Home News and Views መለስ ዜናዊ ተፋብኝ

መለስ ዜናዊ ተፋብኝ

1 COMMENT

  1. መቸውንም ቢሆን በዚህ ሰሞን የተወራውንና የሚባለውን አልፎ ተርፎም በተንቀሳቃሽ ምስልም ሆነ በፎቶ የምናየውን እንዳለ መሰልቀጥ ይከብዳል። ታሪክህ አስገራሚ ነው። በሌላ ሃገር ቢሆን ኑሮ ጉዳዪ ተመርምሮ ፊልም ይሰራበት ነበር። ያው ሞትና ቅበረው በሚባልበት ሃገር ግን የሞተን ነገር ብቻ ሳይሆን የቆመንም ቶሎ ብሎ አፈር ማልበስ የተለመደ ባህል ነው። ግራም ነፈሰ ቀኝ የተፈጸመብህ በደል የወያኔ እጅ እንዳለበት የሚያጠራጥር አይደለም። አንተ እድለኛ ነህ በወያኔ እስር ቤቶች ገብተው ሳይወጡ የቀሩ ስንት ናቸው? ቤቱ ይቁጠረው። ከሱዳን፤ ከኬኒያ የስደተኞች ሰፈር በክፍያ ያስገደሏቸው ብዙ ናቸው። ወያኔ እንስሳ ነው። ዶክተር/ጄኔራል/ቄስ/ፓስተር ይባሉ እንጂ ስራቸው ሁሉ የሳጥናኤል ነው። እውነተኛ ነገር ልንገርህ የተረጋገጠ። ልጅቷ ባንድ ትልቅ የውጭ ድርጅት ተቀጥራ ትሰራለች። በትምህርቷ እጅግ ጎበዝ ስለነበረች ሥራዋ ሁሉ ይከናወንላታል። በዚህ መካከል በአንድ የወያኔ ባለስልጣን አይን ውስጥ ትገባለች። ይወድሻል። እሺ በይ እየተባለች ብትለመን እምቢኝ አሻፈረኝ ትላለች። ይህ ያስቆጣው የጊዜው ጌታ ከሥራ ወደ ቤት ስትሄድ ያሳፍናትና ወደ ሌላ ቦታ ወስዶ በማስገደድ የሚፈጽመውን ፈጽሞ ለማንም ብትናገር ሰሚ እንደማታገኝ አስጠንቅቆ ይለቃታል። ጧት ሥራ ገብታ ከፎቅ ላይ ራሷን ወርውራ ትገላለች። ወያኔ በሰው ደም ሻምፓኝ የሚከፍት ነው። ከሰሞኑ ጠ/ሚሩ መቀሌ መሄዳቸው ይታወሳል። ዲጂታል ወያኔና የኤርትራ ተቃዋሚ ድርጅቶች ባንድ አፍ ፎቶ ሾፕ ነው እሱ እዛ አልሄደም፡ ይሉናል። አዎን ፓለቲካው ጠንጋራ እንደሆነ እናውቃለን። አንድ ቀን ተስማምቶ ሌላ ጊዜ ደግሞ ሲቧቀስ ማየት የተለመደ ነው። በለንዶን የወያኔ ጡሩንቦኞች ሰላማዊ ሰልፍ አድርገዋል። 45 ዓመት ሙሉ የትግራይ ህዝብ ሃበሳ ሲቆጥር ዝም ያለው ይህ ስብስብ አሁን ያዙኝ ልቀቁኝ ማለቱ ጥቅሜ ቀረብኝ እንጂ ሌላ አይደለም። ብዙዎቹ በወያኔ ዘመን በስኮላርሽ፤ በልዪ ልዪ የንግድና የሴራ መንገድ የወጡ ከገዢው መደብ ጋር የተሰለፉ እቡዪች ናቸው። ትግራይ ድጋሚ በወያኔ የመተዳደሯ ጉዳይ አክትሟል። የዘር ሰልፈኞቹ በማይካድራ ስለ ደረሰው መከራ ያወገዙት የለም። ሁሌም ለእኔ ብቻ የሚለው ሆዳሙ የሃበሻ ፓለቲካ ለምዕተ አመት ሲያላትመን ኑሯል። በዳርፉር ሱዳን ኢትዮጵያዊውን ኮሌኔል በመግደል እናቱን እንኳን ሳይነግሩ አስከሬኑን አዲስ አበባ ያስቀመጡት እነማን ናቸው? በደቡብ ሱዳን ወጣቱን ኢትዮጵያዊ ዶክተር ማን ገደለው? ይህ ሁሉ ወያኔ በሴራ የፈጸመው እንጂ ዝም ብሎ የሆነ ነገር አይደለም። አሁን በተመድ፤ በአውሮፓ፤ በአሜሪካ እና በአረብ ሊግ ስም ኡኡታ የሚያሰሙት ወስላቶች ትላንት እልፍ ሰው ሲሞት ለምን ዝም አሉ ብሎ መጠየቅ አስፈላጊ ነው። አሁን የትግራይ ተወላጆች ከሥራ ከውትድርና ገለመሌ ተገለሉ የሚሉን የውሻ ፓለቲካ አራማጆች ትላንት 90% የሃገሪቱ ወታደራዊ መዋቅርና ሃብት በወያኔ ብቻ ሲነዳ ያሉን ነገር የለም። ግን የነጭም ሆነ የአረብ አላማና ህልም አንድ ነው። የጥቁር ህዝቦች ዝቅጠት። ሌላው ሁሉ አሻሮ ሃሳብ ነው። ወያኔ በኢትዮጵያ ምድር ተክሎት የሄደው የዘር፤ የጎሳ፤ የክልል ፓለቲካ ገና ለመቶ አመት ያፋልመናል። የማያጠግብ እንጀራ ከምጣድ ያስታውቃል እንዲሉ ነውና። የኦሮሞ ጽንፈኝነት፤ የአማራ ሃገሬ ሃገሬ ማለት፤ የትግራዪ ጎደለብን ጭኽት፤ የደቡብ ህዝቦች የክልል ጥያቄ አብረው አንድ ሜዳ ላይ እሳር ግጠው ይገቡ የነበሩ እንስሳትን ሳይቀረ የከፋፈለ ነው። ይህ ማለት በወረፋ ስንገዳደል እንኖራለን ማለት ነው። ሌላው ሁሉ ለጊዜው ሆታና ከበሮ መምታት ይበጃል እንጂ ለህዝባችን ቅንጣት ያህል እድል ፈንታውን አያሳምርም። ወያኔ ተለምኖና ተንደላቆ እየኖረ፤ አንድ ቤት ብቻ በማከራየት እስከ 20 ሺ የአሜሪካን ብር በወር እያገኙ በስልጣን ጥም ብቻ አብሮ የኖረውን ሰራዊት ከውስጥና ከውጭ በትግራይ ሃይሎች መምታት ዘግናኝ ነው። ግን የሰሜኑ ጦር ለወያኔ አገልጋይ እንጂ ጦር አልነበረም። ለአረም፤ ለአጨዳ፤ ለእርሻ ወዘተ ውጣ ሲባል የሚወጣ እንጂ ለራሱ የኖረ በወታደርነቱ የኮራ አልነበረም። 87% የሰሜን እዝ አመራር በትግራይ ተወላጆች ብቻ የተያዘ በመሆኑ እዙ የትግራይ ህዝብ አገልጋይ ነበር። ያም ሆነ ምህረት አልተደረገለትም። ሞተ፤ ተሰደደ፤ የሴቶች ጡት ተቆረጠ፤ በማህጸናቸው ሳንጃ ገባ። ይህ ድርጅት የአኖሌን ሃውልት አቁሞ ኦሮሞዎችን ይህን ያደረጉት ነፍጠኞች አማሮች ናቸው በማለት በአርባጉጉና በሌሎችም እስከዛሬ ድረስ ሰው ሲያጫርስ የኖረ ግን ራሱ ተመልሶ የወታደር ሚስቶችንና የወታደር ሴቶችን ጡት ቆርጦ በሌሎች ላይ የሲኖ ትራክ የነዳ በቁሙ የሞተ ድርጅት ነው። የትግራይ ልጆች እውነት ራሷ ትመሰክርላቸዋለች። በቦታውም ሂደው ጉዳዪን ማጣራት ይችላሉ። ግን ያልተሰበረው ተሰበረ፤ ያልሆነው ሆነ፤ አሁን የደረሰን አዲስ ዜና፤ ትኩስ ዜና በማለት ወሬ የሚያናፍሱልንን ከሰማን እውነቱን ጭራሽ አናውቅም። ያው በስማ በለው ፓለቲካ ሁሌ ስናሽካካ አለዚያም ስንናደድ አፈር ይመለስብናል። ኑሮ ካሉት መቃብር ይሞቃል የሚሉት እንዲህ ሲሆን ነው። አታድርስ። በቃኝ!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here