Home News and Views በአውስትራሊያ የትህነግ ቤ/ክናት ሰማያዊና ዓለማዊ መግለጫ …

በአውስትራሊያ የትህነግ ቤ/ክናት ሰማያዊና ዓለማዊ መግለጫ …

በአውስትራሊያ የሚገኙ 5 የትህነግ ቤ/ክርስቲያናት ያወጡትን የጋራ መግለጫ አነበብኩት። ለስለስ ብሎ በመንፈሳዊ ድባብ የሚጀምረው መግለጫ ቀስ በቀስ እየጠነከረ ይወርድና በመጨረሻም እንደ ጁንታው አመራሮች በማስፈራራት ይቋጫል። ካህን ጀምሮት ካድሬ የቋጨው የሚመስል በተቃርኖ የተሞላ ሰማያዊና ዓለማዊ መግለጫ ነው።
 
ታላቁን መጽሃፍ ገልጦ (የሐዋርያት ሥራ 20: 28) በመጥቀስ መንፈሳዊ መልዕክቱን የሚጀምረው መግለጫ ፤ አያይዞም “እንሆ እናንተ ግን መንጋውን ትጠብቁ ዘንድ የተሰጣችሁን ሃላፊነት አልተወጣችሁም” በማለት የሲኖዶሱን ጳጳሳት ይወቅሳል። የትግራይ ህዝብ ሲጨፈጨፍ ዝምታን መረጣችሁ በሚል ውንጀላ ዛሬም በትግራይ ሕዝብ ሊነግድ ይሞክራል። እውነታው ግን የሲኖዶሱ ጥበቃ የተነፈገው መንጋ አረመኔው የጁንታው ሠራዊት እንጂ የትግራይ ህዝብ አለመሆኑ ነው።
 
በመንፈሳዊ ዲስኩር እያዋዛ የጀመረው መግለጫ ወዲያው ደግሞ ፖለቲካዊ መልዕክቱን ያስከትላል። የምድራዊውን መተዳደሪያ ጥራዝ “ህገ-መንግስቱን” ይገልጥና “ብልጽግና ፓርቲ ህጋዊ ስልጣን የለውም! “ ሲል ይሞግታል። በአንድ ግዜ ሁለት ክስ ይመሰርታል። ሲኖዶሱን በሰማያዊው ችሎት ብልጽግናን በዓለማዊው ችሎት ይከሳል። ግን በሁለቱም ይረታል…!
 
በነገራችን ላይ ትህነግ የ5ቱም ቤተ ክርስቲያናት ባለቤት መሆኑን የሚያውቀው በአውስትራሊያ የሚገኝው ኢትዮጵያዊ በጋራ መግለጫው ያልተለመደ ፖለቲካዊ ይዘትም ሆነ ጭልጥ ያለ ወገናዊነት አይገረምም።
 
መግለጫው ሃተታውን ሲቋጭ ፤ ሲኖዶሱ የተለያዩ 4 እርምጃዎች እንዲወስድ ያሳስብና ፤ በመቀጠልም “ይህን ካላደረጋችሁ አማራጭ እርምጃ ልንወስድ እንገደዳለን” በማለት ያስፈራራል።
 
ለመሆኑ አማራጭ እርምጃው ምን ይሆን ? የሚለውን ጥያቄን ማንሳት ተገቢ ይመስለኛል። አማራጭ እርምጃው በቅርቡ ከዋናው ሲኖዶስ የሚገነጠል (ይቅርታ የሚሰነጠር) የጁንታው መታሰቢያ ሲኖዶስ ያረገዘ ይሆን…?
 
     ያገርሽ ይሆን ወይ የሲኖዶስ ጣጣ
የውጪው ሲገባ የውስጡ እየወጣ … ?
 
የሚለውን ጥያቄ እንመርምር ? እውን የመግለጫው ማስፈራሪያ ሚዛን ያነሳል? ምንስ ድረሰ ሊጓዝ ይችላል?፡
በኔ እይታ ማስፈራሪያው ሚዛን የሚያነሳ አይደለም። የጁንታውን አቅም ያገናዘበም አይደለም። ለምን/እንዴት ማለት ጥሩ!
 
