Home News and Views መከላከያችን በነካ እጁ የቤንሻጉልን አውሬዎች አንድ ይበላቸው!! /ቋጠሮ/

መከላከያችን በነካ እጁ የቤንሻጉልን አውሬዎች አንድ ይበላቸው!! /ቋጠሮ/

በቤንሻጉል ጉምዝ ክልል በአማራ/አገው ሕዝብ ላይ በተደጋጋሚ እየተፈጸመ ያለው ዘግናኝ ግፍና ግድያ ሁለት መልክ አለው።

አንደኛው ፦ ግብጽ በባንዶች ጀርባ ተንጠላጥላ ሃገሪቷን በማተራመስ የግድቡን ግንባታ ለማደናቀፍ የሰነዘረቺው/የምትሰነዝረው ብሄራዊ ጥቃት ነው። ሁለተኛው፦ ደግሞ የትህነግ ርዝራዦች የአልሞት ባይ ተጋዳይ ሙከራ ነው። ተጠቂው ለምን የአማራ/አገው ህዝብ ሆነ? ለሚለው ጥያቄ አጥቂዎቹ የትህነግ ርዝራዦች መሆናቸው ብቻ በቂ መልስ ይመስለኛል።

ጉዳዩ ለግብጽ “የትም ፍጪው ዱቄቱን አምጪው”  ነው፦  የግድቡ ግንባታ እስከተጓጎለ ድረስ አማራ ተጠቃ አገው ፤ ኩናማ ተጠቃ ጉራጌ … ችግሯ አይደለም። የሁለቱም ፍላጎት ሊሳካ የሚችለው ግን አገር ሲረበሽና ማዕከላዊ መንግስት ሲዳከም ብቻ በመሆኑ ማተራመሱን አብረው ይሰራሉ።

ግብጽ በጀት ትመድባለች፤ የትህነግ ርዝራዦች ገበያ ወጥተው አማራ-ጠል ባንዳ በመግዛት ለግድያ ያሰማራሉ። ይኽው ነው። ቤንሻጉል ደግሞ አንድም፦የግብጽ ቅዠት የሆነው ግድብ የሚገኝበት ክልል ነው። ሁለትም፦ ወደ አውሬነት የሚጠጋ ባንዳ በርካሽ የሚገኝበት ቦታ በመሆኑ ለማተራመሱ ዓላማ ተመራጭ ሆኗል።

ጥቃቱን ከግብጽ አንጻር ስናየው በሃገር ብሄራዊ ጥቅም ላይ የተሰነዘረ ብሄራዊ ጥቃት ነው። ከትህነግ ርዝራዦች አኳያ ስናየው ደግሞ የተለመደውና ስግብግብነት የተጠናወተው የዘረኝነት በሽታ ነው። በጎሳ ፖለቲካ ቫይረስ የሚዛመት በሽታ።

በመሆኑም ፌዴራል መንግስት ክልሉን ሙሉ በሙሉ ተቆጣጥሮ “በአንድ ድንጋይ ሁለት ወፍ” እንዲሉ ሁለቱንም ጥቃቶች መመከት አለበት።  የግብጽን ብሄራዊ ጥቃት መመከትና የአማራን ህዝብ ህይወት መታደግ ይጠበቅበታል።

በአብዲ ኢሌ ላይ የወሰደውን የማያዳግም ቅጣት በቤንሻጉል ባለስልጣናት ላይ በአስቸኳይ በመድገም፤ ሮጠው ማምለጥ፤ ታግለው መጣል የማይችሉትን ሕጻናትና አዛውንቶች ህይወት ከአውሬ ማዳን አለበት። ወንጀለኞችንም አሳዶ በመያዝ ለፍርድ ማቅረብ አልያም መደምሰስ ይገባዋል። ይህ ተግባራዊ ሲሆን የግብጽ የጀርባ ሴራ በራሱ ግዜ እንደ ጉም ተኖ … ይጠፋል።

