Home News and Views በሰሜን እዝ ላይ ጥቃት ሲፈፀም ከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮቹ የት ነበሩ? /ተመስገን ደሳለኝ/

በሰሜን እዝ ላይ ጥቃት ሲፈፀም ከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮቹ የት ነበሩ? /ተመስገን ደሳለኝ/

1 COMMENT

  1. የወያኔ ከውጭና ከውስጥ የተቀናበረ በሰሜን እዝ ላይ ያደረሰው ጥቃት እብደት ቢሆንም የሰሜን እዝን ማንቀላፋት አጉልቶ ያሳየ ነው። በመሰረቱ የሰሜን እዝ ለወያኔና ለትግራይ ህዝብ የላም ጥገት እንጂ ሌላ ሙያ አልነበረውም። ተጋብቷል፤ ተዋልዷል፤ በጡርንባ ውጣ ሲባል እርሻ ይሄዳል፤ ይዘራል፤ ያርማል፤ እንደተባለው ሁሉ ከደሞዙ እየቀነሰ ት/ቤቶች፤ የህክምና ጣቢያዎች፤ መንገዶች ሰርቷል። ለወያኔ ግን ከትግራይ ሰው ውጭ ሁሉ አውሬ ነው። በዘራቸው የሰከሩ በሌብነት የከበሩ፤ በደም የተነከሩ በመሆናቸው ሰራዊቱን ለማጥቃት ከስር እስከ ላይ ሲያቅዱ እረ ይህ እብደት ነው ተው ያለ የለም። ወይም ጭፍጨፋው ከመሆኑ በፊት ሾልኮ ለመንግስት ሹክ ያለ የለም። ይህ የሚስጥር አጠባበቅ እጅግ የሚያስገርም ነው። ሰራዊቱ ለእርሻ ስራ ይውጣ ተብሎ መሳሪያውን ግምጃ ቤት አስገብቶ ሲሰራ ውሎ ደክሞት ወደ ማረፊያው ሲመልስ ካዝና በራፍ ላይ መትረጌስ የጠመድ የወያኔ ወታደሮች ነው የገጠመው። ከዚያም እፎይ ብሎ በተኛበት ተጨፈጨፈ፤ ተነዳ፤ መኪና ተነዳበት፤ የሴቶች ጡት ተቆረጠ፤ በብልታቸው ሳንጃ ከተቱባቸው ወዘተ… እኔን ከወያኔ ድርጊት ይልቅ እጅግ የሚያናደኝ እንደዚህ ያደርጋሉ ብለን አስበን አናውቅም የሚሉ ሰዎች ናቸው። 27 ዓመት የሰርቱ ምንድን ነው። እስቲ ሂዱና የሶማሊ ክልል ህዝባችን ጠይቁ፤ እስቲ የአማራን የኦሮሞን ህዝብ ጠይቁ። ከሰው ባህሪ ውጭ የሆነ ድርጊት አልተሰራም? እስቲ ቀደም ያሉትን ሁኔታዎች እንመልከት በበደኖ፤ በኢንቁፍቱ፤ በአርባጉጉ ምን ነበር የተደረገው? ሰዎች እንደ እንስሳ አልታረድም፡፡ ዛሬስ በመታረድ ላይ አይደሉንም? ወደ ዋናው ሃሳብ ስንመለስ የስሜን እዝ አመራሮች ምን ይሰሩ ነበር ለተባለው ያንቀላፉ ነበር ማለት ይቻላል። የሰራዊቱን መሪ መርዝ አብልተው ከጫወታ ውጭ ካደረጉት በህዋላ በምትኩ የተላከውን አንቀበልም ሲሉ የሆነ ነገር ለመኖሩ እጣት መቁጠር አያስፈልግም። በመሰረቱ የሰሜን እዝ በጊንጥና በእባብ ወያኔዎች የተከበበ በመሆኑ ከዚህ በፊት ቀደም ብሎ አለመንቃቱ የቱን ያህል