“አማራጭ እርምጃ እንወስዳለን ” የሚለው ማስፈራሪያ፤ ለ25 ዓመታት ተለያይቶ ቆይቶ ከ 3 አመት በፊት በዶ/ር አቢይ ሸምጋይነት አንድ የሆነውን ሲኖዶስ ዳግም ለሁለት እንከፍለዋለን! ወይም እንገነጠላለን የሚል ቀጲጸ ተስፋ የያዘ ይመስላል። ይሁንና በውጭው አለም ያለውን የጁንታውን የድጋፍ መጠን ጁንታውን አምርሮ ከሚጠላው ኢትዮጵያዊ ቁጥር ጋር ስናመዛዝነው ማስፈራሪያው ከንቱ ፤ የከንቱ ከንቱ ሆኖ እናገኘዋለን። የጁንታው ድጋፍ እንኳን ከመላው ኢትዮጵያዊ ቀርቶ በቅርቡ ነጻ ከወጣው በትግራይ ከሚገኘው የትግራይ ህዝብ ቁጥር ጋም የሚመጣጠን አይደለም..…
 
በመጨረሻም የምሰናበታችሁ፤
 
     ለ27 አመት … በሰፈሩት ቁና፤
ዛሬ ሲሰፈሩ … ዙር ተራ ሆነና፤
ላማ ሰበቅታኒ – ኤሎሄ አሉ እሪ…
ቁናውን ሲያዘጋጅ አዲሱ ሰፋሪ ።
 
