በህዝብ ስም የተቀበሉትን ገንዘብ የሚዘንጡበት ስንቶች ናቸው? በፋኦ ስም ስንት ምዝበራ ተሰርቷል? በሮም የዚህ ድርጅት ሰራተኞች የሚኖሩትን ኑሮ ብቻ በማየት እግዚኦ ማለት ይቻላል። እርዳታ ሰጪ ፓለቲካ ውስጥ መግባት የለበትም። ግን ያንኑ ነው የሚያረጉት። ወያኔ በረሃ እያለ ብዙዎችን ተጠቅሞባቸዋል። ዛሬም በአለም ዙሪያ ባሰማራቸው የውሸት ቱልቱላዎችና ተከፋይ ሃይሎች እውነትን እያማቱ ዜና ይነዛሉ። በመሰረቱ በሚሽነሪ ሆነ በእርዳታ ወይም በቱሪስት ስም ወደ ሃገር የሚገቡ ሁሉ የሚታመኑ አይደሉም። በሌላ በኩል እንደ አልጄዚራ፤ የእንግሊዝኛው ቢቢሲ፤ የተለያዪ ድህረ ገጾችና የአሜሪካ የውሸት ጡርንባ ሚዲያዎች የትግራይ ልጆች ተደፈሩ፤ ፕሮፋል ተደረጉ ሲሉ እንዴት እንደማያፍሩ አይገባኝም። ለ 27 ዓመት ምድሪቱ በዘርና በጎሳ በቋንቋ በክልል ተከልላ የትግራይ ተወላጆች ብቻ ሲፈነጥዙባትና በሌላው ላይ መከራና ሰቆቃ ሲያዘንቡ የት ነበሩ? ግን የተከፈለው በበላበት ነው የሚጭህ። የማንም ሃገር መንግስት አንድ ክፍለ ሃገር ወይም በወያኔ አጠራር ክልል ብሄራዊ የመከላከያ ሰራዊቱ በክልል ሃይሉ ሲመታ ዝም ብሎ የሚያይ የለም። ነጩና አረቡ ዓለም ግን እኛ ስንናቆር ደስ ይላቸዋል። ለዚህም ነው በሳውዲ ዘርና ቋንቋ እየጠየቁ በህጋዊና ከህግ ውጭ በሃገራቸው የገቡ ሃበሾችን ለሰቆቃ እየዳረጉ ያሉት። ይህ በዓለም ዙሪያ ወያኔ የዘራው የሸፍጥና የዘረፋ ፓለቲካ ያበቀለው ነው። አንድ ነገር ላጫውታችሁ።
    እስራኤል አይሁዶች ናቸው ብለው የሚያምኗቸውን ለማውጣት በአዲስ አበባና በጎንደር ጉድ ጉድ ማለት ጀምረዋል። በአንድ ካምፕ ውስጥ የሚሰራ ሰው ስልክ ይደወልለታል። የሚከተሉትን ሰዎች (ሁሉም ወታደር የነበሩ ወያኔዎች) ወደ አንተ እንልካለን እንደምንም ብለህ አብረው እንዲሄድ አድርግ። ጉዳዪ ያስደነገጠው ሰራተኛ ለማንም እንዳትናገር ስለተባለ በዝምታ ነገሩን ሲያልፈው ሌላ የስልክ ጥሪ ይደርሰዋል። ነገሩን ለማሳጠር በሌላ ጊዜ በረራ እስራኤል ገብተው አሁን ህዝቡን ከሚረብሹት የወያኔ የስለላ መረብ ሰዎች መካከል ቀዳሚዎቹ ናቸው። ሌሎች በሱዳንና በግብጽ አድርገው ኤርትራዊ ነን ብለው የገቡ የወያኔ ሰላዮች ይገኙበታል። ወያኔ ሌባ፤ ዘራፊ፤ ገዳይ፤ አስገዳይ ለሃገርና ለህዝብ ምንም የማይገደው እያለን ስንናገርና ስንጽፍ ተቀልዶብናል። እስቲ አሁን አፋችሁን ሞልታችሁ ንገሩን ከሃዲና ሃገር ሺያጭ አለመሆናቸውን? የት አላችሁ ድጂታል ወያኔዎች፤ የት ናችሁ ተጋዳላይ ነን