የዘሩ ፓለቲካ ሰርጾ እንደገባ ነው። አሁን አይወድቁ አወዳደቅ የወደቀው ወያኔ ድርቡሻዊ ነው ስንል ሥራውን መዝነን እንጂ የእነርሱ የፓለቲካ አጨብጫቢዎች እንደሚሉት የትግራይን ህዝብ ስም ለማጥፋት አይደለም። ወያኔ ማለት ፋሽሽት ማለት ነው። አሁን በባህርዳር የሙሉዓለም አዳራሽ ተብሎ በስሙ አዳራሽ ያቆመለት ወያኔ ከገደለው በህዋላ ነው። ጄ/ሃያሎም በሆለታ (ገንት) ጦር ትምህርት ቤት ስሙ እንዲጠራ የወሰነው ሆን ብለው ከገደሉት በህዋላ ነው። ብዙ የትግራይ ልጆች በሃገር ውስጥና ከሃገር ውጭ በወያኔ ሴራ አፈር ለብሰዋል፡ ወያኔ ሞት ብቻ የሚበቃው ድርጅት አይደለም። ከሰው ተራ የወጣ አራዊቶ የተጠራቀሙበት ለራሱ ብቻ የሚኖር ዘራፊና ገዳይ የማፊያ ቡድን ነው። ለዚህም ነው አሁን በሱዳንና በግብጽ እየተረዳ በድንበር አሳቦ ሃገር የሚያተራምሰው። ሱዳንና ግብጽ በምንም መልኩ ኢትዮጵያን ከማተራመስ አያርፉም። የተጠናከረ የጦር ሃይልና የኤሌክትሮኒክስና የሰው የስለላ መዋቅር እጅግ አስፈላጊ ነው። አሁን ከየስፍራው ያመለጡት የወያኔ ስመ ጄኔራሎችና መኮንኖች ከሱዳን ሃይል ጎን ተሰልፈው እየተዋጉ እንደሆነ መረጃዎች ደርሰውናል። የሰሜን እዝ ከደረሰበት ጥቃት አንጻር ራሱን እንደገና ፈትሾ ማስተካከል የሚገባው እልፍ ነገሮች አሉ። የመጀመሪያው የጦሩ የመገናኛ መንገድ ነው። እንዴት አንድ ጦር አንድ አይነት የመገናኛ መንገድ ብቻ ይኖረዋል? ሊሆን አይገባም። ሁለተኛ የሚዋጋበት መሳሪያ ኋላ ቀርነት እጅግ ያሳዝናል። የደርግ ዘመን ዙ 23 ገለ መሌ ሲሉ ያሳፍራል። እንዴት ሰው በክላሽንኮፕ ስናይፕር ከያዘ ሰው ጋር ይፋለማል። እንዴት ሰው ሚግ 21 ና 23 እያለ ያወራል። የወታደሩ ትጥቅ መቀየር አለበት። ይህ ካለባበሱ እስከ ጫማው ድረስ ነው። ለምሳሌ የብዙዎቹ አይን በጠንካራው የጸሃይ ብርሃን ጉዳት እንደ ደረሰበት ያስታውቃል። እንዴት የጸሃይ መነጸር ወታደሩ እንዲለብስ አይደረግም። የሰው ልጆችን አይን ከሚጎዳው አንድና ዋንኛው ነገር ያልተመጣጠን ብርሃን ነው። የሰሜኑ ክፍል ለዚህ ምልከዓ ምድሩ ይመሰክራል፡፡ ሌላው እጅግ የሚያሳዝነው ነገር ደግሞ ምግባቸው ነው። እንዴት ነው የሚዋጋ ጦር ፍየል፤ በጎች፤ የቀንድ ከብቶች አርዶ መብላት የሚችለው? ምን አይነት ባህልና የጦር ስልት ነው? ደግሞስ ሰው እንጀራና ዳቦውን ትቶ በሥጋ ብቻ ይኖራል ተብሏል እንዴ? የጦር ሰው ስንቁ በቀላሉ የሚደርስበት፤ እሳትና ሌላም ነገር የማያስፈልገው ቀድሞ የበሰለና የታሸገ በቀን የተወሰነ ካሎሪ (ጉልበት) ሊሰጠው የሚችል መሆን ነበረበት። ቂጣ ጋግረው ሲበሉ ሳይ እጅግ አዝኛለሁ። ስለዚህ የወታደሩ የሎጂስቲክ ክፍል በሃገሪቱ ውስጥ አጫርቶ አልሚ ምግብና በረሃ ለበረሃ ሲንከራተቱ ከኪሳቸው በቀላሉ መዘው ሊመገቡት የሚችሉት ምግብ ማዘጋጀት አለበት። ሌላው ልብስ ነው። ቀን የሚያቃጥለው ጸሃይ ማታ ብርዱ መከራ ነው። የታለ ብርድ ልብሳቸው? ወይም ቁሩን መቋቋም የሚችሉበት ጃኬት ወይም ከውስጥ የሚለበስ ልብስ? እጅግ ኋላ ቀርተናል። ሩጫው ማን በ ቪ – 8 ይጓዛል አይነት ይመስላል። የሰራዊቱ የእቃና ትጥቅ እንዲሁም ምግብና ልባሽ አቅብሮት ሊጠና ይገባዋል።
    የወያኔው ግጭትና አሁን የሱዳን በግብጽና በወያኔ ትራፊዎች እየተገፉ ሃተፍ ተፍ ማለት የሃገሪቱ የመጨረሻ ፍልሚያ ነው ብሎ የሚያምን ፓለቲከኛ ፌዜኛ ነው። ሃገሪቱ ጠላቷ ብዙ ነው። አሁን በመተከልና በቤኒሻንጉል ዙሪያ “ቀይ ቀዪችን ግደሉ” የሚለው ትዕዛዝ በወያኔ ተሸርቦ በተከፋይ ሃይሎች የሚፈጸም ነው። ሲጀመረ መተከልን ከቤኒሻንጉል ጋር የሚጨፈልቀው ጉዳይ አልነበረም። ግን ወያኔ ልክ በበወሎ በጎንደር በአፋር መሬቶችን እየቀማ የትግራይ ነው ያለ ትግርኛ መናገር አይቻልም እያለ ሲገድል፤ ሲዘርፍ፤ ሲያሳድድ የነበረው ያው እጅ ነው አሁን በደቡብ፤ በምስራቅ፤ በምዕራብና በሰሜን ህዝባችን የሚያተራምሰው። እኛ በስልጣን ካልቆየን ኢትዮጵያ ትፈርሳለች ይሉ ስለነበር ለዛ ነው በሃገሪቱ ህግ አልተከበረም ወዪ እያሉ ሲያላዝኑ የቆዪት። ራሱ በድሎ ራሱ አለቀስ ይሉሃል ይሄ ነው። አሁን የዓለም ጤና ጥበቃ አለቃ ሆኖ ለወያኔ የሚያላዝነው ቴድሮስ አድሃኖም ለወያኔ መሳሪያ ለማቅረብ በዚህም በዚያም መንግስታትን ደውሎ እንደጠየቀ መረጃዎች አሉ። ከወያኔ ጋር ሆኖ በሃገሪቱ ውስጥ የሰራው ግፍ ሰማይ ጠቀስ ነው። አሁን የሃገሬ ጉዳይ ያሳስበኛል በተለይም የትግራይ ህዝብ ሁኔታና የወንድሜ መጥፋት የሚለው እልፎች በወያኔ እየታፈኑ ሲጠፉ እሱ ቆሞ ነበር የሚያጨበጭበው። ስለ ትግራይ ህዝብ የሚገድህ ከ 45 አመት በህዋላ አሁን ነው? አዲስ አበባ ውስጥ በቢሊዪን የፈጀ ሆቴል ለዘመድ አሰርቶ ያስረከበው ይህ ግፈኛ ሰው አሁን የሚያላዝነው የደም ጓደኞቹ ጠፍተውበት እንጂ ለትግራይ ወይም ለኢትዮጵያ ህዝብ አይገደውም። እውቁ ደራሲና ተርጓሚ ማሞ ውድነት እባክህ ውጭ ወጥቼ እንድታከም እርድኝ ብሎ ይህ የወያኔ ሰው የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር በነበረበት ጊዜ ሲጠይቅ በዝምታ ነው ወደ ሞት የሸኙት። ወያኔዎች ከጣሊያን ወራሪ ከናዚ ገስታፓ ይከፋሉ። ቆመው መሄዳቸው ብቻ ነው የሰው ምስልነታቸው። ጭራሽ ጭራቆች ናቸው።
