Home News and Views ሱዳን ምን አቅዳ ማንን ተማምና ተዳፈረችን?

ሱዳን ምን አቅዳ ማንን ተማምና ተዳፈረችን?

1 COMMENT

  1. ያለውን የሃይል አሰላለፍ መልካም አድርገህ አሰምተኸናል። አመሰግናለሁ። አረቦች ለኢትዮጵያ ተኝተው አያውቁም። በሳውዲና በሌሎቹ መዲናዎች ኢትዮጵያዊ ሆኖ መገኘት እንደ ወንጀል ተቆጥሮ ይህ ነው የማይባል ኢሰብአዊ ድርጊቶች በሴትና በወንድሞቻችን ላይ ተፈጽሟል፤ በመፈጸምም ላይ ይገኛል። በአሜሪካ በጥገኝነት ይኖር የነበረውን እንደ ቄራ ሥጋ ቆራርጠው የገደሉት የሳውዲ የደህነንት ሰዎች በራሳቸው ዜጎች ላይ የሚፈጽሙት በደል ሰማይ ጠቀስ ነው። ግን ነዳጅ ያሰከረው ምዕራቡ መንግስታት እንዳላዪ አይተው በማለፍ ስንቅና ትጥቅ እያቀበሉ ሰውን በማጨራረስ ላይ ይገኛሉ። የሱዳንም የኢትዮጵያን ደንበር አልፎ ጦርነት መግጠም ከዚሁ የአረብ ካምፕ የጦር አሰላለፍ ጋር የተያያዘ ነው። ዛሬ በየመን ሰው ሰውን እንዲበላው የሚያደርጉት እነዚህ ጉዶች ናቸው። በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ሶሪያን፤ ኢራቅን፤ አፍጋንስታኒን ያፈራረሱት በእቅድ ነው። ሳውዲዎች በአረቡ ዓለም የተጠሉ የሰው ፍጥረት የሌላቸው ድርቡሾች መሆናቸውን ሰውን በስለት አንገቱን ሲቆርጡ ማየት ብቻ በቂ ነው።
    ኢትዮጵያ እንድትፍረከረክ ሻቢያን አሰልጥነዋል፡ አስታጥቀዋል፤ በተለይ በሱዳን በኩል መጠለያና የማስለጠኛ ቦታዎችን በመስጠት የሻቢያና የወያኔ ጭፍሮች እጅና ጓንት ሆነው እንዲሰሩ ታላቅ አስተዋጾ አድርገዋል። አሁን የሱዳን ጦር ወደ ኢትዮጵያ ብቅ ማለቱ በግብጽና የወያኔ ጉቦ ባሰከራቸው የሱዳን ወታደሮች እየተረድና እየተመሩ እንደሆነ ግልጽ ነው። የሻቢያውን አለቃ እግሩ ላይ ወድቀው ለምነው አልሳካላቸው ያሉት ግብጾች አሁን በሙሉ ሃይላቸው ኢትዮጵያን ለማፈራረስ ታጥቀው ተነስተዋል። በደቡብ ሱዳን ለጉብኝት ብቅ ብሎ የነበረው አል ሲሲ እልፍ ግብጻውያን የማይወድት ከጎረቤቱ ጋር አተካራ ያለበት ለህዝቡ ዳቦ ማቅረብ ያቃተው በአሜሪካና በሳውዲ ዶላር የቆመ መንግስት ነው። የሱዳን ወታደር መዋጋት አይችልም። በደማቸው ውጊያ የለም። ምንም ቢታጠቁ በተሻለ ሚሊሻ እልፍ መማረክ ይቻላል። የግብጽና የሳውዲ አማካሪዎችም አንድ ሁለት ሲሞትባቸው ጥለው ነው የሚፈረጥጡት። ይህ ግን በጭፈራ የሚሆን ስልት አያስፈልግውም። በመጀመሪያ የጂኦ ፓለቲካውን አሰላለፍ መገንዘብ ያስፈልጋል። ቱርክና ግብጽ በሊቢያ ጉዳይ ተፋጠዋል። ቱርክ በምንም መንገድ በኢትዮጵያ ላይ ችግር እንዲፈጠር አትሻም። ጉዳዪን መልእክተኛ ልኮ ለቱርኮች ማሳወቅና ሊረድ የሚችሉበትን መንገድ ማመቻቸት አስፈላጊ ነው። እሾህን በእሾህ ይሉሃል እንዲህ ነው። በአሜሪካ የሚታመን ሁሉ ጅል ነው። ሲላቸው በለው ሳይላቸው አምጣና ውጣ የሚሉ ጉዶች ናቸው። ከእነርሱ የቻይና የራሺያ እርዳታ የተሻለ ይሆናል። ባጭሩ ውጊያው የመሬት አይደለም። ወያኔ እያለ ከነበረው የተለየ መሬት ዛሬ ከሱዳን ላይ የተወሰደ የለም። ለሱዳን ህዝብና ጦርነቱን ለማይሹ የአመራር አካላት በግልጽ ጠ/ሚሩ ኢትዮጵያ መወረሯን፤ ጦርነቱን እንደማትፈልግ፤ የሱዳን ህዝብ ወገን እንደሆነ፤ ሆን ተብሎ በግብጽ የተሸረበ ሴራ እንደሆነ ማስረዳት አለባቸው፡፤ ህዝቡ ሆ ብሎ ጦርነቱ እንዲቆም ይጠይቃል፡፤ ያ ካልሆነ ሱዳን ወታድሮችን/ግብጽን/ወያኔ አንድ ላይ መምታት ነው። ይህም በስልት እንጂ እንዲሁ የሚሆን ነገር አይሆንም። ባጭሩ የመከላከያ ሰራዊቱ ነገሮችን በሰከነ መልኩ መታገል አለበት። ወሬ፤ ይህን አረግን ያን ሰራን መባል የለበትም፡፤ ሁሉ በሚስጢር መያዝ አለበት፡፤ ድረሱልኝ ያለ ሁሉ ወገን አይደለም። አስፈላጊ ከሆነም በሽምቅ ውጊያ ስልት ድባቅ መምታት ይቻላል። ዋናው ነገር በልመናና በመለማመጥ ሱዳንን ወደ ሰላም መንገድ ማምጣት አይቻልም። አንድ በር ቢዘጋ ሌላ ይከፈታል፡፤ ነዳጅና ሌሎች ነገሮች ለምን በኤርትራ በኩል ማስገባት እንደማይቻል አይገባኝም። ታዲያ ሰላሙና ያ ሁሉ መተቃቀፍ የት ገባ? አሁን ማን ይሙት ኢትዮጵያ ተፍረክርካ ኤርትራ በሰላም መኖር ትችላለች? የማይታሰብ ነገር ነው። በየተራ ነው አረቦቹ የሚያጠፉን። እኔን አይነካኝም ማለት ጅልነት ነው። ነቃ እንበል፡፤ ከየመን ገመና እንማር። በቃኝ!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here