ባዪች? የትግራይ ህዝብ በዚህ ስራቸው አላፈረም ብላችሁ እስቲ ተናገሩ? እጅን ባነሳው ሰው ላይ ታንክ ነድበት ትላለች የአይን ምስክሯ ወታደር። እንዴ መለስ ብሎ ታሪክን ማየት ነው ወያኔና ሻቢያ ለምርኮ እጃቸውን ባነሱ የደርግ ወታደሮች ላይ ነድተውባቸዋል። የጦር ሜዳ ውሎ የተባለውን በብ/ጄ ተስፋዬ ሃ/ማሪያም የተጻፈውን ብቻ መመልከት የጭካኔአቸው ጥልቀት በጭልፋ ለማየት ይረዳል። አረመኔዎች ናቸው። የገብረመድህን አርአያን (የቀድሞ ወያኔ) ምስክርነት በዪቱብ ፈልጎ ማዳመጡ የበለጠ ወያኔን ሳጥናዊነት ያሳያል።
    እኔ እሚያናድድኝ የሰሜን ጦር ተጋብቶ ተዋልዶ አጭዶ ከምሮ ት/ቤት ሰርቶ ገለ መሌ እያሉ ሲያወሩ ነው። ለወያኔ በጎነት ምኑም አይደለም። በዘሩ የሰከረ ለእኔ ብቻ የሚል ለትግራይ ህዝብ ያልቆመ እቡይ ድርጅት ነው። ለ 45 አመት መከራ የቆጠረው የትግራይ ህዝብ በወያኔ 1 ለ 5 ተጠፍሮ የተያዘ አፈሙዝ ጭንቅላቱ ላይ የተደገነበት ህዝብ ነው። ዝምታው ከዚህ ፍራቻ የመነጨ እንጂ ወያኔን አሜን ብሎ ተቀብሎ አይደለም። የቀድሞው ጠ/ሚ ታምራት ላይኔ ከወያኔ ኮሮጆ እንዴት እንደተፈነጠሩና ለእስር እንደተዳረጉ ሲያስረድ የፈጠራው ክስ ወያኔ በሚለው ካልተባበሩ አንድ ወንድ ልጃቸውን እንደሚገሉ ፊት ለፊት ነግረውታል። ማን ነው የሲሳይ አጌንናን ወንድም የገደለው? ማን ነው ፕ/አስራት ወ/የስን የገደለው? ማን ነው እውቁ የወያኔ አቀንቃኝን ኢያሱ በርሄን ትግራይ መሬት ላይ የገደለው? ስንት የትግራይ ልጆች ናቸው ጥያቄ አንስተው በበረሃም በከተማም ከነቤተሰባቸው የተገደሉት? ስንት አሳፋሪ ነገር ተፈጽሟል በወያኔ። ታሪክ ሁሉን ዘግቦ ለህዝባችን ያለምንም ጭማሪ እንደሚያቀርብልን ተስፋ አደርጋለሁ።
    በመጨረሻም በወሬ ናዳ የተጣበበው ዪቱብ አንዴ 3 ሰበር ዜናዎች፤ ሌላ ጊዜ ሰበር ዜና፤ ትኩስ፤ አሁን የደረሰን በማለት ከወሬው ጋር ምንም የማይገናኝ ፎቶና ቪዲዪ በመለጠፍ የሚነዛው ወሬ የቆሻሻ ክምር ነው። የጦር ሜዳ የመጀመሪያ ሰለባ እውነት ናት። አታሰልቹን። እርግጠኛነት ያለው ወሬ አካፍሉን። ያለዚያ ዝምታችሁ በቂ ነው። ይገባኛል ወሬና የፈጠራ ዝባዝንኬ፤ እርቃነ ስጋውን ካሳዬ ክፍያው ከፍ እንደሚል። ሁሉም ይሰለቻል። ታረሙ። ሰበር ወሬ ብሎ ነገር የለም። ወሬው ከተሰበረ እውነትነት የለውም። ያልተሰበረና የተረጋገጠ ወሬ አሰሙን። አትጨምሩ፤ አትቀንሱ። በቃኝ!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here