የሚሉትን ስንኞች በመጋበዝ ነው
 
ቸር ይግጠመን

1 COMMENT

  1. ወዳጆቼ ከወያኔ ጋር አብረው ሰውን ሲያርድ፤ ሲገፍፉ፤ ሲሰውሩ፤ በዘራቸው ተደራጅተው እልፍ ሰዎችን ሃበሳ ያስቆጠሩ የትግራይ ልጆች ምንም ሃፍረት የሌላቸው ሌቦች ናቸው፡፡ ራሳቸውን በወታደራዊ መስክ፤ በንግድ፤ በቤተ ክርስቲያን ወዘተ በማስጠለል ያልሰሩት ግፍ በምድር ላይ የለም፡፡ የሚገርመው ርቀው ከምድሪቱ እየኖሩም የሚያስቡት ያው በዘራቸውና በቋንቋቸው ዙሪያ ብቻ መሆኑ የበለጠ ታማሚ ያደርጋቸዋል፡፡ በኢትዮጵያ ስም እልፍ መከራን አዝንበዋል፡፡ በአንድ እጃቸው መስቀል በሌላ እጃቸው ሽጉጥ ይዘው ሰውን ገድለው ፍታቱ ላይ የሚቆሙ እንስሳ ናቸው፡፡ ስለሆነም በአውስትራሊያ በኢትዮጵያ ቤ/ክርስቲያን ስም የወጣው መግለጫ ወያኔአዊ መሆኑ እግዚኦ አያሰኝም፡፡ ለሰማይ ማደራቸው ቀርቶ ለዘራቸው ብቻ የቆሙ እብዶች መሆናቸውን ህዝባችን ለይቶ ያውቃል፡፡ አንድ በአዲስ አበባ ይሰሩ የነበሩትን ግፍ ልግለጥ፡፡ በየስፍራው ተዘዋውረው የመኖሪያ ቤቶችን ካዪ በህዋላ የማንና በምን ያህል እንደሚከራይ ወይም ማን እንደሚኖርበት ለይተው ያጠናሉ፡፡ በዚህ ጥናት መሰረት የአዲስ አበባ የቤቶች አስተዳደር መ/ቤት በመጠቀም የሚከራዪት ሰዎች ለአከራዪቹ (የቤቱ ባለቤቶች) ክፍያ እንዲያቆሙ ያደርጋሉ፡፡ በዚህ ክርክር መካከል ክፍያው ለወያኔ ገቢ ይሆናል፡፡ የሴራውን ጉዳይ ያላወቁት ባለሃብቶች እረ ቤቱ የእኛ ነው ሲባሉ ከብዙ ውጣ ውረድ በህዋላ ሌላ ስፍራ እንምራችሁ ይባሉና የራሳቸው ሰው ያን የተሰራ ቤት በባለቤትንነት እንዲረከበው ያደርጋሉ፡፡በዚህ ሴራ ቤታቸውን ተቀምተው የቀሩ፤ የማይረባ ስፍራ ላይ የወደቁ፤ አለዚያም ጭቅጭቅና ከርክር በማብዛታቸው ታፍነው የት እንደ ገቡ የማይታወቁ፤ እስር ላይ የነበሩና የተገደሉ ብዙዎች ናቸው፡፡ ወያኔ ከናዚ ጀርመኒ ይከፋል ስንል በመረጃ ነው፡፡ አሁን በሱዳን ወደ 30 ሺህ የትግራይ ተወላጆች በስደት ገቡ የሚባለው በተጠና መልኩ እንዲወጡ የተደረጉ ወጣቶች ናቸው፡፡ ያው እንደ 45 አመቱ ተግባሩ ወያኔ በአረብና በሌሎች ሃይሎች እየተረዳ ጥይት ለማጮህና የመገናኛና የኢኮኖሚ አውታሮችን ለማውደም ያዘጋጃቸው ሃይሎች ናቸው፡፡ እዚያው በደረሰኝ መረጃ መሰረት ወጣቱ ሞኝ ስለሆነ የሚነገረው ወደ አሜሪካ ወደ ካናዳና አውስትራሊያ እናወጣችሁሃለን እየተባሉ እንደሆነ ሰምተናል፡ አይ ሞኝነት አፍንጫህን ላስ፡፡ ኣለም ሁሉ ጥቁር ህዝብን ጠልቷል፡፡ ምንም አይወስድህም፡፡ ያው አያትና ቀድመ አያቶችህን ወያኔ ሥራ አለ እያለ ከስፍራቸው ነቅሎ ጠበንጃ ተሸካሚ እንዳደረጋቸው ሁሉ እነዚህም በተመሳሳይ ገመድ ታስረዋል፡፡ ያኔ ለምን አታለላችሁን ያሉ የትግራይ ሽማግሌዎች ተረሽነዋል፡፡ የቆመን ጠይቆ መረዳት ነው፡፡ አሁንም ይህ የወጣት ስብስብ አንዋጋም ቢል ለሱዳን ፓሊስ እየከፈሉና በራሳቸው የስለላ መረብ እየጠለፉ አፈር እንደሚመልሱባቸው የታወቀ ነገር ነው፡፡ ወያኔ ሞት ሰርጉ ነው፡፡ ራሱ አይሞትም ሌላውን ይገድላል ያስገድላል እንጂ፡፡
    ባጭሩ እኔ ወያኔ ቀመስ ከሆኑ የትግራይ ልጆች እውነት ይመነጫል ብዬ አላምንም፡፡ ቢመስልም ቢያስመስሉም መሰላቸውንና የተመቻቸው ሁኔታ እስኪያገኙ እንጂ ጭራሽ ጭራቆች ናቸው፡፡ ቄስ ቢባል ካህን ያው ነው፡፡ የሌባ ጥርቅም ነው፡፡ ለዘሩ ብቻ የቆመ ማንኛውም ጡሩበኛ ያስጠላኛል፡፡ ዝብርቅ በሆነ አለም ውስጥ እየኖረ በስማም ብሎ ጀምሮ አንገቱን ቁረጠው የሚል የቤ/ክርስቲያን መግለጫ ፋሽሽታዊ ነው፡፡ ግፍ መልቶ ሲፈስ ዝም ይሉ የነበሩ እነዚህ አፍቃሪ ወያኔ ቤ/ክርስቲያናት አሁንም እንዳለፈው ዝም ብለው ከስር በሚስጢር ለመስቀሉ ሳይሆን ለወያኔ ቢያድሩ ከትዝብት ይድኑ ነበር፡፡ ሰው እንዴት 45 ኣመት ሙሉ ዘርና ቋንቋን ብቻ ሲያቅራራ ይኖራል? የዘርና የክልል ፓለቲካ እንዲያ ነው፡፡ ለራስ ሲቆርሱ አያሳንሱ አይነት፡፡ የማይድን በሽታ ሲያክሙ መኖር፡፡ የወንብድና ፓለቲካ! በቃኝ!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here