አሁኑ የፌዴራል መንግስት ጥቃቱን ሲያሳልጡ በነበሩት ባለስልጣናት ላይ ርምጃ መውሰድ መጀመሩን እየሰማን ነው። ቢዘገይም የሚያበረታ ርምጃ ነው!! አውሬ አድኖ መብላት እንጂ ሽምግልናና ሰላም ብሎ ነገር አያውቅም።

በመጨረሻም፦ ከየትኛውም መንግስታዊ ተቋም በበለጠ ኢትዮጵያዊነት እያበበበት የሚገኝው መከላከያችን የተሰነዘረብን ብሄራዊ ጥቃት በአጭር ግዜ ውስጥ ታሪክ እንደሚያደርገው ጥርጥር የለኝም። እናም እላለሁ! የትህነግን የዘመናት ጥጋብ በሁለት ሳምንት ያስተነፈሰው መከላከያችን የቤንሻጉልን ሹልኩሉክ አውሬዎችም በነካ እጁ አንድ ይላቸው ዘንድ ግዜው አሁን ነው!!

ሲጀመር የሰው ስጋ የሚበላ አውሬ እንጂ ሰው አይደለም።

ኢትዮጵያዊነት ይለምልም!

1 COMMENT

  1. ገና ወያኔ ሳይፍረከረክ፤ ገና ግብጽ የሻቢያውን መሪዎች አግባብቶ የጦር ሰፈር ለማስፈቀድ ሲሯሯጡ፤ አል ሲሲ በሻብያ ተስፋ ቆርጦ ወደ ኡጋንዳና ደቡብ ሱዳን ሳያመራ ሱዳን ውስጥ በተገኘው ተጨባጭ መረጃ መሰረት የዶ/ር አብይን መንግስት ሱዳን በሶስተኛ ሃይል እየተገፋችና እየተከፈላት የግድያ ሙከራ ተደርጎበት የተረፈው የሃገሪቱ መሪ እሺ አለ አላለም ጉልበት አለኝ የሚለው የሱዳን ሰራዊት መሪ በኢትዮጵያ ላይ አሳቦ ጦርነት እንደሚከፍት ጽፈናል አስታውቀናል። ሰሚ ግን የለም። ሱዳንን በመለማመጥ በምንም ተአምር ወደ ሰላም መመለስ አይቻልም። የሚቻለው የተጠናከረና በእውነት ላይ የተመሰረተ ዲፕሎማሲና ወታደራዊ ዝግጅትና ውጊያ በማድረግ ነው። ላስረዳ። የዶ/ር አብይ መንግስት የሱዳን ወታደሮችና መንግስት በኢትዮጵያ ላይ የሚያደርገውን ለሱዳን ህዝብ በአረብኛ ማስረዳት አለባቸው። ይህ አቀራረብ ህዝቡ ጦርነቱንም ሆነ የኢትዮጵያን መወጋት አይፈልግምና በመንግስታቸው ላይ ይነሳል። ሲጀመር የድንበር ችግር የለም። የግብጽ ችግር እንጂ። ግብጽ ራሷ ከሱዳን ጋር የድንበር ችግር አለባት። በከሰላ ሱዳን ከኤርትራ ጋር ባላት አለመግባባት የህዝቡ መግቢያ መውጫ አንዴ ሲዘጋ አንዴ ሲከፈት ይኖራል። ከደ/ሱዳን ጋር ተላትመው ነገሩ እልባት ሳያደርግ እንደ ቆመ ይገኛል። ከዚህ ባሻገር ዳቦ ያረረበት የሱዳን ህዝብ በየጊዜው ሰላማዊ ሰልፍ በማድረግ መንግስታቸውን እየጠየቁ ይገኛሉ። ይህ ሁሉ ጫና ያለባት ሱዳን ኢትዮጵያን ወራ ይህን መለስን ያ ቀረብን ማለቷ ለጊዜአዊ የፓለቲካ ፍጆታ ካልሆነ በስተቀር ፋይዳ የለውም። መታገስ መልካም ነው። ትግስት ብቻውን ግን ግብ የለውም። አሁን በግብጽና በወያኔ ትራፊዎች እንዲሁም በእርዳታ ድርጅት ስም ገብተው ወንጀለኞችን የሚያስወጡና የሚደግፉ በመረጃ የተያዙትን ማሰር ያስፈልጋል። ማሰር ብቻ ሳይሆን የሰሩትን ለዓለም ሁሉ ግልጽ ማድረግ ተገቢ ነው። 45 ዓመት ከወያኔ ጋር ተጋብቶ የነበረው የሱዳን መንግስት አሁን የጫትና የሺሻ ደምበኞቻቸው ከስልጣን ሲወርዱ ጦርነት መክፈታቸው የሚያስደንቅ አይደለም። ድሮም ወያኔና ሻቢያ ስልጣን ላይ እንዲወጡ የረዷቸው አረቦችና በተለይም ሱዳን መሬቷን ለቃ ነው። በድንበር ጥግ የነበሩት የትግራይ ስደተኞች ከድንበር ተነሱ ብሎ የተመድ መግለጫን ሳይ የገባኝ ነገር ቢኖር አካባቢው የጦርነት ቀጠና ስለሚሆን ለእነርሱ ጥንቃቄ እንደሆነ ነው የገባኝ።
    ለ 45 ዓመት የአማራን ህዝብ እያደነ እንደ ድር አራዊት የሚገድለው ወያኔ፤ የኦሮሞ ጽንፈኞችና የቤኒሻንጉል ጉዶች የሚፈጽሙትን ማጋለጥ፤ ወይም የተፈናቀሉትን ከግማሽ ሚሊዪን ህዝብ በላይ እንርዳ በማለት ወደ ሃገር የገባ ሰብአዊ ድርጅት አንድም የለም። ግን ወያኔ የስሜኑን እዝ ጨፍጭፎ የማይካድራ ኗሪዎችን አርዶ ሲወጣ ስደተኛ የሚል ስም ተለጥፎለት እንክብካቤ ይደረግለታል። የሚያሳዝነው ነጩና አረቡ ህዝብ ለጥቁሩ ህዝብ (ለትግራይ ልጆች) ያዘኑ ይምሰሉ እንጂ ሱዳን ልክ እንደ ወያኔ የመለመና ስልቻ አርገው ነው የሚጠቀሙቧቸው። ዝርፊያው፤ እስራቱ፤ ግርፋቱ፤ የሱዳንና የሌሎች ሰዎች የሚያደርሱት ግፍ ሰማይ ጠቀስ ነው። የሚገርመው የዶ/ር አብይ መንግስት እነዚህን ሰዎች ወደ ሃገር እንመልሳለን ማለቱ ነው። አልገባውም። እነዚህ ሰዎች 95% ከ 30 ዓመት በታች ይበልጡ ወንዶች ሆን ተብለው በወያኔ የተላኩ ደጀኖች መሆናቸውን ነው። አሁን አሰልጥነው፤ አስታጥቀው እንደገና ወደ እሳት ይማግዷቸዋል። የወያኔ መሰሪነት ሃገር እስከ መሸጥ ነው።
    ታዲያ ይህን ሁሉ የሃገሪቱን ገመና እንዴት መግታት ይቻላል። አንደኛ – ጠንካራና ሃገር ወዳድ የሆነ ሰራዊት መገባት፡ በዘሩና በቋንቋው የሰከረ ሰራዊት ከወራሪ ሃይል አይለይም። የሃገሪቱን ህዝብ በእኩልነት የሚያይ ሞቱና መኖሩ በሃገሩ የሆነ ሰራዊት ማንንም መጋፈጥ ይችላልና፤ ሁለተኛ – በዲፕሎማሲ በልመና አይደለም በኢትዮጵያ ላይ በአረቦች የሚደረጉ አሻጥሮችን በየጊዜው ማሳየት። ትላልቅ የዜና ማሰራጫ አውታሮች ገብተው እንዲዘግቡ መፍቀድ። ሶስተኛ – የሃገሪቱ ተምረናል የሚሉ ስራ አጦችና አውደልዳዪች ተሃድሶ ተደርጎ በቀጥታ ምልመላ ወደ ውትድርና እንዲገቡ ማድረግ። ለዚህም ጠ/ሚሩ የድሮውን የሃረር ጦር አካዳሚ እንደገና መክፈትና የዚያው ምሩቆችንና አሁን በጡረታ ላይ ያሉትን ከሌሎች ጋር አጣምሮ አስተማሪዎች ማድረግ፤ የሆለታ ገንት ጦር ት/ቤት ስሙን መልሶ የሆለታ ገነት ጦር ት/ቤት በማለት ሰው ወደ እዚያው ገብቶ ስልጠና እንዲያደርግ ማድረግ፤ አራተኛ – እሾህን በእሾህ እንዲሉ ግብጽና ቱርክ አይን ለአይን አይተያዪም። የቱርክን እርዳታ መጠየቅና የሃገርን አንድነትና ሚስጢር በማያባክን መልኩ ማስተካከል፡፡ አሁን እንደ እንስሳ አማራን እየጎተተ የሚያርደውንና ቤቱን የሚያቃጥለውን እቡይ ሃይል ለይቶ መግደል፡፡ ተባባሪና ተከፋይ የአመራር አካላቶችንም ለፍርድ ማቅረብ ወይም መረሸን ነው፡፡ የሃበሻው ጭንቅላት ፍቅርን፤ ሰላምን፤ ደስታን አብሮ መኖርን ካልተቀበለ መኖሩ ለራሱም ለጎረቤቱም አይጠቅምም፡፡ ማስወገድ ነው፡፡ በመተከል፤ በቤኒሻንጉል፤ በወለጋ የሚሰራው ስራ ተመዝግቦ ለትውልድ መቅረት አለበት፡፡ ወስላቶቹ የአማራ መሪዎች ነን የሚሉትም ልብ የላቸውም፡፡ የቆመ ሃውልት ማፍረስ እንደ ሙያ ይቆጥሩታል የቆመ ሰው በየቀኑ እየተቀጠፈ፡፡ በህቡእም ሆነ በይፋ ሰውን ለመርዳት መቻል አለበት፡፡ ይህን ያህል ሞተ፤ ያን ያህል ተሰደደ፤ ይህን ያህል ቆሰለ ማለቱ ለወሬ ፍጆታ እንጂ ለተጠቃው ህዝብ አይበጅም፡፡ ሥራ በልብ ነው፡፡ ሳይደነፉ፤ ስንት መስራት ይቻላል፡፡ ሞክሩትና እይቱ፡፡ ዘፈንና ቀረርቶውን ተውት! አሁን ጠ/ሚ በስፍራው ተገኝተው ባለስልጣኖችንና የአካባቢውን ሰው አናግረው በተመለሱ ማግስት ይህ ጭፍጨፋ መሆኑ የነገሩን መክፋትና ከላይ እስከ ታች ያሉ ባለስልጣኖች ጥቃቱን አውቀው እንደሚያደርሱት ያመላክታል፡፡ መሪውን መናቅ፤ የህዝብ ህይወትን እንደ ገለባ መመልከት፡፡ ይህ ሥራ ወያኔን/አል ሲሲን/ሱዳንን ይመስላል፡፡ ግፉን ማቆም የሚቻለው መልሶ በማጥቃትና ገዳይን እና አስገዳይን በመግደል ብቻ ነው፡፡ ሌላው ሁሉ ለፎዎች የሚተው እንክርዳድ ነው፡፡ በቃኝ!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here