Home News and Views ሰላሳ አመት በጣሊያን ኤንባሲ የቆዩት የደርግ ባለስልጣናት

ሰላሳ አመት በጣሊያን ኤንባሲ የቆዩት የደርግ ባለስልጣናት

1 COMMENT

  1. አይ ጊዜ ስንቱን ያሳያል። የቆመው ሲወድቅ፤ የወደቀው ሲነሳ፤ የሞተው ተቆፍሮ ሲለቀስለት፤ ዛሬ የታየው የት እንደገባ ሳይታወቅ ሲሰወር ጊዜ ለኩሉ ይሉሃል ይሄ ነው። በአዲስ አበባ ባለው የጣሊያን ኤምባሲ ተጠልለው የነበሩት እኮ እነዚህ ሁለቱ ብቻ አልነበሩም። ያው ከላይ እንዳልኩት ነው። የሞተው ተረስቷል፤ ለራሱ የፓለቲካ ፍጆታ አጽሙን ቆፍሮ ሰው እስኪያለቅስለት ድረስ። የምንኖርበት አለም ጢምቢራዋ ዙሯል። በአሜሪካ ለአለም ሁሉ እና ለአሜሪካ ህዝብ አስጊ የሆነው አሁን ሃገሪቱን በአፉ ብቻ የሚያተራምሰው ትራምፕና ደጋፊዎቹ አሳፋሪ የሆነ ስራ ሲሰሩ በቴሌቪዚን መስኮት ተመልክተናል። ይህ እንደሚሆን በቀደሙት ጹሁፎቼ የነካካሁት በመሆኑ አሁን ጫዋታው ካለፈ በህዋላ የምጨምረው የለኝም። ግን አንድ ነገር በማለት ይህን የአሜሪካ የፓለቲካ እሰጣ ገባ አልፈዋለሁ። አሜሪክ እንደ ጀርመኖች ናዚ አይነት መንግስት ለመቀበል የቀራቸው አንድ እርምጃ ብቻ ነው። ቆይተን እናያለን የዚህን ልክነት። እጅግ የሚያሳዝነኝ ግን የዚህ ታሪክ አጠልሺ ደጋፊዎች ክርስቲያን ነን የሚሉ ጭምር መሆናቸው እምነታችውን ጥላሸት ቀብቶታል። በመሰረቱ ሰውየው ከሚናገረው ሌላ በተግባር የሞተ፤ ነጭ ብቻ ሰው እንደሆነ የሚያምን ጨካኝ ለመሆኑ የተጻፉ መጽሃፍትና የአይን እማኞች ይመስከራሉ።
    ዋሽንግተን ዲሲ በዚህ ሁኔታ ስትተራመስ የሃብት ሚኒስትሩ ሱዳን ውስጥ 1.2 ቢሊዪን ብድር ለሱዳን ለመስጠት ካርቱም ነበር። አሁን ከእስራኤል ጋር ታርቀናል የሚሉት የአረብ ሃገሮች እንደ ልጆች ጫዋታ ብዙም ሳይቆይ ፍርስርስ እንደሚል ሊታወቅ ይገባል። ትራምፕ ለሞሮኮ በድሮ አጠራር ስፓንሽ ሳሃራ አሁን ደግሞ ባጭሩ ምዕራብ ሰሃራ የሚባለውን ቦታ ለሞሮኮ እንካችሁ ማለቱ የቱን ያህል ለሰው ልጆች ገመናና መከራ እንደማይገደው ያሳያል። በሞሮኮ የጸጥታ ሃይሎች በእነዚህ ህዝቦች የሚሰራው ግፍ ጣራ ጠቀስ ነው። ግን ምን ችግር አለበት የነጭ ደም እስካልሆነ ድረስ እንደ ውሃ ቢፈስ። ሱዳን የገቢያው ዝቅጠት 200% የደረሰበት፤ በውጭና በሃገር ውስጥ እዳ የተዘፈቀች፤ በግብጽ የምትመራ በራሷ አስባ የማትኖር ሃገር አሁን ደግሞ በወያኔና በግብጽ ቅስቀሳ ድንበርን ምክንያት አድርገው በኢትዮጵያ ላይ ጦርነት ከፍተዋል። ይህ ሁሉ የሚያመላክተው ጥቁሩ ህዝብ በራሱ አስቦና አልሞ መኖር እንደማይችል ነው። የአረቦችና የነጮች መጫወቻ! በጋና በቅርብ በተደረገ ምርጫ ፓርላማ ውስጥ ግብ ግብ ተገጥሞ በጸጥታ ሃይሎች ነው ነገሩ የረገበው? በሊቢያ/ ሶሪያ/ኢራቅ/ ሱማሊያ/የመን/ ወዘተ ሰዎች በየጊዜው ይሞታሉ እነዚህ ሃገሮች በፊት የነበራችው ሰላምና ቆመና ተቀምተው አሁን እርስ በርሳቸው በየምክንያቱ ሲጠዛጠዙ ይኖራሉ። በቅርቡ አንድ ኤርትራዊ ነኝ የሚል ወስላታ (ተወልዶ ያደገው ካዛንቺስ ነው) አቶ ኢሳያስ መውረድ አለበት እያለ ሲቀባጥርልኝ። በምትኩ ምን አዘጋጅተሃል ብየ ለጠየኩት መልስ በማጣቱ ቻው ሳይለኝ እንደ ታክሲ ጠባቂ ገትሮኝ ሂዷል። ስሜታዊነትና እውነታ ይለያያሉ። ኤርትራ ከኢትዪጵያ እንድትገነጠል ሻቢያን አይዞህ ሲሉ የነበሩ ሃገሮች ናቸው ዛሬ የኤርትራን መፈራረስ የሚናፍቁት? እስቲ አስቡት ስንት ጊዜ ይነገድብን?
    በኢንተርኔት መስመር ሁሉ ዜና አቅራቢ፤ ሁሉ ውደድልኝ ባይ በመሆኑ የምናነባቸውንም ሆነ የምናያቸውን በቪዲዪ የተደገፉ ዜናዎች ጭራሽ ማመን አይቻልም። ሁሉ ለፍላፊ፤ ተናጋሪ፤ ዘፋኝ፤ አዘፋኝ፤ ተዋጊና አዋጊ በሆነበት አለም ላይ የሚቀርብልን “ሰበር ዜና” ሁሉ ሽምድምድና እግር የሌለው ለመሆኑ የሚለጥፉት ምስልና የቃል ጋጋታ በዜናው ካለው ይዘት ጋር አለመገናኘቱ አመላካች ነው። ያበደ አለም ሌላውን ያሳብዳል።
    እነዚህ ሁለት የደርግ ባለስልጣናት ከእገታ መፈታታቸው ማለፊያ ነው። እንደ እኔ እይታ ኮ/መንግስቱ ሃ/ማሪያምም ከስደት ወደ ሃገራቸው ገብተው የቀራቸውን ዘመን ቢኖሩና በጊዜአቸው በምድራቸው ቢያሸልቡ መልካም ነው ባይ ነኝ። አሁን ማን ይሙት ወያኔ በሃገራችን ላይ ካደረሰው የበለጠ በደል የደርግ ባለስልጣኖች ፈጽመዋል? በጭራሽ። መስሏቸው በመጤ የፓለቲካ ዘይቤ ተዘላዝለዋል፤ ዘልዝለዋል። ስለሆነም አቅማቸው የሚፈቅድ ሁሉ በተለምዶ የደርግ ወታደሮች የሚባሉ በራሳቸው ፈቃድ የሚያውቁትን በማስተማር፤ ሌላውን በመረዳት አሁንና ወደፊት ሃገሪቱ ለገጠማትና ለሚገጥማት አይቀሬ ፍትጊያ የራሳቸውን አስተዋጾ ማድረጉ ተገቢ ነው እላለሁ። በተረፈ በትግራይ ቆላማ በረሃዎች የሰውር እስር ቤቶችና በየከተማው ባሉ የይፋ መታጎሪያ ስፍራዎች እንዲሁም የብልጽግናው ፓርቲ በየሰበቡ ያለ አግባብ ያሰራቸው ሁሉ መፈታት ይኖርባቸዋል። ሃገርን ለመገንባት ቁርሾን መተው ተገቢ ነው። ብቀላ ብቀላን ይወልዳል። እኔ በቅርብ ቀን በአማራ ክልል የማየውና የምሰማው ጉራ ሁሉ ወያኔን ወያኔን ይሸታል። ሙያ በልብ ነው። ለነገሩ ኦሮሚያስ ውስጥ ያው አይደል፡፤ ቱልቱላ ሁሉ። ምን ጥቅም ይገኛል ወገንህን አርደህና አሳደህ? ዞረህ ተመልሰህ እኮ እንደ ጉንዳን እርስ በራስህ ነው የምትባላው? የመንደር ፓለቲአክ፤ የክልል እይታ አፈር ይመለስበት። አፍሪቃዊ፤ አለም አቀፋዊ እይታ ይኑረን። ሌላው ሁሉ አሻሮ ነው። እናንተ አሁን ከጣሊያን ኤምባሲ የተፈታችሁ ደግሞ ያለፋችሁትን ሁሉ በመጽሃፍ መልክ ለቀሪና ቋሚ ትምህርት እንዲሆን እውነቱን ጻፉልን። በቃኝ!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here