Home News and Views አልወጣ ያለቺው የወያኔ ሶስተኛዋ ነፍስ ./ቋጠሮ/

አልወጣ ያለቺው የወያኔ ሶስተኛዋ ነፍስ ./ቋጠሮ/

ወያኔ እስካሁን ሁለት ሞት ሞታለች፡፡ ፖለቲካዊና ወታደራዊ፡፡ በድርጅትም ሆነ በጋንታ አምሳል ህልው አይደለቺም ፡፡ ፖለቲካዊ ነፍሷን በ3 አመት ወታደራዊ ነፍሷን ደግሞ በሶስት ሳምንት ጦርነት አጥታለች፡፡  ሶስተኛው ነፍሷ (ዲፕሎማሲያዊ) ግን እስካሁን አልወጣችም፡፡በፖለቲካውም በጦርነቱም ተሸንፋ በዲፕሎማሲው ፍልሚያ ግን እጅ አልሰጠቺም፡፡
ለዚህ ትልቁ ምክንያት ደግሞ የዘር ድርጅት አባላት ዘንድ ያለው የሚያስቀና ትጋትና ትብብር ኢትዮጵያዊ ወገን ዘንድ አለመኖሩ ነው፡፡ እነሱ ያርዳሉ፤ እነሱው ቀድመው ታረድን ብለው በጽናት ይጮሃሉ፡፡ እነሱ ይዘርፋሉ ተዘረፍን ብለው በትጋት ያለቅሳሉ፡፡ በማንነታቸው የገደሏቸውን ሰዎች ፎቶ እየለጠፉ በማንነታችን ተገደለን ብለው ይከሳሉ፡፡ በተቃራኒው እውነት የያዘው ኢትዮጵያዊ የተበዳይ ተከሳሽ እየሆነ ነው፡፡
በሌላው በኩል የኢትዮጵያ መንግስትም ቢሆን ፖለቲካዊና ወታደራዊ ፍልሚያውን በመራበት ቅልጥፍናና ብልሃት የዲፕሎማሲውን ጦርነት ሲመራ አይታይም፡፡ በርግጥ የዲፕሎማሲው ጦርነት አስቸጋሪ ነው፡፡ በርካታ አለም አቀፍ ተከፋይ ሚዲያዎች የወያኔን አካላዊና ፖለቲካዊ ሞቷን ክደው በድኗ ላይ ነፍስ ለመዝራት እየታተሩ መሆናቸውም እውነት ነው ፡፡ የዲፕሎማ ሲው አለም ደላሎች ሩጫም ቀላል ኣይደለም፡፡ ግብጽን መሰል ቋሚ ጠላትም አለን!!
ይሁንና መንግስት እንደ መንግስት ህዝቡን በማስተባበርና አገራዊ ተቋማትን በማሳተፍ በዲፕሎማ ሲውም ፍልሚያ በትጋት ከተንቀሳቀሰ 3ኛውም ድል እሩቅ እንደማይሆን በእርግጠኝነት መናገር ይቻላል፡፡ ምክንያቱም በአሁኑ ሰኣት ወያኔ ምናባዊ እንጂ አካላዊ ህልውና የላትምና 3ኛዋ ነፍሷም . . .
የነ አቦይን መጨረሻ በፍጥነት ለህዝብ ይፋ ማድረግ በራሱ ወደ ዲፕሎማሲው ድል የሚያደርስ አቋራጭ መንገድ መሆኑም ሳይረሳ ማለት ነው!!