    የሚያሳዝነው ጥቁሩ ህዝብ ራሱን በራሱ የሚጎዳ ህዝብ ነው። በዚህ ላይ ነጭና አረቡ ደግሞ አጣብቂኝ ውስጥ አስገብቶ ይደቁሰዋል። በጣሊያን ሃገር በራሷ ቆሟ ለሰው ተርፋ ፍየሎች እያረባች በደስታ የምትኖረውን ሰው ነው በቆዳዋ ቀለም ብቻ የጣሊያን ዘረኞች እልፍ መከራ ሲያደርሱባት ቆይተው አሁን ሞተች የተባልነው። አጊቱ ጉዴታን ማን ገደላት? ማን አስገደላት? በውጭም ሞት፤ በሃገር ቤትም ሞት መቼ ነው ጥቁሩ ህዝብ ራሱን አይቶና መዝኖ በህብረትና በሰላም የሚኖረው? መቼ ነው እንደ ጄ/ሃይሉ ጎንፋ ያሉ ስሜ የተቀየረው በሚኒልክ ነው እያሉ በ 21ኛ ክፈለ ዘመን ላይ ቆመው የሚያላዝኑት? እነዚህ ናቸው የሃገር መከላከያን ወደ ከፍታ የሚያወጡት? በመንደርና በዘር ፓለቲካ የሰከሩት? እይታቸው አለም አቀፋዊ፤ ሁለገብ፤ ሃገራዊ ያልሆኑ የወታደሩ አባሎች የህዝባችን ሰቆቃ ያብሱታል እንጂ ለምንም አይጠቅሙም። ይህ ሰው እንዲህ ባለ ጎጣዊ አስተሳሰቡ እንኳን የሃገሪቱ ጄኔራል ቀርቶ የመንደር ፍየሎችን ለማገድ እንኳን በእረኝነት አይታመንም። ከሰራዊቱ መሰናበት አለበት! ባጭሩ ለጥቁር ህዝቦች ህብረትና አንድነት ለህዝቦች ሰላምና ጤን ያልቆመ በዘሩና በጎሳው በቋንቋ አቀንቃኝ የሙታን መንጋ ለራሱም ለማንም አይጠቅምም። ወያኔን ያየህ ተማር! የሰሜኑ የጦር አለቆችም ራሳችሁን ፈትሹ። እንዲህ ያለ ጥቃት እንዳይከሰት ከትጥቅ፤ እሰክ መገናኛ እንዲሁም የሰራዊቱ ምግብና አልባሳት እንደገና መፈተሽ አለባቸው ባይ ነኝ? የአየር ሃይሉ የማጓጓዣ ሄሊኮፕተሮች በብዛት ያስፈልገዋል፡ በቀዳሚ ጦር (አብሪ) በተጠና የማሳረፊያ ስፍራ ጦርን በቀላሉ በማውረድ የርቀት ጉዞን በሰአት ማድረግ ይቻላል። ዛሬ ሁሉ አዲስ ነገር በሚሻበት በምሥራቅ አውሮፓ፤ በሰሜን አሜሪካ፤ በብራዚል፤ በኮሪያ በሌሎችም ሃገሮች በቀላል ዋጋ ተገዝተው እየተጠገኑ የሚያገለግሉ የጦር ሄሊኮፕተሮች በ “surplus” ተከማችተው ይገኛሉ። መግዛት ወይም አፍ አውጥቶ በእርዳት መጠየቅና ቀድሞ መዘጋጀት አስፈላጊ ነው። ሰርገኛ መጣ በርበሬ ቀንጥሱ አይሰራም። ይገባኛል ወያኔ የሰራዊቱ ቁመና እንዳይሻሻል እንቅፋት ያስቀምጥ እንደነበር። ሰራዊቱ ከስር እስከ ላይ እንደገና መፈተሽ አለበት። በቃኝ!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here