1 COMMENT

  1. ድመት ዘጠኝ ነፍስ አላት ይባላል። ጉዳዪ ለእኔ ባይገባኝም አባባሉ ወያኔን ይመስላል። ወያኔ ሽንክ ነው። በምድራችን እንደ ወያኔ ያለ የክፋት ኮረጆ ተፈጥሮል አያውቅም። የሚገርመኝ ግን እነዚህ አረመኔዎች የራሳቸው ሰዎች ሲሞቱ ማን መሆናቸው እንዳይታወቅ አንገት ይቆርጣሉ መባሉ ነው። ከተፈጠሩ ጀምሮ በሰው ደም አይደል እንዴ ሲታጠቡ የኖሩት። የትግራይ ቆላማ በረሃዎች፤ የጎንደርና የወሎ ቦታዎች ይመስክሩ። ጥይት አናባክንም ብለው አይደል እንዴ ሰዎችን ጉድጓድ አስገብተው በጭስ አፍነው የገደሏቸው? ወያኔ ሆኖ ደም ያላፈሰሰ የለም። አሁን ነፍስ ግቢ ነፍስ ውጭ ሆኖባቸው ቀሚስ ለብሰውና ቄስ መስለው የሚርመሰመሱት የወያኔ ወታደራዊ መኮንኖችና የድርጅቱ ቆንጮዎች ይህ ቀን እንደሚመጣ እንዴት አይገባቸውም? የግብጽ አይዞህ ባይነት፤ የሱዳን በኢትዮጵያ ድንበር ወረራ አድርጎ የማምለጫ ኮሪደር ማመቻቸት ሁሉ ልፋት እንጂ ጠቀሜታ የለውም። አበው እንደሚሉት ብርሌ ከነቃ አይሆንም እቃ ነው። ወያኔ ቀድሞ በነበረበት ስፍራ ላይመለስ ተሰናብቷል። ይህ ማለት ግን በውስጥም ሆነ በውጭ የተንኮል ሴራ ከመስራት ይገታሉ ማለት አይደለም። ተከፋይ ነጮች የሚጽፉትን ማየት ብቻ ለዚህ በቂ መረጃ ይሆናል። በሞቀ ቤታቸው ላይ ተቀምጠው የሌለ የሰው ቁጥር 50 ሺህ ተፈናቀለ እርዳታ ገለ መሌ የሚሉት የራሳቸውን ኪስ ለመሙላት እንጂ ለትግራይ ስደተኞች ተጨንቀው አይደለም። የትግራይ ህዝብ ለሱዳን፤ ለእርዳታ ሰጪ ድርጅቶችና ለወያኔ ተስፈኞች አሁን መነገጃ ነው። ወያኔ በ 45 ዓመት የውሸት ትረካው ሰውን ስለከፋፈለው በስደትም ቢሆን መገዳደላችን፤ መደባደባችን ጭራሽ አይቀሬ ነው። አንድ በነጮች በሰማኒያዎቹ በሱዳን ውስጥ በተራዶኦ ድርጅት የሰራ ነጭ እንዲህ ሲል አጫወተኝ። ” ስማ ተስፋ አለ እኔ ልንገርህ አይኔ ያየውን በዚያ ፋኦ በሚባል የስደት ስፍራ” ሁሉም የመጡት ከትግራይ ነው። ይበልጦቹ ሴቶች ናቸው፡፤ ሞት በየቀኑ ነው። ከዚያ አንድ የመጠለያ ስፍራ ጠቦ ሌላ ተከፈተ ያም ሞልቶ ሌላ ተከፈተ፡፤ ይህ በዚህ እንዳለ ሳይታሰብ የወንዶችም ቁጥር እየበዛ በእኛ ስራ ላይም ያገባናል የሚሉ እንቅፋት መሆን ጀመሩ ይልና አንድ ቀን በሳርና በትንሽ አጥር አጥረን ያቆምናት ፋርማሲ ተዘርፋ አደረች በህዋላ ስንሰማ ዘራፊዎቹ ወያኔና የሱዳን ፓሊሶች መሆናቸው ታወቀ፡፤ ሌላ ልንገርህ በስደተኛው ድንኳን ውስጥ ሰው ከሰው ጋር እንዳይገናኝ በማድረጋቸው ሰው ተቀራርቦ መነጋገር አይችልም ነበር። አልፎ ተርፎም ለእኔ አስተርጓሚና በሌላም ሙያ ለምሳሌ በላቦራቶሪ ይረድን የነበሩ ልጆች በወያኔ በተደራጅ ሰዎች መደብደባቸው ትዝ ይለኛል ካለ በህዋላ ቆም ብሎ አይኖቹ እንባ አቀረሩ። ምነው ምን ሆንክ ስለው የሁለት ሰዎች ድብደባ በተለይም የአንድ ወጣት ድብደባ ትዝ ይለኛል አለ። ስማቸው ትዝ ይልሃል ስለው አዎን አንድ በህዋላ እንደተረዳሁት የራሳቸው ሰው ነው። ማለት የትግራይ ተወላጅ ግን የንጉሱ ደጋፊ የነበረ ባለ ሃብት ታደሰ ይባላል። ወጣቱ ደግሞ የአዲስ አበባ ልጅ ዳንኤል የሚባል አማራ በመሆኑ ጥርሱን ሁሉ እንዳወለቁት በድብደባ ትውስ ይለኛል አለ። ይህ ሰው መጽሃፍ ጽፎአል። ግን በመጸሃፉ ውስጥ እነዚህን አላካተተም። ይህን ሁሉ ማለት ለምን አስፈለገ? ሃሳባችን የወያኔ ሴራ ማብቂያ አይኖረውም። የማይጠቀሙበት ዘዴ የለም። መርዝ፤ በመኪና መግጨት፤ መሰወርና መግደል፤ በማጅራት መቺ ማስደብደብ፤ በእሳት የማምለኪያ ቦታዎችንና ገቢያዎችን ማውደም፤ የትግራይን ህዝብ ራሳቸው ገድለው ሌላ ሃይል እንደ ገደለው አድርገው ማቅረብ፤ ሃገርና ድንበርን መሸጥና መለወጥ ሌላም በጤነኛ ሰው የማይታሰብ ግፍን ያደርጋሉ። በውጭም ሆነ በውስጥ ያየነው ይህኑ ነው። ባጭሩ ወያኔዎች ከራሳቸው ጋር የተጣሉ ሳጥናኤሎች ናቸው።
    ስለሆነም አሁን በትግራይ የሚታየው አንጻራዊ ሰላም እንዲደፈርስ በማስፈራራትም ሆነ በሌላ መልኩ ሰውን ወደ ጭንቅ መክተታቸው አይቀሬ ነው። ወያኔ ማለት አልሸባብ፤ በአፍጋኒስታንና በሶሪያ፤ በኢራቅ በየመን እንደምናያቸው የእምነት እብዶች ያበድ ናቸው። የሰው ሰላም መሆን አይዋጥላቸውም። ለዚህም የሱዳን ወታደራዊ ክንፍና የግብጽ አይዞታ ከጎናቸው ነው። አልወጣ ያለችው የወያኔ ነፍስ መሰንበቷ ቀድመው ስለተዘጋጅና ነገሮችን ስፍራ ስፍራ አስይዘው የውሸት ወሬ የሚነዙ ሰዎችን ስለቀጠሩ ነው። የሚገርመኝ ተምረናል የሚሉ የአዞ እንባ አፍሳሾች የእነዚህን የስማ በለው ወሬ ያልሆነ ምስልና ቪዲዮ እየለጠፉ አለምም አብሮአቸው እንዲበጭጭ ጥሪ ማሰማታቸው ለሰው ልጆች ያላቸው እይታ ዘር ተኮርና በውሸት የተላበሰ እንደሆነ ያሳያል። ሞት ለማንም አይቀርም። የዘገየ ቢመስልም በጊዜው ብቅ ይላል። ሰው እንዴት ውሸትና የዘር ፓለቲካን እንደተጋተ ያንቀላፋል? ህይወትን ከፓለቲካ ባሻገር ማየት የማይችል ሰው ድርቡሽ ነው። ስለሆነም የወያኔ ለቅሶ ለመድረስ የምትሯሯጡ ረጋ በሉ። ወያኔ ባለ ዘጠኝ ነፍስ ነው። አንድ ጋ ሲሞት ሌላ ጋ ይተነፍሳል። ተንኮላቸው፤ ዘርተውት ያለፉት የ 45 ዓመት የውሸት ፓለቲካ ገና ብዙ ገመና ያመጣል። አዋቂ ሰው በቀን ይደገፋል። ጉራው፤ ቱልቱላ መንፋቱ፤ ቀረርቶው ሁሉ ለአለንበት ዘመንና የውጊያ ስልት አይመጥንም። ከዚህ በህዋላ ምን ይመጣ ይሆን? እንዴትስ ራሳችን መከላከል እንችላለን። ጠላት የሚታጠቀው ትጥቅ ምን ይመስላል? በማለት ራስህና የጠላትን ጎራ ቃኝቶ በተጠንቀቅ መቆም ተገቢ ነው። ወያኔ ገድሉን በራሱ ለራሱ ጽፎ ራሱ እሳት ከቶ ተመልሶ የወጣበት ጫካ ከ 45 አመት በህዋላ ገብቶ የመሽገ ድርጅት ነው። ነጻነት ይሉሃል ይሄ ነው። ተገፋሁ ብለህ በወረፋህ ሌላውን አርደህና አሳርደህ ሃገርን ከፋፍለህ ተመልሰህ ጫካ? አይ ጊዜ አይ ነጻነት፤ አይ ንግድ በወረፋ መገዳደል ይህቺ ናት የእኛ ሃገር ፓለቲካ! ሌላው ሁሉ አሻሮ ነው። የሚሆነውን ቆይተን እንይ! በቃኝ!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here